የመድረክ መሪ ስለኢሕአዴግ መጭ ስብሰባዎችና ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ /ፎቶ - ፋይል/

ከኢሕአዴግ አዲስ ለውጥ እንደማይጠብቁ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገልፀዋል።

ከኢሕአዴግ አዲስ ለውጥ እንደማይጠብቁ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገልፀዋል።

የፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ምክትል ሊቀመንበርና የመድረኩ የውጭ ግንኙነቶች ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር በየነ ከአሜሪካ ድምፅ በወቅቱ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ ጉዳይ ላይ ሃሣብ እንዲሰጡ ተጠይቀው አካሄዱ እስከአሁን ከታየው የተለየ እንደማይሆን፤ ሊቀመንበር ሆኖ የሚመረጠው ሰው የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

ፕሮፌሰር በየነ መጭው የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እገሌ ሊሆን ይችላል ብለው ከመገመት ተቆጥበዋል።

ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሃገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ሰፊ ሚና እንዳላቸው የጠቆሙት የመድረኩ መሪ የኢትዮጵያ ሕዝብ አብሮ የሚኖረው “ማንም ጉልበተኛ ጨምድዶ ስለያዘው ሳይሆን ጥቅሙን ስለሚያውቅ ነው” ብለዋል። በኢትዮጵያም እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ለሙሉው ቃለ ምልልስ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የመድረክ መሪ ስለኢሕአዴግ መጭ ስብሰባዎችና ስለኢትዮጵያ ፖለቲካ