ኢትዮጵያዊቷ ሙኒት መስፍን እና ባንዷ የዋሚ ሙዚቃ ሽልማት ተቀዳጁ
Your browser doesn’t support HTML5
ኢትዮጵያዊቷ አቀንቃኝ ሙኒት መስፍን ባለፈው ቅዳሜ በቡድን እና በተናጥል ሁለት ሽልማቶችን ተቀዳጅታለች። ሙኒት 'አቤት አቤት' በሚለው ዘፈኗ በተናጥል ስታሸንፍ ላክሬያ ከተሰኘው ባንዷ ጋር ያወጣችው አልበም ዋሚ የተሰኘው የዋሺንግተን ዲስ እና አካባቢዋ አርቲስቶች ሽልማት አሸንፋለች። ኤደን ገረመው ትላንት ማምሻውን ሙኒትን እና ባንዷን ለትዕይንት ሲዘጋጁ አግኝታ አነጋግራቸዋለች። ቆይታቸው ሙኒት የላክሬያ ባንድ አባላትን ከምታስተዋውቅበት ይጀምራል።