ዋሺንግተን፤ ዲሲ —
አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ - በናይል ተፋሰስ ሃገሮች የትብብር ድርጅት - የምሥራቅ ናይል ሃገሮች የቴክኒክ ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር
Your browser doesn’t support HTML5
የኅዳሴ ግድብ ስብሰባ ካይሮ ላይ እየተካሄደ ነው
በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብፅ መካከል የሚደረገው የኅዳሴ ግድብ ድርድር ዛሬ ካይሮ ላይ ተጀምሯል፡፡
የዛሬው የካይሮ ስብሰባ ቀደም ሲል በሃገሮቹ በተደረሰበት ስምምነት መሠረት በኅዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ተጨማሪ ጥናቶችን ያካሂዳል የተባለ ዓለምአቀፍ አማሪካ ቡድን ለመቅጠር የተጠራ ነው፡፡
የሦስትዮሽ ስብሰባው ዛሬና ነገ የሚካሄድ ሲሆን ተሣታፊዎቹ በየሃገሮቹ የውኃና መስኖ ሚኒስትሮች የሚመሩ ልዑካን መሆናቸው ታውቋል፡፡
በናይል ተፋሰስ ሃገሮች የጋራ ትብብር ጅማሮ ወይም ድርጅት ኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ግብፅና ደቡብ ሱዳን የሚገኙበት የምሥራቅ ናይል ሃገሮች የቴክኒክ ፅ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ የቪኦኤ የሰጡትን ማብራሪያ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡