የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ህጋዊ የውጭ ሀገር ዜጎችን ወርሃዊ ክፍያ ማስከፈል ጀመረ

Your browser doesn’t support HTML5

ቤተሰብ መሥርተው ለብዙ ዓመታት ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን በአዲሱ ክፍያ ንረት ምክንያት ቅሬታ እንዳላቸው ለቪኦኤ ገልፀዋል። ካለፈው ሐምሌ አሥር ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የመጀመሪያው በወር የአንድ መቶ ሪያል የነፍስወከፍ የክፍያ ተመን በየዓመቱ በመቶ ሪያል እየጨመረ እንደሚሄድ ነው ደንቡ የደነገገው። በሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሪያድ በሚገኘው የማኅበረሰብ ቢሯቸው አማካኝነት ተሰባስበው መፍትሄ ይሆናሉ ባሏቸው ሃሳቦች ላይ ተወያይተው ነበር።