የ2009ዓ.ም. የቀን ገቢ ግምት የተጋነነና ትርፍና ኪሳራችንን ግምት ያላስገባ ነው፤ ያሉ የአዲስ አበባ ግብር ከፋዮች ማማረራቸውን ቀጥለዋል፡፡
አዲስ አበባ —
የ2009ዓ.ም. የቀን ገቢ ግምት የተጋነነና ትርፍና ኪሳራችንን ግምት ያላስገባ ነው፤ ያሉ የአዲስ አበባ ግብር ከፋዮች ማማረራቸውን ቀጥለዋል፡፡
የቀን ገቢ ግምቱ በትክክል መሠራቱን የሚገለፀው የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን በበኩሉ፣ የተጋነነ ግምት ካለ ግን፣ እንደሚስተካከል አስታውቋል፡፡
እንደዚህ ዓይነት ቅሬታ የተነሳበት የቀን ገቢ ግምት አይቼ አላውቅም ብለዋል በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፡፡ አነስተኛ ሱቆች ወደ ሚበዙበት የከተማዋ መንደር ለደቂቃዎች ጎራ ማለት ብቻውን የቅሬታውን ስፋት መረዳት ያስችላል፡፡
የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Your browser doesn’t support HTML5
የአዲስ አበባ ግብር ከፋዮች ማማረር ቀጥለዋል