“የአይሲስን ሸማቂዎች ድል መንሳታችን ጥርጥር የለውም” የሶማሌ ጦር አዛዥ

Your browser doesn’t support HTML5

የሶማሊያዋ ከፊል ራስ ገዟ የፑንትላንድ ኃይሎች አንድ ወር ለተቃረበ ጊዜ የእስላማዊው ጽንፈኛ ቡድን ተዋጊዎች በመሸጉባቸው ተራራማ አካባቢዎች ላይ የተነጣጠረ ጥቃት ሲሰነዝሩ ቆይተዋል።

ከሁሉ የበረታው ውጊያ የተካሄደው የፑንትላንድ ጦር ባለፈው ሳምንት መገባደጂያ ከቦሳሶ ደቡብ ምሥራቅ 150 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የምትገኘውን ወሳኝ ሥፍራ ቱርማሳሌን ባስለቀቁበት ወቅት ነው።