ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ድንበር ላይ በቅርቡ የተቀሰቀሰው ውጊያ ከሔግሊጅ፥ ከታሎዲና ከሌሎች በደቡብ ሱዳን ኮርዶፋን ክፍለ ሀገር የሚገኙ ከተሞች 35 ሺህ የሚጠጉ ሰዎችን አፈናቅሏል።
በተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር /ዩኤንኤችሲአር/ መግለጫ መሠረት ድርጅቱ በያዝነው ሚያዝያ ወር ውስጥ ብቻ ከብሉ ናይል ስቴት አዲስ የተፈናቀሉ 2 ሺህ 400 ስደተኞችን በጎረቤት ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ጉምዝ ካምፖች ተቀብሏል።
ይህንኑ ትናንት ሐሙስ የወጣውን የመንግሥታቱን ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር መግለጫ መነሻ በማድረግ የኮሚሽነሩ የአዲስ አበባ ፅ/ቤት ቃል አቀባይ አቶ ክሱት ገብረእግዚአብሔር ለቪኦኤ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡