በድሬዳዋ የኮሮናቫይረስ የነበረባቸው ሰዎች ነፃ ተባሉ

በድሬዳዋ የኮሮናቫይረስ የነበረባቸው ሁለት ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ ሆነው ወደቤታቸው ሲመለሱ ሌሎች ሦስት ሰዎች ደግሞ የኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሦስቱም ሰዎች ከጂቡቲ ተመልሰው በለይቶ ማቆያ ያሉ ናቸው።
ከጂቡቲ ተመልሰው በለይቶ ማቆያ የሚገኙ 574 ሰዎች በሙሉ የደም ናሙናቸው ተልኮ ውጤት እየተጠበቀ ነው ተብሏል።
ከጂቡቲ በህጋዊ መንገድ የሚገቡት ላይ ሙሉ በሙሉ ባለሙያዎችና የፀጥታ አካላት ቢኖሩም በህገወጥ መንገድ የሚገቡትን መቆጣጥር ግን አስቸጋሪ ሆኗል ተብሏል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

በድሬዳዋ የኮሮናቫይረስ የነበረባቸው ሰዎች ነፃ ተባሉ