ዩናይትድ ስቴትስ ከሐማስ ጋራ መነጋገሯን ያረጋገጡት ትረምፕ ቡድኑ ታጋቾቹን በአስቸኳይ እንዲለቅቅ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

  • ቪኦኤ ዜና

Your browser doesn’t support HTML5

ዩናይትድ ስቴትስ ከሐማስ ጋራ መነጋገሯን ያረጋገጡት ትረምፕ ቡድኑ ታጋቾቹን በአስቸኳይ እንዲለቅቅ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጡ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ሐማስ የተቀሩትን እስራኤላዊያን ታጋቾች በአስቸኳይ መልቀቅ እንዳለበት ትላንት ሐሙስ በድጋሚ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል::

በዩናይትድ ስቴትስ በሽብርተኛ ቡድንነት የተመዘገበው ሐማስ በበኩሉ "ታጋቾቹን የምለቀው ዘላቂ የተኩስ አቁም ከተደረገ ብቻ ነው" ብሏል:: በተጨማሪም ዩናይትድ ስቴትስን እና እስራኤልን "ከድርድሮቹ ወደኋላ ለማፈግፈግ እየሞከሩ ነው" በማለት ወንጅሏል::