የአሜሪካ የጉዞ እገዳ - አዲስ

ዋይት ሃውስ

የደኅንነት ደረጃዎችን አያሟሉም ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት በፈረጇቸው ስድስት ተጨማሪ ሃገሮች ላይ የትረምፕ አስተዳደር በሕጋዊው ኢሚግሬሽን ላይ ገደብ እንደሚጥል አስታውቋል።

ከኪርጊዝስታን፣ ከማያንማር፣ ከኤርትራ፣ ከናይጀሪያ፣ ከሱዳንና ከታንዛንያ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለመጓዝ በሚፈልጉ ሰዎች ወይም ኢሚግራንቶች ላይ አንዳንድ የመግቢያ ፍቃዶች ወይም ቪዛዎች ላይ አዳዲስ እገዳዎችን እንደሚያደርጉ ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።

አዋጁ ላይ ፕሬዚዳንቱ የፊታችን ዐርብ ከፈረሙ በኋላ ከየካቲት 12/2012 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ታውቋል።

ሰፋ ላለ መረጃና ለባለሙያ ማብራሪያ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

Your browser doesn’t support HTML5

የአሜሪካ ጉዞ እገዳ - አዲስ