የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት /ዩኤስአይዲ/ አስተዳዳሪ ማርክ ግሪን ከነገ ጀምሮ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ ያደርጋሉ፡፡
አዲስ አበባ —
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት /ዩኤስአይዲ/ አስተዳዳሪ ማርክ ግሪን ከነገ ጀምሮ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ ያደርጋሉ፡፡ አስተዳዳሪው የመጀመሪያ ለሆነ ጉብኝት ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙት 8.5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በድርቅ ምክንያት ለዕርዳታ በተጋለጡበት ወቅት ነው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት /ዩኤስአይዲ/ አስተዳዳሪ ማርክ ግሪን ወደ አፍሪካ ብሎም ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዚ የመጀመሪያቸው ነው፡፡ ጉብኝታቸውም በድርቅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው የኢትዮጵያውያን ቁጥር መጨመሩ ይፋ ከተደረገበት ወቅት ጋራ ተገጣጥሟል፡፡
በድርጅታቸው የሚደገፉና የማኅበረሰቡን የተፈጥሮ አደጋ የመቋቋም ብቃት እንዲሁም የኢኮኖሚ አቅም የሚያጠናክሩ ፕሮጀክቶችን ይመለከታሉ፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
Your browser doesn’t support HTML5
የዩኤስአይዲ አስተዳዳሪ በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው