ኤደን ገረመው በትምራን የሲቪክ ማኅበር የመርኃግብር አስተባባሪ የሆነችውን ወጣት ቤተልሔም አለምን እና የኤውብ የሴት አመራሮች ማኅበር አጋር አመስራች እና ዳይሬክተር ወ/ሮ ናሁሰናይ ግርማን አነጋግራ ያሰናዳችው ዘገባ በመቀጠል ይቀርባል።
የሴቶች ውክልና እና ሴቶችን ማብቃት በኢትዮጵያ
Your browser doesn’t support HTML5
ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የላቀ ብዛት ያላቸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የሚኒስትር ቦታዎች እና የፍትህ አካላት ሃላፊነት ላይ ያሉ ሴት አባላት እንዳሏት አሃዞች ቢያሳዩም፤ ነገር ግን በፖለቲካውም ሆነ በተለያዩ ማኅበራዊ ዘርፎች ላይ የሚሳተፉት ሴቶች በቂ እና አጥጋቢ የሆነ የውሳኔ አቅም እንዲኖራቸው የሚያደርግ ምህዳር እንደሌለ በሴቶች ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት ይናገራሉ።