ጠላን ከጓዳ ያወጣው ሴሎ ክራፍት ጠላ

Your browser doesn’t support HTML5

በቱሪዝሙ ዘርፍ ውስጥ ይተዳደር የነበረው ወጣት ዮሃንስ አይቸው በኮቪድ ምክንያት ገበያ እየቀነሰ ሲመጣና ስራ ሲጠፋ አንድ ዓመት ሙሉ ስራ አጥ ሆኖ እንደተቸገረ ይናገራል፡፡ ይሁንና የኮቪድ የጽሞና ጊዜ ከዚህ ቀደም ሲያስበው የነበረውን የንግድ ሃሳብ እንዲሞክር ዕድሉን ፈጠረለት፡፡ ሴሎ ክራፍት ጠላ በአሁን ሰዓት ጠላን ከጓዳ አውጥቶ በሆቴል ደረጃ ያቀረበ ሲሆን ለብዙ ጠላ መጥመቅ የሚችሉ እናቶች የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል፡፡