የቀድሞ ወይንም የጥንት አውሮፕላኖች በአስር የአፍሪካ ሀገሮች ሰማይ ላይ የበረራ ውድድር ለማካሄድ እሁድለት ኬንያ አርፈው ነበር። ከደቡብ አፍሪካ የተነሱት ጥንታዊ አውሮፕላኖች መካከል የሚደረገው የበረራ ውድድር ዋና አላማ ለተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ(UNICEF) ፣ ለብሄራዊ አእዋፋት የዱር እንስሳት ጥበቃ እንዲሁም ዘርን በመዝራት ደንን መልሶ በማልማት ላይ ለሚገኘው ቡድን የእርዳታ ገንዘብን ለማሰባሰብ ነው።
በዋሽንግተን ዲሲ ቨርጂኒያና ሜሪላንድ የሚገኙ ከሶስት መቶ የሚበልጡ አዲስ መጥ ስደተኞች የአሜሪካውያንን የምስጋና ቀን ተሰባስበው አክብረዋል። ዝግጅቱን ያስተባበረው በስደተኞች ዙሪያ የሚሰራው መንግስታዊ ያልሆነው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የልማት ድርጅት ኢሲዲሲ (ECDC) ነበር። በኢሲዲሲ ቅርንጫፍ መስሪያቤት የአፍሪካ ልማት ስደተኞች ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳራ ዙሎ እና የድርጅቱ ዋና አስተባባሪ ቤተልሄም ደስታን ስለነዓሉ አከባበር መስታወት አራጋው አነጋግራለች።
ሙሉጌታ አባተ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በተወለደ በሀምሳ አመቱ ባሳለፍነው ሳምንት ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ለቤተሰቦቹና ለሙያ አጋሮቹ እንዲሁም ለአድናቂዎቹ መፅናናትን ከልብ እንመኛለን።
የአሲድ ጥቃት የደረሰባት መሠረት ንጉሤ ታሪኳን ለቪኦኤ አጫውታለች፡፡ የሕግ ባለሙያዎችና የሴቶች መብቶች ተሟጋቾችም አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል፡፡
ወ/ሮ ማሪያ ሙኒር የህግ ባለሙያ ናቸው። በጥብቅና እና በዳኝነት ለረጅም አመት አገልግለዋል። የሴቶች ማረፊያና ልማት ማህበር ወይንም 'ሴፍ ሀውስ' የተባለ ድርጅት መስራችና ስራአስኪያጅ ናቸው።
ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር ከሌሎች የሩጫ አትሌቶች የተለየ የአሯሯጥ ስልት ነበረው፤ በመጨረሻው ዙር ከየት መጣ የሚያሰኝ ፍጥነትን በመጨመር ደጋግሞ ያሸነፈበት ስልት። ለዚህም ይመስላል ማርሽ ቀያሪው የሚል ተቀጥያ የአድናቆት ስም የተሰጠው።
በአሯሯጥ ስልቱ ማርሽ ቀያሪ በመባል የሚታወቀው ሻምበል ምሩፅ ይፍጠር በሰባአራት አመቱ ከትላንት በስትያ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል የሚል ዜና ደርሶን በትላንትናው ዕለት እኛም ዜናውን ለናንተ መዘገባችን ይታወሳል። ዜናው ስህተት በመሆኑ ሻምበል ምሩፅ ይፍጠርንና እናንተን አድማጮቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን።
መሰረት ንጉሴ ከባህርዳር ሰማንያ ኪሎ ሜትር ላይ በምትገኘው በዳንግላ ከተማ ትሰራበት በነበረው ሆቴል ውስጥ በርካታ ደምበኞችን ያፈራች የምግብ ባለሙያ ነበረች። ቤተሰቦቿን ሰርታ ከምታገኘው ትደጉምም ነበር ።
በኢትዮጵያ በተንቀሳቃሽ የእጅ ስልኮች የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ መንግስት ገደብ ከተጣለ አራት ሳምንታት ተቆጠሩ።
አሜሪካኖች አዲሱን ወይም አዲሷን ፕሬዝዳንታቸውን በሚቀጥለው ሳምንት ማክሰኞ ይመርጣሉ። በዩናይትድ ስቴትስ የምጣኔ ሃብትና የውጭ ፖሊሲ ጉዳዮች ትልቅ ቦታ ቢኖራቸውም የህዝብ አስተያየት መለኪያዎች እንደሚጠቁሙት ለሁለቱ እጩ ተወዳዳሪዎች ለዲሞክራቷ ሒላሪ ክሊንተንና ለሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ መራጮች ድምፃቸውን የሚሰጡት በተወዳዳሪዎቹ የግል ባህሪ ላይ ተመስርተው ነው። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ።
ፈጣን መተጫጫ ወይም ስፒድ ዴቲንግ (Speed Dating) ይባላል። አዲስ ትዳር ፈላጊን ለጥቂት ደቂቃ በማነጋገር ለጓደኝነት ለማጨት መሞከር፤ ካልሆነም ያው.. ይቀራላ! መተው። በጃፓን ፈጣን መተጫጫን ያዘጋጀው ኩባንያ የተክለሰውነት ውበት ብቻ ጓደኝነትን አያመጣም በሚል፤ ፊትን ለህክምና አገልግሎት በሚውል ጭምብል በመከለል የፍቅር ጓደኛ ፈላጊ ወንድና ሴት ለማገናኘት እየተጋ ነው።
አሜሪካዊያን በአማካይ አብዝተው ስጋ ይመገባሉ። እንደ ዶሮና ተርኪ ካሉ ነጭ ስጋዎች በይበልጥ ቀይ የከብት ስጋ ላይም ያተኩራሉ። እንደሚታወቀው ስጋ ደግሞ በፕሮቲን የተሞላ ነው። ረጅምና ጤናማ ህይወት ለመምራት የስጋ አመጋገብን መቀነስ፣ አትክልቶች አብዝቶ በመመገብ ለሰውነት የሚያስፈልገውን በቂ ፕሮቲን ለማግኘት ይቻላል ይላል አዲሱ ጥናት።
በማላዊ የሚገኙ ሴት ተማሪዎች ራሳቸውን ከፆታዊ ጥቃት እንዴት መከላከል እንደሚችሉ ስፖርታዊ ስልጠንና በመውሰድ ላይ ይገኛሉ። ከ18 አመት በታች በሆኑት የማላዊ አዳጊ ሴቶች ላይ በተደረገው የፆታዊ ጥቃት ጥናት ከ5 ተማሪ አንዷ የጥቃቱ ሰለባ እንደሆነች ተረጋግጧል። ስልጠናው ከኬንያ በመጡ የግብረሰናይ ድርጅት አባላቶች ነው በመሰጠት ላይ የሚገኘው።
በሚቀጥለው አመት ለሚዘጋጀው 'ማንዴላ ዋሽንግተን' መርሃ ግብር ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ወጣት አፍሪካውያን በዝግጅቱ ለመካተት በማመልከት ላይ ናቸው።
ማዕከሉ በየአመቱ በመስከረም ወር ከኢትዮጵያውያን ገጣሚያን በተጨማሪ አፍሪካውያን ገጣሚያንና ደራሲዎች የሚሳተፉበት መድረክ ያዘጋጃል። የዘንድሮውም በሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ በሜሪላንድ ግዛት የተለያዩ የአፍሪካ ሃገር ገጣሚያን የተሳተፉበት ምሽት ባሳለፍነው ወር መጨረሻ ተዘጋጅቶ ነበር።
አልፋ የጡት ካንሰር ህሙማን መርጃ ድርጅት በየአመቱ በሚዘጋጀው በዚህ የእግር ጉዞና አጭር ርቀት ሩጫ ከተሳታፊዎች የሚገኘው ገንዘብ በኢትዮጵያና በኤርትራ ለሚገኙ የካንሰር ህመምተኞችን እርዳታ ይውላል። በዚህ አጭር ርቀት ሩጫና የእግር ጉዞ ላይ ከተሳተፉት መካከል ጥቂቶቹን አነጋግረን ነበር። ሁለተኛው ክፍል እነሆ።
የያዝነው የጥቅምት ወር በአለም አቀፍ ደረጃ የጡት ካንሰርና የሚያስከትላቸው ችግሮች የሚታሰብበት ወር ነው። ይህንኑ ተንተርሶም ባሳለፍነው ቅዳሜ በዋሽንግተን ዲሲና በአጎራባች ክፍለግዛቶች በሜሪላንድና ቨርጂኒያ ነዋሪ የሆኑ ቁጥራቸው ከሁለት መቶ ሃምሳ በላይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የአጭር ርቀት ሩጫና የእግር ጉዞ አካሂደው ነበር። የዝግጅቱ የመጀመሪያ ክፍል እነሆ።
ይህ የአዳጊ ሴቶች ቀን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ከአምስት አመታት በፊት መብታቸውን ለማስጠበቅና የሚገጥሟቸውን ፈተናዎች ለመከላከል ይቻል ዘንድ ለማሳሰብ ነው የሚከበረው። የዩናይትድ ስቴትስ ቀዳሚዋ እመቤት ሚሼል ኦባማ ይህንን ቀን ‘አዳጊ ሴቶችን እናስተምር’ በሚል የተጀመረ ዓለም አቀፍ ዘመቻን ለማስተዋወቅ ተጠቅመውበታል። የቪኦኤው ዘጋቢያችን ሮበርት ራፌል የዘገበውን መስታወት አራጋው ታቀበዋለች።
በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ዲግሪ በተለያየ ሙያ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እረፍታቸውን ጨርሰው የ2009 የትምህርት ዘመን ለመጀመር ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ ወደየ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ።
ለኢትዮጵያ የአዲስ አመት ዋዜማ በአሌክሳንደሪያ ቨርጂንያ በማደጎ በአሜሪካን ሃገር ለሚገኙ ህፃናትንና አዳጊ ወጣቶች ባህላቸውንና ታሪካቸውን እንዳይረሱ በሚል እሳቤ በኔትዎርክ ኦፍ ፋሚሊ ሰርቪስ ፕሮፌሽናልስ ባህላዊ ምሽት ተዘጋጅቶ ነበር። በዝግጅቱ ላይ የቨርጂንያ ከንቲባን ጨምሮ የባህልና ቅርስ ተመራማሪዎች ተገኝተው ነበር። ይህን ዝግጅት ያዘጋጀውን የኔትዎርክ ኦፍ ፋሚሊ ሰርቪስ ፕሮፌሽናልስ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈራ ሃይሉን ስለዝግጅቱ ይገልጽልናል።
ተጨማሪ ይጫኑ