መራኄ መንግሥት አብይ አሕመድ በጠቅላይ ሚኒስትነት የመጀመሪያ የሥራ ጉብኝታቸውን ዛሬ፣ ቅዳሜ መጋቢት 20/2010 ዓ.ም. ሶማሌ ክልል ዋና ከተማ ጂጂጋ ላይ አድርገው ውለዋል።
በእሥራኤል የጋዛ ሠርጥ ወሰን ላይ ዛሬ በተነሣ ግጭት ቢያንስ አንድ ፍልስጥዔማዊ ተገድሎ ሌሎች ቁጥራቸው አርባ የሆነ ሰዎች ቆስለዋል። ግጭቱ የተፈጠረው ከአንድ ሣምንት በፊት በዚያው አካባቢ ተካሂዶ በነበረ ሁከት የበረታበት የተቃውሞ እንቅስቃሴ 19 ፍልስጥዔማዊያን በእሥራኤል ወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎ ነው።
በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ውስጥ የፖለቲካና የምጣኔ ኃብት ጭቆናዎች ይደረጋሉ፤ የእንቅስቃሴ ነፃነትም የተገደበ ነው ሲሉ አንድ የክልሉ ምክር ቤት አባል ለቪኦኤ ገልፀዋል።በሌላ በኩል ግን ክልሉ እየለማ ያለበት ሰላም የሠፈነበትና አስተዳደሩም መልካም ነው ሲሉ አንድ የክልሉ ፕሬዚዳንት አማካሪ ተናግረዋል።
አዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሃገሪቱን ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲ ለማሸጋገር ድፍረት ይኖራቸዋል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ የአውሮፓ ፓርላማ አባሏ አና ጎምሽ አስታውቀዋል።
አብይ አሕመድ - በኢትዮጵያ የፖለቲካ አውድ ከቅርብ ወራት ወዲህ በብዙ ሲንገዋለልና ሲንከባለል የሰነበተ ስም።
በቅርቡ ከእሥር የተፈቱትን እስክንድር ነጋን፣ ተመስገን ደሣለኝን፣ አንዱዓለም አራጌን በፍቃዱ ኃይሉን ጨምሮ 12 ሰዎች ዛሬ ምሽት ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ሥር ዋሉ።
የዩናይትድ ስቴትስ ዋና ከተማ ዋሺንግተን ዲሲና ሃምሳውም ግዛቶች በመቶዎች ሺሆች የሚቆጠሩ ሰልፈኞችን ዛሬ አስተናግደዋል። የሰልፉ መሪ ርዕስ “ለሕይወታችን እንሰለፍ” የሚል ሲሆን የጦር መሣሪያዎችን በመያዝ አሠራር ላይ የጠበቀ ቁጥጥር እንዲደረግ የሚጠይቁ ሰልፈኞች ናቸው በየአደባባዩ የወጡት።
ኢትዮጵያን የሚጎበኙ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በሚያደርጓቸው ንግግሮች “ስለሃገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ የተሳሳቱ ወይም የተዛቡ መልዕክቶችን ያስተላልፋሉ” ሲል የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ መብቶች መከበርና አካታች ወይም አሳታፊ የሆነ አስተዳደርን ለማበረታታት በሚል የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት በተለያዩ ደረጃዎች ሲመክርበት የቆየው ኤችአር 128 የውሣኔ ረቂቅ ለፊታችን ሚያዝያ ድምጭ ሊሰጥበት ተቀጥሯል፡፡
"የሁሉም ችግሮች ምንጭ የሆኑት የሥርዓቱ ቁንጮ የትግራይ ሕዝብ ልዩ ተቆርቋሪ፣ ጠበቃና ነፃ አውጭ በመምሰል በሕዝቡ ስምና ደም እየነገዱ ለጥቃት፣ ለስደት፣ ለውርደትና ለአፈና እየዳረጉት ነው" ያለው በዳያስፖራ የዓረና ትግራይ አባላትና ደጋፊዎች መሆኑን የገለፀ ቡድን ባወጣው ባለአራት ነጥብ የአቋም መግለጫ ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ያለችበትን ሁኔታ መገምገሙን አስታውቋል፡፡
የኤርትራ መንግሥት በዘፈቀደ ያሠራቸውን ሁሉ በአፋጣኝ እንዲለቅቅና ፍትሐዊ ፍርድ የሚያገኙበትን ሁኔታ እንዲያረጋግጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ አሳሰበ።
ከኢሕአዴግ አዲስ ለውጥ እንደማይጠብቁ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገልፀዋል።
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ “አገር አድን ጉባዔ” የተባለ ስብሰባ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጥራት ማቀዳቸውን ሲአትል ዋሺንግተን ላይ ለሦስት ቀናት የተካሄደ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችና የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብሰባ ተሣታፊዎች አስታውቀዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ መታወጁ “መልካም ሃሣብ አይደለም” ሲሉ “የኢትዮጵያ ማኅበረሰባዊ ድርጅቶች ትብብር” የሚባል ጥምረት ዋና ፀሐፊ ዶ/ር እርቁ ይመር ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ ተቃውሟቸውን ገለፁ።
የኢትዮጵያ የወቅቱ ሁኔታ የማይቆም የለውጥ ሂደት ላይ እንደሚገኝ የገለፁት የኢትዮጵያ የኮምዩኒኬሽንስ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ኢትዮጵያዊያን ለውጡን በመደገፍ አብረው እንዲቆሙ ጠይቀዋል። ያ ለውጥ ምንድነው? ወደ የትስ ይወስዳት ይሆን? ለምን ይሆን መንግሥት በሰላማዊ ሕዝብ መካከል የታጠቀ ኃይል የሚያሰማራውና ወታደሮቹ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተው እንዲገድሉ ባለሥልጣናቱ ትዕዛዝ የሚሰጡት? ለጠፋው ሕይወት የሚጠየቅስ ይኖር ይሆን?
የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ድንገት የመጣ አለመሆኑን የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ገለፁ።
የእሥራኤል ለጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ተነካክተውበታል በተባለ ሙስና ምክንያት ሥልጣን እንዲለቅቁ እየተጠየቁ ናቸው። ኔታንያሁ ክሦቹን እያጣጣሉ ናቸው።
የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ከሥልጣናቸው ይሰናበቱ ይዝለቁ የሃገሪቱ ፓርላማ ነገ ይወስናል። ፓርቲያቸው ግን “በቁኝ” ብሏል።
በኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባርና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል ለሦስት ቀናት ይቆያል የተባለ ውይይት ትናንት ዕሁድ ተጀምሯል። በኢትዮጵያ ባለሥልጣናትና በኦብነግ መካከል ንግግሩ የተጀመረው ተለይቶ ባልተገለፀ የኬንያ ከተማ ነው።
የጥቁሮች ታሪክ ወር በዩናይትድ ስቴትስና በካናዳ በወርኃ ፌብርዋሪ፤ በእንግሊዝና በኔዘርላንድስ በኦክቶበር በየዓመቱ ይታሰባል።
ተጨማሪ ይጫኑ