ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ወቅቶች የሚነሱ ግጭቶችና የሚፈጠሩ አለመረጋጋቶች በተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጪ መገናኛ ብዙሃን ይዘገባሉ። ሆኖም በቅርቡ በትግራይ ክልል የተካሄደውን ግጭት ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ አለመረጋጋቶችን መገናኛ ብዙሃን የሚዘገቡበት መንገድ በአብዛኛው ሀላፊነት የጎደለው ነው ሲሉ ምሁናን አስተናየታቸውን ይሰጣሉ። ለመሆኑ በግጭት ዘገባ ወቅት የመገናኛ ብዙሃን አዘጋገብ ምን መምለል አለበት? ሀላፊነታቸውስ እስከ ምን ድረስ ነው?
ተሰናባቹ 2020 ዓ.ም. በዓለም ዙሪያ በብዙ ፈታኝ ሁነቶች የተሞላ ነበር። ሚሊዮኖችን ለሞት ከዳረገው ኮቪድ 19 ወረርሽኝ አንቶ፣ የዓለም ኢኮኖሚ ማሽቆልቆል፣ የማህበራዊ ግንኙነቶች መቋረጥና ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት የተከሰቱ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ አደጋዎች እንዲሁም ግጭቶች ብዙዎችን የፈተኑ ነበሩ። ለመሆኑ 2020 ለኢትዮጵያኖች እንዴት አለፈ? በመጪው 2021 ምን ይጠበቃል?
ከጉግል ካምፓኒ ከሳምንታት በፊት በድንገት የተሰናበተችው የሰው ሰራሽ ልህቀት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) ባለሙያ ትምኒት ገብሩ የቀድሞ የስራ ባልደረቦች፣ ትምኒት እድገት ተሰጥቷት ወደ ስራዋ እንድትመለስ በደብዳቤ ጠይቀዋል። ትምኒት ግን ከጉግል ጋር ያለኝ ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ አብቅቷል ስትል ለአሜሪካ ድምፅ ተናግራለች። ጉግል ትምኒት ከስራ የተሰናበተችበት መንገድ ለፈጠረው ጥርጣሬ ይቅርታ ቢጠይቅም፣ ትምኒት ይቅርታው ለኔ አልቀረበም ስትል አልተቀበለችውም።
በአለም ዙሪያ ያሉ በአስራዎች እድሜ የሚገኙ እና ለ ሳይንስና ለሂሳብ ትምህርት ፍቅር ያላቸው ልጆች በየአመቱ የሚወዳደሩበት ብሬክ ስሩ ጁኒየር ቻሌንጅ የተሰኘ የጥሎ ማለፍ ውድድር የዘንድሮ አመት አሸናፊ፣ በካናዳ አገር ተወልዳ ያደገቸው ማሪያም ሞገስ ፀጋዬ ስትሆን በአጠቃላይ የ 400 ሺህ ዶላር ሽልማት አግኝታለች። ከአለም ዙሪያ ከተወዳደሩ 5600 ተማሪዎች መሀል አንደኛ ወጥታ ይህስ ስኬት ያገኘችው ማሪያምንና ወላጅ እናቷን መርሃዊት እዮብን አነጋግረናቸዋል።
በግዙፉ የአሜሪካ የመድሃኒት አምራች ኩባንያ ፋይዘር እና የጀርመኑ የሕክምና ቴክኖሎጂ ኩባንያ ባዮንቴክ በጋራ የሰሩት የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት በአሜሪካን አገር መሰጠት ከጀመረ አንድ ሳምንት አስቆጠረ። ለመሆኑ የኮቪድ 19 ክትባት አወሳሰድ ምን አይነት ነው? ክትባቱ ከተወሰደ በኃላ የሚኖረው ስሜትስ ምን የምስላል? ባለፈው ሳምንት ክትባቱን ከወሰዱ የመጀመሪያ የጤና ባለሞያዎች መሃል አንዱ የሆነውን ኢታና ጨመዳ ዲሳሳን ጋብዘናል።
ከኢትዮጵያ በጉዲፈቻ ወደ ተለያዩ ሀገራት ይወሰዱ የነበሩ ህፃናት በሚደርስባቸው የማንነት ቀውስና በአሳዳጊዎቻቸው በሚደርስባቸው በደል ምክንያት የውጪ ጉዲፈቻ ሙሉ ለሙሉ ከታገደ ሶስት አመታትን አስቆጥሯል። በዚህም ምክንያት የሀገር ውስጥ ጉዲፈቻ እያደገ መሆኑን የአዲስ አበባ ሴቶችና ህፃናት ቢሮ ቢያስታውቅም በዘርፉ የሚሰሩ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ግን እድገቱ ጅማሮ እንጂ በቂ አይደለም ይላሉ።
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል ባካሄደውና ህግ የማስከበር ዘመቻ ባለው ርምጃ ዙሪያ በዓለም አቀፍ ተቋማትና በተለያዩ ሚዲያዎች የሚወጡ የተሳሳቱ መረጃዎች፣ ህብረተሰቡን እያሳሳቱና ውዥምብር ውስጥ እየከተቱ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሲቪክ ማህበራት ጥምረት የተሰኘ ተቋም አስታወቀ። ጥምረቱ ይህን ያለው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮችን የሚገመግሙ ፅሁፎችን ለተለያዩ የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች በድህረ-ገፅ አማካኝነት ባቀረቡበት ወቅት ነው።
በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግስቱ መሃከል የተከሰተውን ውጊያ ተከትሎ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው በርካታ ዜጎች ህክምና ለመስጠት የህክምና ባለሙያዎች ተንቀሳቃሽ የህክምና ቡድን በማቋቋምና ግጭቱ ወደተከሰተባቸው በመሄድ የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል። ከነዚህ መሀል በጋንዲ ሆስፒታል የአንስቴዥያ ባለሙያ የሆነችውና ከሌሎች የህክምና አጋሮቿ ጋር በመሆን በወልዲያ ሆስፒታል ለተለያዩ ቁስለኞች የህክምና አገልግሎት ስትሰጥ የቆየችው መቅድም ባዬ አንዷ ናት።
በኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ኢትዮጵያ አብዛኞቹን ትምህርት ቤቶቿን ዘግታ በቆየችባቸው ግዜያት በክፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚማሩ የሁለተኛና የሶስተኛ አመት ድህረ-ምረቃ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሲከታተሉ ቆይተዋል፣ ጥቂቶችም ትምህርታቸውን አጠናቀው ለመመረቅ በቅተዋል። ይህ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየተካሄደ ያለው በቴክኖሎጂ የታገዘ የትምህርት ሂደት ምን ይመስላል፣ በትምህርት ጥራቱ ላይስ ያሳደረው ተፅእኖ አለ ወይ ስንል ጠይቀናል።
የኢትዮጵያ መንግስት ህግ የማስከበር ዘመቻ ያለውንና በትግራይ ክልል ከህወሃት ጋር ሲያካሄድ የቆየውን ውጊያ በድል ማጠናቀቁን መግለፁን ተከትሎ፣ በእርምጃው ላይ ለተሳተፉ አካላት የተዘጋጀ ልዩ የምስጋና እና የድጋፍ ስነስርዐት ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ይካሄዳል። አንጋፋው ድምፃዊ መሀሙድ አህመድን ጨምሮ በርካታ ድምፃውያን በዝግጅቱ ላይ እንደሚገኙም አዘጋጆቹ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከልና የህክምና አገልግሎት በመስጠት በቀጥታ ለሚሳተፉ የጤና ዘርፍ ሰራተኞች የተጋላጭነት ልዩ አበል እንዲከፈላቸው የሚያዘው አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ከወጣ ስድስት ወር ቢያልፈውም እስካሁን ክፍያው አልተፈፀመም። ደሞዝም ግዜውን ጠብቆ ስለማይከፈል በኮቪድ 19 ዙሪያ የሚሰሩ ባለሙያዎች ለኢኮኖሚ ጫና መዳረጋቸውንም ተናግረዋል።
ለኢትዮጵያ የኪነጥበብ እድገትና ዛሬ ላለበት ደረጃ መሰረት የጣሉት አንጋፋ ቲያትር ቤቶች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ተዘግተው በመቆየታቸው ሙያውና ሙያተኞች ትልቅ ችግር ላይ ወድቀዋል። ቀድሞውንም በተመልካች ማነስና በአማራጮች መበራከት ምክንያት ፈተናዎች የበዙበት የቲያትር ሙያ ኮሮና ይበልጥ አጣብቂኝ ውስጥ እንደከተተው የቲያትር ቤት ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ይገልፃሉ።
ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት 8.5 በመቶ የሚሸፍኑት ብሄራዊ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙት የተፈጥሮ ሀብትና የዱር እንስሳት እየተመናመኑ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል። በተለይ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች መካከል በሚገኘው የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ህገ-ወጥ ሰፈራ በመስፋፋቱ መጠለያው በሁለት ዓመት ግዜ ውስጥ ሊጠፋ እንደሚችል የመጠለያው ሀላፊዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ አገልግሎት ሰጪዎችንና ተጠቃሚዎችን በቀላሉ ለማገናኘት የሚረዳ የሞባይል መተግበሪያ የፈጠረ ወጣት እንግዳ አድርገን ጋብዘናል። እንግዳው አለም አብርሃ ይባላል። የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሲሆን ለ15 ዓመታት ያክል አሜሪካ ውስጥ በተለያዩ የቴክኖሎጂ ካምፓኒ ውስጥ ሲሰራ ቆይቷል። ከአለም ጋር በፈጠራ ስራውና የዲጂታል ማርኬቲግ ጠቀሜታ ዙሪያ ቆይታ አድርገናል።
አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከእለት ወደ እለት እየጨመረ የሚሄደው የከተማ ግርግር፣ የድምፅ ሁካታና በየመንገዱ የሚታየው የቆሻሻ ክምር ያስመረራቸው ወጣት ነዋሪዎቿ፣ ከግርግሩ ርቆ ራስን ለማዳመጥ፣ ንፁህ አየር ለማግኘትና አዳዲስ ነገሮችን ለማየት ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከከተማዋ ራቅ ወዳሉ ቦታዎች ሲጓዙ ይስተዋላል። አዲስ ሀይኪንግ የተሰኘ ከ17 ሺህ በላይ አባላት ያሉት የፌስቡክ ስብስብም እነዚህን ጉዞዎች በየጊዜው በማሰናዳት ወጣቶችን ከተፈጥሮ ጋር የማገኛነት ስራ ይሰራል።
በኢትዮጵያ ወደ ትምህርት ቤት የሚገቡ የሴት ህፃናት ቁጥር ከግዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢሄድም አሁንም ሴት ተማሪዎች አስቸጋሪ በሆኑ ሁኔታዎች የሚማሩ በመሆናቸው ከወንድ አቻዎቻቸው በበለጠ ትምህርታቸውን ያቋርጣሉ። ቀድመው ከነበሩት በሴቶች ትምህርት ዙሪያ ግንዛቤ ማነስ፣ የአቅም ውሱንነት፣ ያለእድሜ ጋብቻና የመሳሰሉት ተግዳሮቶች በተጨማሪም፣ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በብዛት የሚስተዋለው ህገወጥ ስደት ለሴት ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥ ምክንያት መሆኑን የትምህርት ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
የኮሮና ቫይረስ በዓለማችን ላይ ከተከሰተ በኃላ የሰው ልጅ ከቴክኖሎጂ ጋር ያለው ጥምረት ይበልጥ እየጠነከረ መሄዱን ተከትሎ፣ ጀርመን ሀገር የሚገኝ ስቲፍድ የተሰኘ የሚዲያ ተቋም የሰውን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ይበልጥለማቅለል የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችን ለዓለም ለህዝብ ያቀረቡ 80 ድርጅቶችን መርጦ አስተዋውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ