በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት በመካከለኛው ምስራቅና በሰሜን አፍሪካ በረሀብ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ47 ሚሊዮን በላይ ሊሆን ይችላል ሲል የዓለም ምግብ ድርጅት አስጠነቀቀ። ይሄ ቁጥር አሁን ካለው የረሀብተኞች ቁጥር ጋርሲነፃፀር በ 6.7 ሚሊዮን ከፍ ያለ ነው።
በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት እጅጉን ተመናምኖ የነበረው የደም ለጋሾች ቁጥር መሻሻል እያሳየ መሆኑን የብሄራዊ ደም ባንክ አገልግሎት አስታውቋል። በደም እጥረት ምክንያት በቀጠሮ የሚሠሩ ቀዶ ጥገናዎችን ሰርዘው የነበሩ የህክምና ተቋማትም በቂ ደም ማግኘት በመጀመራቸው ያ ቋረጧቸውን አገልግሎቶች መልሰው መስጠት ጀምረዋል።
በንፁህ ውሃ አቅርቦት ችግር ዜጎቿ ለተለያዩ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከሚጋለጡ ሃገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት። ውሃ ለመቅዳት ለሰአታት በእግር ከመጓዝ ጀምሮ በንፁህ ውሃ እጦት ለበሽታ የሚዳረጉ ሰዎች ብዙ ናቸው። ሄርሜላ ወንድሙ በወጣትነት ዕድሜዋ ይህንን ተረድታ በመላው ኢትዮጵያ በዚህ ችግር የሚሰቃዩ ዜጎችን በንፁህ ውሃ ተደራሽ ለማድረግ 'ጠበታ ውሀ' የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት መስርታ፣ በአምስት የተለያዩ ክልሎች 70 የውሃ ጉድጓዶችን አስቆፍራለች።
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ያለበት የመጀመሪያው ሰው ከተገኘ በኃላ፣ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የተለያዩ ጥረቶችን እያደረገ ይገኛል። ከነዚህ ጥረቶች አንዱ በጤና ሙያ ተመርቀው ወደ ስራ ያልተሰማሩ ባለሙያዎችን በፈቃደኝነት ተመዝግበው አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ የጤና ባለሙያ እጥረትን መቅረፍ ነው።
ለረጅም አመታት ለፕሬስ ነፃነት ከሚያሰጉ አገሮች ትመደብ የነበረችው ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለት አመታት በመገናኛ ብዙሀን እንቅስቃሴ ዙሪያ በታዩ ለውጦች ምክንያት አለም አቀፍ አድናቆት ብታገኝም በኢትዮጵያ ያለው የፕሬስ ነፃነት አሁንም ከስጋት ነፃ አይደለም። የሚዲያ ፅንፈኝነት፣ የጋዜጠኞች የሙያ ብቃት እና በነፃነት ዙሪያ የታዩት መሻሻሎች ወደኃላ የመቀልበስ ስጋት አሁንም የሚዲያው ፈተናዎች ሆነው ቀጥለዋል።
ከኤርትራ ወጥተው ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞች ድንበር ላይ የሚመዘገቡበትን መስፈርት ኢትዮጵያ መቀየሯ በተለይ እድሜያቸው ለአቅም ያልደረሱ ህፃናትን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሲል የአለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይት ወች ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ለወራት የአለም ስጋት ሆኖ በቀጠለው የኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በኢትዮጵያም እያሻቀበ መሄዱን ተከትሎ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን፣ ግለሰቦች ሊያደርጏቸው ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች ከማስተማር ባለፈ ለወትሮው ማህበረሰቡ በአካል ተገኝቶ ይሳተፍባቸው የነበሩትን ማህበራዊና ሀይማኖታዊ ስነስርዓቶች ከቤታቸው ሳይወጡ ባሉበት እንዲከታተሉ አድርገዋል።
በኢትዮጵያ የአሶሼትድ ፕሬስ የፎቶ ባለሞያ የሆነው ኢትዮጵያዊው የፎቶ ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አየነ እጩ ከሆነባቸው ሦስት ዓለም አቀፍ ሽልማቶች ውስጥ በዋና ዜና ታሪክ ስብስብ አሸናፊ ሆነ። የፎቶ ባለሞያው ያሸነፈበት ስራው ቢሾፍቱ አቅራቢያ በወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ 8 አይሮፕላን አደጋ የሞቱ ቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ባለማግኘታቸው አውሮፕላኑ የወደቀበት ቦታ ሄደው ፊታቸው ላይ አፈር እየበተኑ ሲያለቅሱ በሚያሳይ አሳዘኝ ፎቶ ነው።
በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ትልቅ ስፍራ ከሚሰጣቸውና በነገው ዕለት የሚከበረው የፋሲካ በአል በኮሮናቫይረስ ምክንያት ድምቀቱ ቀንሷል። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚያዚያ 8 ባወጣው መግለጫ በቤተሰብ መካከል የሚካሄድ የአካል መጠያየቅ እንዳይኖር የቅድመ ጥንቃቄ መመሪያ አስተላልፏል። ከዛም በተጨማሪ የሀይማኖት ተቇማት ህብረተሰቡ ከበሽታው እንዲጠበቅ ምዕመናን ከቤታቸው ሆነው በዓሉን እንዲያከብሩ መመሪያዎችን አውጥተዋል።