የብሄር አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ ዓመታዊ ጉባዔ ነገ ከመስከረም 17 – 21 በባህር ዳር ያካሄዳል፡፡
በኢትዮጵያ በብሄርና ኅብረ ብሄር ፖለቲካ አደረጃጀት ላይ የባህር ዳርዋ ዘጋቢያችን አስቴር ምስጋናው ሁለት ምሁራንን አከራክራለች።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር፣ ከግንቦት 7 ጋር ገልፅነት በጎደለው የፋይናስ አሠራርና በአመራር ችግር ምክንያት ከመስከረም 13 ቀን ጀምሮ መለያየታቸውን ገለፀ።
በኢትዮጵያ ሱማሌ ክልል በተከሰተው ውከት ተፈናቅለው ወደ አማራ ክልል የሄዱ የክልሉ ተወላጆች በከፋ ችግር ላይ መሆናቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ገልፀዋል።
የአርበኞች ግንቦት7 ለፍትህና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ መሪ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ በባህርዳር ከተማ ባሰሙት ንግግር ንቅናቄው ወደ ሀገራዊ ፓርቲ ለመቀየር መወሰኑን አስታውቀዋል።
ላለፉት 8 ዓመታት በኤርትራ ሀሪና እየተባለ በሚጠራው የጦር ሰፈር ካንፕ ገንብቶ ለአማራ ህዝብ ነፃነት ሲታገል የነበረው የአማራ ዴምክራሲ ኃይል ንቅናቄ /አዴኃን/ ዛሬ በባህር ዳር በመገኘት ሰላማዊ ትግል ለማድረግ መወሰኑን ገልፆል።
እንዲህ አውደ ዓመት ሲመጣ ከወዳጅ ዘመድ ጋር በጋራ አብሮ በመብላት እና በመጠጣት በዓልን ማሳለፍ ለኢትዮጵያውያን የተለመደ ባህል ነው።
ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልልና ከኦሮምያ ክልል ተፈናቅለው ባህር ዳር ከተማ በጊዚያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ ያሉ ተፈናቃዮች በአስከፊ ችግር ላይ እንደሚገኙ ገለፁ።
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ያውጣውን መግለጫ ተከትሎ “መግለጫው የህዝቡን መሰረታዊ ጥያቄ ያነሳ አይደለም፣ ከዚህ በመነሳት አስራ ሁለተኛው መደበኛ ጉባዔ እንዴት እንደሚሆን ማወቅ ይቻላል” ያሉ ወገኖች ድምፃቸውን እያሰሙ ነው።
የማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን አቀንቃኞች ምክንያታዊ አስተሳሰብ ለመገንባት በስሜት ሳይሆን በዕውቀት የሚመራ ትውልድ ሊፈጥሩ ይገባል ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ተናገሩ።
ከሃያ ሁለት ዓመታት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው አርቲስትና የሰብዓዊ መብት አራማጅ ታማኝ በየነ ኢዮጵያዊነትን በጋራ ማጠናከር የሚጠይቅ ንግግር አድርጓል።
ብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ብአዴን/ 12ኛ መደበኛ ጉባዔውን በቅርቡ ያካሂዳል።
በውጭም ሆነ ሀገር ውስጥ ያሉ የአማራ ክልል ተወላጅ ምሁራን አሁን የተገኘውን ለውጥ ለማስቀጠል ያስችላል የተባለ የምክክር ጉባዔ ጉባዔ 105 አባላትን እና 15 የቦርድ ሰብሳቢዎችን አፅድቆ ተጠናቅቋል።
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሣ አሁን ባላቸው ወቅታዊ አቋም የአማራን ህዝብ ጥቅም እንደማያስጠብቁ በመረጋገጡና በጥረት ኮርፖሬት ላይ በሰሩት ጥፋት እስከ ሚቀጥለው የድርጅቱ መደበኛ ጉባኤ ድረስ ከብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት አግዷቸዋል፡፡
ነፃነት ሥርዓተ አልበኝነትን፣ ሥርዓት አልበኝነት ደግሞ አምባገነንነትን ሊየመጣ እንደሚችል ሕብረተሰቡ እየተገነዘበ በመምጣቱ፣ የሕግ የበላይነት ይከበር ጥያቄ እያነሳ ነው ሲሉ የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ንግሡ ጥላሁን ገለፁ፡፡
በኢትዮጵያ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ሀገሪቱ ብዙ ለውጦችን በማስተናገድ ላይ ትገኛለች።
ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ ቁጥራቸው 125 የሚሆኑ ወሰን ተሻጋሪ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰጭ ወጣቶች በባህር ዳር ከተማ ዙሪያ ልዩ ስሙ ሰባት አሚት በተባለ አካባቢ በአባይ ወንዝ ላይ የእምቦጭ አረምን የማስወገድ ሥራ ሰርተዋል፡፡