የሐረር ከተማ የውኃ ችግር በከፊል እየተቃለለ መሆኑ እየተሰማ ነው።
የሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን አራት ነዋሪዎች መገደላቸውንና ሁለት ሰዎች ታፍነው መወሰዳቸውን ገለፀ፡፡
በአፋር ክልል ልዩ ኃይሎች የሚደርሰውን ጥቃት ለመቃወምና ሦስቱ አወዛጋቢ ቀበሌዎች ወደ ሶማሌ ክልል እንዲካለሉ ለመጠየቅ የኢሳ ሶማሌዎች በትላንትናው ዕለት ከድሬዳዋ ደወሌ የሚወስደውን መስመር ዘግተውት ነበር፡፡
በሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን ነዋሪዎች፣ በየዞኑ ዋና ከተማ ሺኒሌ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ።
በአፋር ክልል ከትላንት 4 ሠዓት ጀምሮ የነበረው የመንገድ መዝጋት አድማ ማምሻውን እንደተጠናቀቀና መንገዶች እንደተከፈቱ ተገለፀ፡፡
ሲያካሂዱ የነበረውን የትጥቅ ትግል በመተው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የወሰኑትና ወደ ሃገር የገቡት የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦብነግ) እና የሶማሌ ክልል ዴሞክራሲያዊ ትብብር (ሰርዳ) መሪዎች ድሬዳዋ ላይ አቀባበል እንደተደረገላቸው ዘግበናል።
በሐረሪ ክልል የሚገኙ የኮንዶሚኒዬም ቤት ባለቤቶች፤ ቤቶቻቸው እየተሰበሩ ባልታወቁ ሰዎች መወሰዳቸውን ተናገሩ። ቅድሚያ ገንዘብ ከፍለው ቁልፋቸውን የተረከቧቸውንና የውስጥ ግንባታ እያከናወኑ ያሉባቸው ቤቶች እየተሰበሩ የማያውቋቸው ሰዎች መኖሪያ መሆኑን በመግለፅ አቤቱታ እያሰሙ ነው። የክልሉ ቤቶች ልማት ቢሮ በበኩሉ ለደንበኞቹ ያስተላለፋቸው ቤቶችና ለመምሕራን እየተገነቡ ያሉም ቤቶች ተወስደዋል ብሏል።