ሰኔ 15 ቀን በባህርዳርና በአዲስ አበባ የተፈፀሙት ግድያዎች ግንኙነት እንዳላቸው ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ተናግረዋል፡፡
ለውጡን የሚመራው ስብስብ በሰብዓዊ መብት ላይ ያልው አቋም አልተቀየረም ሲሉ ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ገዥ የሆነው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ዴኢህዴን/ ጉባዔውን ዛሬ አጠናቋል፡፡
ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ሁለት መቶ ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የዓለም ክብረ-ወሰን ሰብረዋል።
አሁን ያለው ህገ መንግሥት ለኢትዮጵያ አንድነት ዋስትና የሚሰጥ አይደለም ሲሉ አንድ የቀድሞ የተቃዋሚ መሪና የፓርላማ አባል ተናገሩ፡፡ ህገ መንግሥቱ ለፌዴራሊዝም ሳይሆን ለኮንፌዴሬሽን ወይም ለመነጣጠል የሚሆን ነው ሲሉ ነው የተቃዋሚው መሪው አቶ ልደቱ አያሌው ለአሜሪካ ድምፅ የገለፁት፡፡
የደቡብ ክልሉን ቀጣይ አከላለልና ዕጣ ፈንታ በተመለከተ የተለያዩ አማራጮች የቀረበበት ጥናት ውጤት ዛሬ በምሁራን ውይይት ተደርጎበታል።
በደቡብ ክልል ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የተሻለው አማራጭ አሁን ባለው አንድነት መቀጠል መሆኑን ለአለፉት ሰባት ወራት ጥናት ያካሄደው ገለልተኛ ቡድን አጥኝ አስታወቀ።
ሱዳንን እየመሩ ያሉት የጦር አዛዦችና ተቃዋሚዎቹ፣ ዛሬ የሰላም ሥምምነት ተፈራረመዋል፡፡
“ኢትዮጵያ ውስጥ ጥላቻና ብጥብጥ ከሚቀሰቅሱ የዳያስፖራ አባላት የተወሰኑት ዩናየትድ ስቴትስ የሚገኙ ናቸው” ሲሉ አዲስ አበባ የሚገኙት የአሜሪካ አምባሳደር ተናግረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የትናንትና ማብራሪያ ዋንኛ ነጥብ መንግሥታቸው ህጋዊ ባልሆነ አካሄዶች ላይ ጠበቅ ያለ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምር መጠቆማቸው ነው ይላሉ አንድ አንጋፋ የተቃዋሚ መሪ፡፡
“ተቀምጠው የሰቀሉትን ቆሞ ማውረድ የሚቸግርበት ጊዜ እንዳይመጣ ሁሉም ሊጠነቀቅ ይገባል” ሲሉ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በሰሞኑ የሃገሪቱ ሁኔታ ላይ ዛሬ ለፓርለማው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት አሳሰቡ።
ሰሞኑን በጠባቂያቸው የተገደሉት የጦር ኃይሎች ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን እና ጡረተኛው ጄነራል ገዛዒ አበራ አስከሬን ዛሬ በሚሊኒዬም አዳራሽ ሽኝት ተደርጎለታል፡፡
በአማራ ክልል አመራር አባላትና በኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም ላይ የተፈፀመው ግድያ “ተገለገሏት ኢትዮጵያና በተቋማቱ ላይ እንደተፈፀመ የሚቆጠር ነው” ሲል በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
የዛሬዋ ኢትዮጵያ፣ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበረችው የበለጠ ተስፋ ያላት ነች ሲሉ፣ ተሰናባቹ የአሜሪካ ኤምበሲ ቃል-አቀባይ ኒኮላስ ባርኔት ተናገሩ።
የሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤትና ተቃዋሚዎቹ ተቋርጦ የነበረውን ውይይት ለማስቀጠል በሚያስችሉ አምስት ነጥቦች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገልጿል። ወገኖቹ ለመነጋገር የተስማሙት የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የጀመሩትን የማግባባት ሙከራ ተከትሎ መሆኑ ተነግሯል። የስምምነቱን ጉዳይ ይፋ ያደረጉት በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደርና የሱዳን ዕርቅ ጉዳይ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር መሃመድ ድሪር ናቸው።
ዛሬ ካርቱም የገቡት የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከሱዳን ወታደራዊ የሽግግር ሸንጎ መሪ ሌተናል ጄኔራል አብዱልፋታህ አልቡራህን ጋር ተወያይተዋል፡፡ በካርቱም ለውጥ ከመጣበት ከሁለት ወራት በፊት አንስቶ ኢትዮጵያና ሱዳን እየተመካከሩ ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከአሥር ቀናት በፊት ከአሜሪካን ድምፅ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረው ነበር፡፡ የዛሬ ጉዟቸውም የዚያ ምክክር ሂደት አካል በዚያ ቃለ መጠይቅ ያስረዱት፡፡
ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ከቪኦኤ ጋር በተለይ ያደረጉት ቃለ-ምልልስ የመጨረሻ ክፍል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ሥልጣን ከያዙ አንስቶ የመጀመሪያቸው የሆነው በተለይ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ ከቪኦኤ ጋር በተለይ ያደረጉት ቃለ-ምልልስ የመጀመሪያ ክፍል።
የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት “ልንወረወርበት ከነበረው አዘቅት የማገገም ሁኔታ አሣይቷል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከአሜሪካ ድምፅ ጋር በተለይ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ተናገሩ።
ተጨማሪ ይጫኑ