በኢትዮጵያ መንግሥት ይፈፀማሉ የሚባሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ለማጣራትና ለመፈተሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ኮሚሽን በኢትዮጵያ የምርመራ ቢሮ ሊከፍት እንደሚችል ከእስር ከተፈቱት ጋራ በነበራቸው ውይይት መነሳቱን ከተወያዮቹ መካከል ጥቂቶቹ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረውን አሕመዲን ጀበልና የኢንተርኔት አምደኛው በፍቃዱ ኃይሉ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ሰጥተዋል።
በእስር ላይ የሚገኙት የቀድሞ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ በአስቸኳይ ፍትሕ እንዲያገኙ ባለቤታቸው ወ/ሮ መቅደስ ለማ ጠየቁ።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በኦሮሞ እና በጌዲኦ ተወላጆች መካከል በተፈጠረ ግጭት ከሁለቱም ወገን ብዙ ሰዎች መሞታቸውንና በሺዎች የሚቆጠሩ ከቀያቸው ተፈናቅለው በችግር ላይ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ገለፁ።
ጥያቄያቸው የማንነት እንጂ የልማት እንዳልሆነ በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የወልቃይት ኮሚቴ አመራር አባላት አቶ አታላይ ዛፌ ለአሜሪካ ድምፅ ገለጹ።
በኢትዮጵያ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይና በኮንሶ የታሰሩ እስረኞችን በተመለከተ የተጠናቀረ ዘገባ።
ወደ አምቦ ተጉዘው በስተዲየም ለተሰባሰው የከተማው ነዋሪ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የትናንቱን ቁርሾና ጠባሳን በመተው ጠንካራ የአንድነት ማዕቀፍ እንዲገነባ ጠይቀዋል።
በዛሬው ዕለት ወደ አምቦ ከተማ ተጉዘው በስተዲየም ለተሰባሰው የከተማው ነዋሪ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የትናንቱን ቁርሾና ጠባሳን በመተው ጠንካራ የአንድነት ማዕቀፍ እንዲገነባ ጠይቀዋል።
በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በቆቦ ከተማ ትናንት ለሊት በጥይት ተመታ ተገድላ የተገኘችው የስድስት ወደ ነፍሰጡርና የአንድ ልጅ እናት አያንቱ መሐመድ አሟሟት አነጋጋሪ ሆኗል።
ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው በሐማሬሳ መጠለያ የሚገኙ ተፈናቃዮች በተፈናቀሉበት ወቅት የተገደሉ ሰዎች ገዳዮች ለፍርድ ሳይቀርቡ፣ ጥለውት የወጡት ንብረት እስካሁን የታሰሩ ሰዎችን በተመለከተ እጅግ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል። አያይዘውም ከተፈናቀሉ ጀምሮ በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ገልፀው ቀጣይ ሁኔታቸውን አለማወቃቸውም እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ የሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት እንደተፈቱ በሚነገርበት ወቅት እስር ቤት ውስጥ በፀሎት ላይ እንደነበሩ ለጠያቂዎቻቸው መናገራቸውን ከጠያቂዎቹ መካከል ገልፀውልናል።
የፌደራል የወንጀል መመርመሪያ ማዕከል ወይም በተለምዶ “ማዕከላዊ” እስር ቤት ዛሬ መዘጋቱን የሀገር ውስጥ የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። በዚህ እስር ቤት ውስጥ ከዚህ ቀደም ታስረው የተለያየ የማሰቃየት ተግባራት እንደተፈፀመባቸው የሚናገሩ እስረኞች ግን “ማዕከላዊን መዝጋት ሳይሆን የማሰቃየት ተግባሩን ማቆም የበለጠ ጥቅም ይሰጣል” ይላሉ። “በእስር ቤት የተሰቃዩ ሰዎችን ወደ ሌላ ቦታ እያዛወሩ እስር ቤቱን መዝጋት ምንም ለውጥ የለውም “ ብለዋል።
ካለፈው ዕሁድ ጀምሮ በዳግም እስር ላይ ይገኙ የነበሩት ጋዜጠኞች፣ፖለቲከኞችና የኢንተርኔት ላይ አምደኞች ከእስር ተለቀቁ። ከእስር ከተለቀቁት መካከል ሁለት ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋና ተመስገን ደሳለኝን በተጨማሪም የቀድሞው የአንድነት አመራር አባል አቶ አንዷለም አራጌን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
በቅርቡ ከእስር የተፈቱት አቶ በቀለ ገርባ በእስር ቤት እያሉ ከአቶ አንዷለም አራጌ ጋራ የጀመሩትን አንድ የማርቲን ሉተር ኪንግ መጽሐፍ በኦሮመኛና በአማርኛ ቋንቋ ጽፈው አንዱን አሳትመዋል። ሌላኛው ደግሞ ሕትመት በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። መጽሐፉ እስር ቤት ውስጥ ስለ ተተረጎመበት ሁኔታና ስለመጽሐፉ አስተያየት ሰጥተዋል።
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በፓርላማ ሲሰየሙ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ሕወታቸው ለተቀጠፈ ሰዎች መፀፀታቸውን ገልፀው ይቅርታ ጠይቀዋል። በቅርቡ ልጆቻቸው ከተገደሉባቸው መካከልይቅርታ ብቻውን ለደማ ልብ መጠገኛ ሊሆን አይችልም ይቅርታው ተቀባይነት የሚኖረው ድርጊቱን የፈፀሙ ሰዎች ለፍርድ ሲቀርቡ ነው ብለዋል።
ፓርቲያቸውና የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ መድረክ ለረጅም ዓመታት የሚወቀስበትንና እየተወቀሰ የሚገኝበትን የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለማሻሻል፣ እስረኞችን ለመፍታትና በእስር ቤቶች ውስጥ ይፈፀማሉ የሚባሉትን የማሰቃየት ተግባራት የማስቆም እርምጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ መውሰድ ይችላሉ? ጽዮን ግርማ በኢትዮጵያ የሚገኙ አራት ጠበቆችን አነጋግራ ያሰናዳችውን ዘገባ ያድምጡ።
ከዕሁድ መጋቢት 16/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ በንፋስ ስልክ ፖሊስ መምሪያ በቁጥጥር ሥር በእስር የሚገኙት ዐሥራ አንድ ጋዜጠኞች፣ የኢንተርኔት አምደኞችና የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ዐርባ አንድ ዓለም አቀፍና አሕጉር አቀፍ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጠየቁ። ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ ሆስፒታል ገብቶ እንደነበረም ቤተሰቦቹ ገልፀዋል።
የሰብዓዊ መብቶችና የፕሬስ ነፃነት ተሟጋች ድርጅቶች ግንባር ገጥመው ወይም ኃይሎቻቸውን አስተባብረው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እያደረጉ ያሉት ነገር ጨርሶ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንዲገነዘቡት ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ድምፆቻቸውን ማሰማት እንዳለባቸው ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች ደህንነት ተሟጋች ቡድን (ሲፒጄ) አሳሰበ።
በባሕርዳር ከተማ ውስጥ በአንድ ላይ የነበሩ የዩኒቨርስቲ ምሑራን፣ የመንግሥትና የግል ጋዜጠኞችና ሌሎች ባለሞያዎች በአጠቃላይ 19 ሰዎች ቅዳሜ መጋቢት 15/2010 ዓ/ም መታሰራቸውን ያነጋገርናቸው ሰዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ከእስር የተለቀቁ ሰዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመልሰው መታሰር በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት የሥርዓት ለውጥ መሆኑን ማሳያ ነው ሲል ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ከአዲስ አበባ ውጪ ባሉ ከተሞች በተለይ ደግሞ በአሮሚያና በአማራ የተለያዩ ከተሞች የስልክ ኢንተርኔት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ከተቋረጠ ወራት መቆጠሩን ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።
ተጨማሪ ይጫኑ