ዋሽንግተን ዲሲ —
የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እያለ ስማርት ሀውስ ወይም የውጪውን ሁኔታ በማስተዋል እራሱን የሚቆጣጠር ቤትና የስልክ አጠቃቀምን የሚያቀል መተግበሪያ በመሥራት ሃገር አቀፍ ሽልማቶችን ያገኘው ወጣት ናትናኤል ታምሩ ከአራት ወር በፊት የፕሮግራማችን እንግዳ ነበር።
በዚህ የፈጠራ ሥራውና የትምህርት ብቃቱ ካሊፎርኒያ የሚገኘው ሚነርቫ ዩንቨርስቲ ነፃ የትምህርት ዕድል ቢሰጠውም ለጉዞ የሚያፈልጉትን ወጪዎች ለመሸፈን አለመቻሉን ነግሮን የነበረው ናትናኤል በፕሮግራማችን ላይ ከቀረበ በኃላ በተደረገለት ድጋፍ ወደ ሳንፍራንሲስኮ ከተማ አቅንቶ በሰው ሰራሽ ልህቀት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) የመጀመሪያ አመት ትምህርቱን መከታተል ጀምሯል።
(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)