በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ረሃብ በአፍሪካ

በቦረና እና ጉጂ በድርቅ የተነሣ ሰው እንደ በሬ ተጠምዶ እያረሰ መኾኑን አርሶ አደሮች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00

ከአምስት ተከታታይ የዝናም ወቅቶች መታጎል በኋላ፣ በደቡብ ኦሮሚያ ዝናም ቢዘንምም፣ አሁንም አርሶ አደሮቹ፥ በዘር፣ በማዳበርያ እና በማረሻ በሬ ማጣት ችግር ላይ እንደ ኾኑ ተናግረዋል።

ዘር እና ማዳበሪያ፣ የምናርስበት በሬ የለንም፤ በፈንታው፣ ሰውን እንደ በሬ ጠምደን እያረስን ነው፤" የቦረና እና ጉጂ አርሶ አደሮች

በቦረና ዞን አንድ የድሬ ወረዳ አርሶ አደር፣ ያለፈው ድርቅ በርካታ የቁም ከብቶችን ስለ ፈጀ፣ አሁን ነዋሪው የሚያርስበት ከብት አጥቶ፣ ሰውን ልክ እንደ በሬ በመጥመድ የተገኘውን የእህል ዘር ለመዝራት እየሞከሩ መኾናቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

በጉጂም በተመሳሳይ፣ የዘር እና የማዳበሪያ አለመኖር ብቻ ሳይኾን፣ በአካባቢው ያለው የጸጥታ ዕጦት፣ የአርሶ አደሮቹን ችግር ማባባሱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ፣ አርሶ አደሮቹ፣ የእርሻ ግብአቶቹን እንዲያገኙ እየሠራኹ ነው፤ ይላል።

 በደቡብ ኢትዮጵያ በጠናው ድርቅ የእንስሳት ሞት እና የሰዎች ጤና ከፍቷል
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:16 0:00

ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ዝናም አለመዝነቡን ተከትሎ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ፣ የእንስሳት ሞት እንደ ቀጠለ ነው፡፡

የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ረኀብ፣ አስከፊ የጤና ችግር ያስከተለባቸው፣ ከመቶ በላይ ሕፃናት፣ አረጋውያንና ነፍሰ ጡሮች እንዳሉ አስታውቀዋል፡፡

ዘገባው የሮይተርስ ነው፤ ኤደን ገረመው ወደ ዐማርኛ መልሳዋለች።

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG