በአለማችን በሚልየን የሚቆጠሩ ላጤዎች የኢንተርኔት ድረገፅን ለፍቅረኛ መፈለጊያነት ይጠቀማሉ። በዛሬው በፍቅር ቀን ልባቸውን ለፍቅር በከፈቱ ጓደኛ ፈላጊዎች ላይ የደረሰ የገንዘብ መታለል እርስዎ ላይ እንዳይደገም ለጥንቃቄ ይሆንዎ ዘንድ አንድ ታሪክ እናካፍላችሁ።
ከአንድ ሚልየን በላይ የሚሆኑ በዩናይትድ ስቴትስ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ከተለያዩ ሃገራት የመጡ አለም አቀፍ ተማሪዎች የገንዘብ ብድር የማግኘት ፈቃድ በሲልከን ቫሊ ድርጅት አማካኝነት አገኙ።
"ዩናይትድ ስቴትስ ለስደተኞች ከለላን በመስጠትዋ የምትኮራ ሃገር ናት፤ ስደተኛ ማስተናገዱንም እንቀጥላለን፣ ይህን ስናደርግ ግን ድንበሮቻችንንና ዜጎቻችንን ከአደጋ መከላከልን ቅድሚያ በመስጠት ነው።" ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ
ፀጉርን ቀስ በቀስ የሚያሸብቱ ዋነኛ ምክንያቶች የአካባቢ የአየር ሁኔታና እድሜ ናቸው። ተመራማሪዎቹ እንደሚሉት በምህፃረ ቃል አይ አር ኤፍ ፎር (IRF4) በመባል የሚታወቀው ዘረመል ወይም በእንጊሊዘኛው አጠራር ጂን ፀጉርን እንዴት ሊያሸብት እንደሚችል ከታወቀ ሽበት ደህና ሰንብት የሚባልበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም።
በዚህ ሳምንት ለ89 ኛው የአካዳሚ አዋርድ ከሩት ነጋ ጋር ለእጩነት ከቀረቡት ምርጥ የሆሊዉድ ተዋናዮች ውስጥ ኤዛቤል ሁፐርት፣ ናታሊ ፖርትማን፣ ኤማ ስቶን እና አንጋፋዋ ሜሪይል ስትሪፕ ይገኙበታል። ኢትዮጵያዊ አይሪሿ ሩት ነጋ በቅርቡ ለእይታ የቀረበው ላቪንግ በተሰኘው ልብወለድ ፊልም ባሳየቸው የተወና ብቃት ነው የተመረጠችው።
ከሊቢያ ወደ ጣሊያን ከ170 በላይ የሚሆኑ ስደተኞችን ከአቅሙ በላይ የጫነ ጀልባ ቅዳሜ ለሊት በሚዲትራኒያን ባህር ሰምጦ አራት ስደተኞች ብቻ ሲተርፉ ሌሎቹ ህይወታቸውን ማጣታቸውን አንድ የስደተኞች መርጃ ድርጅት አስታወቀ። ከተረፉት ስደተኞች ሁለቱ ኤርትራዊ ሁለቱ ደግሞ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ አንዷ እርጉዝ ሴት እንደሆነች አጀንሲያ አበሻ የተባለው ስደተኞችን የሚረዳው ቡድን መሪ አባ ሙሴ ዘርዓይ፤ የጣሊያን ባህር ሃይልን ጠቅሰው ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል።
ነገ በዋሽንግተን ዲሲ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ለተመራጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን ያስረክባሉ። ከነገ ጀምሮ የዩናይትድ ስቴትስ 45ኛ ፕሬዚዳንት የሚሆኑት የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች በስነስርዓቱ ላይ ለመገኘት ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ቁጥራቸው የበዛ የትራምፕ ተቃዋሚዎችም የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ናቸው።
መሪጌታ ብሩክ አስማረ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ናቸው። የዘንድሮው የጥምቀት ዋዜማ የከተራ በዓል በባህርዳር እንዴት እየተከበረ እንደሚገኝ አጫውተውናል።
ዛሬ በመላው ዩናይትድ ስቴትስ የጥቁር ህዝብ መብት ተሟጋቹ የዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ 88ኛ የልደት በዓል በመከበር ላይ ይገኛል።
በዩኔስኮ የታሪክ መዝገብ ላይ የሰፈረው የሜክሲኮው ማሪያቺ የሙዚቃ ስልት በአውሮፓ በተለይም በዩናይትድ ስቴትስ ተወዳጅነቱ እየጨመረ መጥቷል። ሙሉ ዘገባውን ከበታች ያለውን ተንቀሳቃሽ ምስል በመጫን ይመልከቱ።
የዛሬ ሰባት አመት በስደት ወደ ደቡብ አፍሪካ ከተጓዙት ኤርትራውያን ወጣቶች መካከል ሜሮን ሰመዳር አንዱ ነው። አሁን ኑሮው በዩናይትድ ስቴትስ ቢሆንም ስደተኛን በተመለከተ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል።
አለም አቀፉ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ አይ ኦ ኤም (IOM) ባሳለፍነው የአውሮፕያውያኑ 2016 ዓ.ም በስደት ጉዞ ላይ የሞቱት ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የሚገልፅ ዘገባ ይፋ አደረገ።
በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት የሚኖሩ ሰዎች አስተማማኝ የሆነ የኤሌክትሪክ ሃይል ባለማግኘታቸው ሲቸገሩ ይታያሉ። የኤሌክትሪክ መስመር በደጃቸው ያላለፈ ገጠራማ ቦታዎችም በርካታ ናቸው። ባለፉት አምስት አመታት የኤሌክትሪክን ሃይል ለሁሉም ማዳረስ የሚቻልበትን መንገድ ሲያጠኑ የቆዩ ባለሙያዎች አዲስ ሃሳብ አፍልቀዋል። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስትም በሚልዮኖች የሚቆጠር ዶላር ይህንን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ መድቧል።
የዘንድሮው ዓመታዊ የአለም አቀፍ የስነህዝብ ጥናት ዘገባ በጆርዳን ዋና ከተማ በአማን ተካሂዶ ነበር። ዘገባው የአስር አመት ዕድሜ ክልል ላይ የሚገኙ አዳጊ ሴቶችን የወደፊት የህይወት እጣ ለመመርመር ሞክሯል። እንደዘገባው አብዛኛዎቹ ልጃገረዶች በማደግ ላይ በሚገኙ ሃገሮች ውስጥ የሚኖሩ ሲሆን መሰረታዊ ትምህርትና ህክምና ባልተሟላበት፤ ደህንነታቸውም አስጊ በሆነበት ቦታ ነው የሚያድጉት። የፆታ እኩልነትነት አመለካከትብ ለመቀየር የበለጠ መሰራት እንዳለበት ተገልጿል።
‘ልረሳሽ አልቻልኩም’ በተባለችው ነጠላ ዜማ በበርካታ የሙዚቃ አድናቂያን ልብ ውስጥ የቀረው ኤርሚያስ አስፋው ሰኞ እለት ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል። ለሙሉ ዘገባው ከበታች ያለውን ተንቀሳቃሽ ምስል ይጫኑ።
በዩናይትድ ስቴትስ የሕክምና ትምህርታቸውን ለመቀጠል የሚፈልጉ ከተለያዩ አገሮች የሚመጡ የሕክምና ትምሕርት ያጠኑ ባለሞያዎች ከፍ ላለ ፈተና ይጋለጣሉ። በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ አብዛኛዎቹ በሕዝብ ገንዘብ የሚረዱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አይቀበሏቸውም። የግል ዩኒቨርስቲዎች ደግሞ በጣም ውሱን የሆነ ቦታና ፉክክሩም ከፍተኛ ነው። ይሁን እንጂ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ መጥተው የሕክምና ትምህርታቸውን መከታተል አይችሉም ማለት አይደለም።
በአዲሱ የጤና ምርምር መሰረት በብዛትም ሆነ በትንሹ ማጨስ የሚያመጣው የጤና እክል ተመሳሳይ ሆኗል። በቀን አንድም ሲጃራ ማጨስ ቢሆን የህይወት ዘመንን ያሳጥራል ነው የሚለው በቅርቡ የተደረገው ጥናት ውጤት። ማጨስን በማቆም ግን እድሜን ማራዘም ይቻላል።
ጣልያናዊቷን ኤማ ሞራኖ ን እናስተዋውቃችሁ። የአንድ መቶ አስራሰባት አመት የእድሜ ባለፀጋ ናቸው። በአስራዘጠነኛው ክፍለዘመን እ.አ.አ በህዳር 27 ቀን 1899 ዓ.ም ነበር የተወለዱት። የእኚህ አዛውንት እድሜ በአለማችን በአስራዘጠነኛው ክፍለዘመን ከተወለዱትና ረጅም እድሜ ከኖሩት ሁሉ ቀዳሚ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።
እየሩሳሌም በሚገኘው ታሪካዊ ሙዝየም ለዕይታ ከተቀመጡት እድሜ ጠገብ ቁሳቁሶች ጀርባ አንድ የእስራኤል የቀድሞ ወታደር በባህላዊ የንቅሳት ምስሎች ሰውነቱን እያስዋበ ነው። በሙዝየሙ ውስጥ የንቅሳት ጥበብን ለማሳየት ብቻ የተዘጋጀ አይደለም። ይህ በሰውነት ላይ የሚከተበው የንቅሳት ጥበብ በውትድርና ሜዳ ለነበሩና ጦርነቱ በሰውነታቸው ላይ ጥሎ ያለፈውን ጠባሳ ለመሸፈን በሚል አላማ የተጀመረ ነው።
እ.አ.አ በ2020 ቫይረሱን ከአለማችን ጨርሶ የማጥፋት አለም አቀፍ እቅድ በኢትዮጵያ ምን ያህል እንደተተገበረ በመገምገምና ለቀጣይ አመታትም ምን ላይ ትኩረት በመስጠት መሰራት እንዳለበት በመመካከር ነበር ቀኑ ታስቦ የዋለው።
ተጨማሪ ይጫኑ