ኢትዮጵያ ውስጥ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የፖለቲካ አለመረጋጋትና፣ የሰላም እጦት፣ በሰው ህይወትና በንብረት ላይ እያደረሰ ካለው ቀላል የማይባል ጥፋት ባለፈ በህብረተሰቡ ውሰጥ ጥሎት የሚያልፈው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና የስነ-ልቦና ቀውስ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የኢኮኖሚና ማህበራዊ ኑሮ ተንታኞች ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ለሁለት ሳምንት ሙሉ ለሙሉ የተቋረጠው የኢንተርኔት አገርልግሎት ሀገሪቱን በቀን ከ 4 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንደሚያሳጣት 'ኔት ብሎክስ' የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት አስታውቋል። መንግስት አገልግሎቱን ያቋረጠው ሁከትና ብጥብጥ እንዳይባባስ፣ ብሎም የሰዎችን ሕይወትና ንብረት ከጥቃት ለመጠበቅ መሆኑን ቢገልፅም፣ መንግስትን ጨምሮ በኢንተርኔት ግንኙነት ላይ ጥገኛ ሆነው የሚሰሩ የንግድ ተቋማት ለከፍተኛ ክስረት መዳረጋቸውን አስረድተዋል።
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ሰዎች በግል የሚጠቀሟቸው ግብዓቶች የአካባቢ አየር ብክለት እያስከተሉ እንደሆነ የአየር ንብረት ለውጥ ተሟጋቾች እየገለፁ ነው። ይህ ስጋት ያሳሰባቸው በእንግሊዝ አገር የሚገኙ ካምፓኒዎች ከፕላስቲክ ነፃ የሆኑና በቀላሉ የሚበሰብሱ፣ ነገር ግን ከአንዴ በላይ ጥቅም ላይ የሚውሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን ማምረት ጀምረዋል። የቪኦኤዋ ዘጋቢያችን ማሪያማ ዲያሎ ያጠናቀረችውን ሪፖርት ስመኝሽ የቆየ እንደሚከተለው ታቀርበዋለች።
በዓለም ዙሪያ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ህይወት የቀጠፈው የኮሮና ቫይረስ በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ ተጨማሪ ስጋቶች ማስከተሉን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል። በወረርሽኙ ምክንያት ለእናቶችና ህፃናት የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች ሀያ በመቶ በመቀነሳቸው፣ የእናቶች፣ አዲስ የሚወለዱ አና ታዳጊ ህፃናት ሞት ቁጥር መጨመሩም ተነግሯል። ዘገባው የካሮል ፒርሰን ነው፣ ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።
ከቅርብ ወራት ወዲህ ሊባኖስ በተለያየ ቀውስ ውስጥ ትገኛለች። ህዝባዊ አመፆች፣ የኢኮኖሚ ቀውስና አሁን ደግሞ በኮሮና ምክንያት የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ አገሪቱን አስጊ ሁኔታ ውስጥ ከቷቷል። በዚህም ምክንያት ከተለያየ የዓለም ክፍል የመጡ በመቶዎችና በሺዎች የሚቆጠሩ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ ስደተኞች ችግር ላይ ወድቀዋል፣ በሊባኖስ ጎዳና ላይ የሚወድቁትም ስደተኞች ቁጥር ቀን በቀን እየጨመረ ነው። ጃኮብ ራስል ከቤሩት የላከውን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ አጠናቅራዋለች።
ባለፈው ግንቦት ወር ላይ በሚኒያፖሊስ ግዛት በፖሊስ እጅ ውስጥ እንዳለ የተገደለው የጆርጅ ፍሎይድ ሞት ለዘመናት በኖረው ዘረኝነት ዙሪያ የሚደረጉ ውይይቶችንና ዘረኝነትን ለመዋጋት የሚደረጉ ጥረቶችን እንደአዲስ ቀስቅሷል። አንዳንድ ባለሙያዎች ደግሞ ዘረኝነትን ለማስቆም ብቸኛው መንገድ ትምህርት ነው ይላሉ። በዚህ ዙሪያ ማክሲም ማስካሎቭ ያጠናቀረውን ሪፖርት ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።
የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ከጤና ባሻገር የተለያዩ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ደህንነት ላይ ጫና እያሳደረ መሆኑን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በወረርሽኙ ምክንያት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ መግባቻቸውንና ከመንግስትና ሌሎች ረጂ ድርጅቶች ፈጣን ርዳታ የማያገኙ ከሆነ የተቋማቱ ህልውና ስጋት ላይ እንደሚወድቅ አስታውቀዋል። በዚህም ምክንያት ተቋማቱ ጥምረት ፈጥረው ኢንዱስትሪውን የማዳን ጥያቄ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮና ለሚመለከተው አካል አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ ህክምና ተቋማት በቂ ራስን ከኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶች ባለመኖሩና በአጠቃቀም ጉድለት የጤና ተቇማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ለቫይረሱ ተጋላጭነት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን ቪኦኤ ያነጋገራቸው የህክምና ባለሙያዎች ገልፀዋል። የኢትዮጵያ የመድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በበኩሉ የህክምና ባለሙያዎችን ከወረርሽኙ ለመክላከል የሚያስፈልጉ የህክምና ግብአቶች እጥረት መኖሩን ገልፆ፣ በሚቀጥሉት አንድ ወራት ችግሩን ለመቅረፍ እየሰራን ነው ብሏል።
የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት በሀገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ያቇረጠውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲመልስ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ጥያቄ አቅበዋል። መንግስት በበኩሉ፣ አገልግሎቱን ያቋረጠው የጥላቻ፣ የሁከትና የግድያ ቅስቀሳ መጠቀሚያ ስለሆነ ነው ብሏል።በአሁኑ ጊዜ በድህረ-ገፆች የሚወጡ መረጃዎች ምን ይመስላሉ፣ ድህረ-ገፆች ላልተገባ ጥቅም በሚውሉበት ጊዜስ መንግስታት ምን አይነት እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል?ተከታዩ ዘገባ ይዳስሰዋል።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መዛመትን ተከትሎ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶች ማሻቀብ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። በቤት ውስጥ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶች መባባስ እንዳለ ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ ከኖሩት ጎጂ ባህላዊ ልማዶች መሃል የሆኑት ጠለፋና በለጋ እድሜ የሚፈፀሙ ጋብቻዎችም በደቡብ ክልል በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመሩ መሆናቸውን የክልሉ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ አልማዝ ከፍታው ገልፀዋል።
በአንድ አገር ውስጥ በየትኛውም መልክ ከሚፈፀም የሰብዓዊ መብት ጥሰት መከላከል የመንግስት ኃላፊነት መሆኑን የሂውማን ራይትስ ወች የአፍሪካ ቀንድ ዳይሬክተር ላቲሺያ ባይደር ተናገሩ። የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ ኦሮሚያ ውስጥ ኦሮሞ ባልሆኑ ግለሰቦች ላይ ደርሰዋል የተባሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና ጥቃቶች እያጣሩ መሆናቸውንም ገልፀዋል። የኢንተርኔት መዘጋት ሥራቸውን አስቸጋሪ እንዳደረገባቸውም ተናግረዋል።
ህፃናት በስነ-ምግባር ታንፀው አድገው ነገ በሀገራዊና በራሳቸው ጉዳይ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ከትምህርት ቤት በቀጥታ ከሚቀስሙት ትምህርት ባሻገር፣ ከመፃህፍት፣ ፊልሞችና ከመገናኛ ብዙሃን የሚያገኟቸው መልእክቶች ትልቅ ሚና አላቸው። በተለይ ታሪክን ለልጆች በማስተማርና ማህበራዊ እሴቶችን በማስተላለፍ ረገድ ደግሞ ተረቶች ትልቅ ቦታ ይሰጣቸዋል።
የኮሮና ቫይረስ በማህበረሰቡ ውስጥ ሊያስከትል የሚችለውን የጤና ደህንነት በመፍራት ኢትዮጵያ እንደ አብዛኞቹ የዓለም አገራት ትምህርት ቤቶችን በመዝጋቷ፣ በአሁኑ ሰአት 26 ሚሊዮን የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በቤት ውስጥ እንደሚገኙና ይህም በመማር ማስተማሩ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንዳለው የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት አብዛኛው የጤና ተቋማት የእርግዝና ጊዜአቸው ገና የሆኑትንና ተጨማሪ የጎንዮሽ ችግር የሌለባቸውን እናቶች ቀጠሮ እንዲራዘም አድርገዋል። ይህን ተከትሎ አንዳንድ ነፍሰጡር እናቶች በተሳሳተ ግንዛቤ ወደ ጤና ተቃማት ለክትትል መሄድ ፍርሀት እንዳሳደረባቸውና አንዳንዶቹም ሙሉ ለሙሉ ክትትል በማቇረጣቸው ለችግር እየተጋለጡ መሆናቸውን የህክምና ባለሙያዎች ይገልፃሉ። በዚህም ምክንያት ለተጨማሪ የጤና እክል የሚጋለጡ እናቶች ተበራክተዋል።
የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከቀጠለ በኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው 15 ሚሊዮን ሰዎች በተጨማሪ ሌላ 15 ሚሊዮን ሕዝብ ለምግብ እጥረት ሊጋለጥ ይችላል ሲሉ በግብርና ሚኒስቴር እርሻ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሳኒ ረዲ ለቪኦኤ ገለፁ።
በሎስ አንጀለስ የሚኖረው የቴክኖሎጂ ባለሞያ ዮሴፍ አዱኛ ኢትዮጵያውያኖች የዲጂታል ኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ወደፊት ለሚፈጠሩ አዳዲስ የሰራ እድሎች ብቁ ሆነው እንዲገኙ በማሰብ የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን በአማርኛ እየተረጎመ ያሰለጥናል። በኢትዮጵያ የሚገኙ የትምህርት ተቋማትንም የቴክኖሎጂ ትምህርት አሰጣጣቸውን ለማሻሻል ያግዛል። ባልደረባችን ስመኝሽ የቆየ ከዮሴፍና እሱ የሚሰጣቸውን የቴክኖሎጂ ትምህርቶች ተምረው ራሳቸውን ከቀየሩ ወጣቶች ጋር ቆይታ አድርጋለች ቀጥሎ ይቀርባል።
በቴክኖሎጂ ሙያ ላይ የሚሰማሩ ሴቶች ቁጥር ከወንዶቹ ጋር ሲነፃፀር 26 በመቶ ብቻ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ጥቁር ሴቶች 3 በመቶ ብቻ ናቸው። የዛሬዋ እንግዳችን እሴተ ስዩም ግን እጅግ በጣም ትንሽ ጥቁር ሴቶች በሚገኙበት በዚህ የሙያ ዘርፍ ውስጥ እራሷን አሳድጋ በአለማችን ግዙፍ ከሚባሉት የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መሀከል፣ ማይክሮሶፍት ካምፓኒ ውስጥ በአመራርነት ታገለግላለች። ባልደረባችን ስመኝሽ የቆየ ከእሴተ ጋር ቆይታ አርጋለች።
በኮቪድ 19 ምክንያት ማህበረሰቡ በቤት እንዲቆዩ መወሰኑን ተከትሎ፣ በቅርብ የቤተሰብ አባላት ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶችና ሕፃናት ቁጥር ጭማሪ እያሳየ መሆኑን የአዲስ አበባ ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር አስታወቀ። በዚህ ወቅት ጥቃት የደረሰባቸው ህፃናትም በወረርሽኙ ምክንያት በቀጥታ ወደ መጠለያ ጣቢያዎች መግባት ባለመቻላቸው የለይቶ ማቆያ መጠለያ ማዘጋጀቱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታቋል።
በአሜሪካና በመላው አለም ላይ ከ ኮቪድ 19 ጋር የሚደረገው ግብግብ እንደቀጠለ ሆኖ ከቤት ያለመውጣትክልከላው መቼ ሊያበቃ እንደሚችል ግን ሰፊ መወያያ ሆኗል። በሽታውና የሚሰራጭባቸው መንገዶች አጣብቂኝ ውስጥ የሚከት ነው።
ሞዛንቢክ ላይ የጭነት መኪና ጀርባ ባለ ኮንቴይነር ውስጥ ተቆልፎባቸው ለሞት ከተዳረጉት 64 ኢትዮጵያውያን መካከል በህይወት የተርፉት 11 ሰዎች ባለፈው አርብ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል። ሲሞን ማርክስ ከአዲስ አበባ ያደረሰንን ሪፖርት ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።
ተጨማሪ ይጫኑ