የአማራ ክልል ፖሊስ ኮምሽን የኢንፎርሜሽን እና ሚዲያ ልማት ዋና መምሪያ ሃላፊ ረዳት ኮምሺነር ሰይድ አህመድ ባለፈው ዓርብ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተውቋል።
በባህር ዳር ከተማ አልፎ አልፎ ምሽት ላይ የሚሰማው የተኩስ ድምፅ ምንነት ግራ እንዳጋባቸው ለቪኦኤ አስተያየታቸውን የሰጡ አንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለፁ።
ላለፍት 7 ቀናት ሲያካሂዱት የነበረውን ፀሎተ ምህላ ያጠናቀቁት በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ምዕመናን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ይፈፀማሉ ያሏቸው ጥቃቶች እንዲቆሙ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በየክልላችሁ ተዋልደውና ተጋምደው የሚኖረውን የአማራ ህዝብ፣ በቆየው ኢትዮጵያዊው የመፈቃቀር መንፈስ አቅፋችሁ ኑሩ ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጥሪ አቅርበዋል።
አዲሱን ዓመት ምክንያት በአማራ ክልል ከ4ሺ በላይ ታራሚዎች እንዲለቀቁ ተወስኗል።
የዩንቨርስቲ መግቢያ ፈተና 645 በማምጣት በኢትዮጵያ ከፍተኛ የተባለውን ውጤት ያስመዘገበው ብሩክ ዘውዱ እና ወላጅ እናቱ ኤልሳቤት ጥላሁን ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
በነብርጋዴል ጀነራል ተፈራ ማሞ የምርመራ መዝገብ ከሁለት ሳምንት በፊት የባህር ዳር ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ውድቅ ያደረገውን ተጨማሪ የምርመራ የጊዜ ቀጠሮ የባህር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት አፀና።
በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ ጋር የተደረገ ውይይት፡፡
በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/አብን/ የብሔራዊ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ከሆኑት አቶ ተሰማ ካሳሁን ጋር የተደረገ ውይይት፡፡
በአማራ ክልል ያለፈው የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥ ወቅት “የቁጥጥር መላላት ነበር” የሚል ለክልሉ የትምህርት ቢሮም ለሃገር አቀፉ የፈተናዎችና ምዘና ኤጀንሲም የቀረበ ቅሬታ እንደሌለ የክልሉ የትምህር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ ገልፀዋል።
በተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ከተሞች የሚገኙ ትውልደ - ኢትዮጵያ ወጣቶች ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው ብባህርዳር ከተማ ከኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ጋር የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።
"አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን ታፍሰው ታሰሩብን" ሲል የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ አቤቱታ አሰምቷል።
ባህር ዳር ላይ በተካሄደ የአማራ እና የሶማሌ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ተገኝተው ተናግረዋል።
አቶ ተመስገን ጥሩነህ የአማራ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሆኑ።
በአማራ ክልል ከሰኔ 15ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የሚገኙት ከፍተኛ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፌዎች በርሃብ አድማ ላይ መሆናቸውን የአንዳንዶች ቤተሰቦች ተናገሩ።
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ በተነሣ ግጭት የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን ግጭቱ የተካሄደባት በማንዱራ ወረዳ የገነተ ማርያም ቀበሌ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ራዕይ ለኢትዮጵያ ባህር ዳር ከተማ ጉባዔ አካሂዷል፡፡ የራዕይ ለኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው ከአሜሪካ ድምፅ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
በቅዳሜው መፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የተገደሉት የአማራ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት የዶ/ር አምባቸው መኮንን፣ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የአቶ ምግባሩ ከበደና የፕሬዚደንቱ አማካሪ የእዘዝ ዋሴ የቀብር ሥነ ሥርዓት ዛሬ ረቡዕ፣ በባሕር ዳር ቅዱስ ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን ተከናወነ።
ራዕይ ለኢትዮጵያ ባሕር ዳር ከተማ ውስጥ ለሦስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ዓመታዊ ጉባዔ ከሰሞኑ አጠናቋል።
በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ግጭት አስነስተዋል ተብለው የተጠረጠሩ 224 ሰዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ