ሁለቱ የቀድሞ የብአዴንና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ሥር የዋሉት በጥረት ኮርፕሬት ፈፅመዋል ተብለው በተጠረጠሩበት የኃብት ብክነት ወንጀል ነው።
በክልልም ሆነ በሀገርቀፍ ደረጃ በዳኝነት የሙያ ዘርፍ የመጀመሪያ ማኅበር ነው ተብሏል፡፡
ስፖርት የሰላም፣ የአብሮነት የወዳጅነት ማሳያ ነው የፖለቲካ ማራመጃ አይደለም ሲሉ የአማራ ክልል የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገለፁ፡፡
“ኤልሻዳይ የእርዳታና የልማት ድርጅት በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት 'ከልመናና ከጎዳና ህይወት እናወጣችኃለን' በሚል ሰበብ ከጎዳና ላይ ታፍሰንና ተጋፈን ወደ ማሰልጠኛ ተቋም ብንወሰድም፤
“ኤልሻዳይ የእርዳታና የልማት ድርጅት በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት 'ከልመናና ከጎዳና ህይወት እናወጣችኃለን' በሚል ሰበብ ከጎዳና ላይ ታፍሰንና ተጋፈን ወደ ማሰልጠኛ ተቋም ብንወሰድም፤ ለጉልበት ብዝበዛ እና ለሰባዊ መብት ጥሰት ተዳርገን ቆይተናል” ሲሉ ከአፋር ክልል አሚባራ ወረዳ አዲስ ራይ ማሰልጠኛ ተቋም ተፈናቅለው ባህር ዳር ከተማ የመጡ ወጣቶች ገለፁ።
"ከሆስፒታሉ ካርድ ከማውጣት ውጭ ምንም ዓይነት አገልግሎት ማግኘት አልቻልንም። ምርመራ ከግል ሆስፒታል አድርጉ፣ መድሃኒት ከውጭ ግዙ ነው የምንባለው" ሲሉ በባህር ዳር ከተማ የፈለገ ሕይወት ሪፈራል ሆስፒታል ተገልጋዮች ገለፁ።
ከዘጠኝ ክልሎች የተወጣጡ ሃያ ሁለት እናቶች - በባህር ዳር
በዕርዳታ በተገኘ ገንዘብ ባጃጅ ገዝቶ በመስጠት ሥራ ያልነበራቸው ያላቸውን ሃያ አምስት ወጣቶች ሥራ ማስጀመሩን የከተማ አስተዳደሩ የጥቃቅንና የአነስተኛ ንግዶች ልማት መምሪያ ገልጿል።
የአማራና የቅማንት ሕዝብ በባህል፣ በቋንቋ፣ በሃይማናትና በሥነ ልቦና አንድ ሕዝብ ነን፣ ሊለያዩን የሚሹ ወገኖችን ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም ስለ ሰላም እንሰራለን ሲሉ በጎንደር በተደረገው የሰላም ውይይት ላይ የተገኙ የሁለቱም ወገን ተሳታፊዎች ተናገሩ።
ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ካማሽ ዞን፣ ያሶ ወረዳ ከሚገኘው ቀያቸው ተፈናቅለው ባህርዳር ከተማ የገቡ አምስት መቶ ተፈናቃዮች ከክልሉ መንግሥት ድጋፍ አለማግኘታቸውን ገልፀው ቅሬታ አቀረቡ።
የአማራ ሕዝብ በአለፉት ጊዜያት በማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ኮስሶ እንዲታይ በውሽት ትርክት ክብሩ ዝቅ እንዲል ሲደረግ፣ መኖሩ ቁጭትን ፈጥሮብናል ይላሉ የባህር ዳር ከተማ ወጣቶች፡፡
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በደንቢያና ጭልጋ በቅማንትና አማራ ብሄር ተወላጆች መካከል ከአራት ቀናት በፊት በተቀሰቀሰ ግጭት ከሥድስት በላይ ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ የሰላምና ደኅንነት ቢሮ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፀ።
ህዝቡ ራሱ ታግሎ ያመጣውን ሰላምና ነፃነት ወደ ኃላ እንዳይቀለበስ ከመንግሥት ጎን ሊቆም ይገባል ሲል የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ገለፀ።
ጎንደር ዩንቨርስቲ በችግር ምክንያት የከፍተኛ ትምህርታቸውን መቀጠል ላልቻሉ ለ60 አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል እየሰጠ መሆኑን የጎንደር ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት ገለፀ። ከ60ዎቹ ውስጥ 40ዎቹ ሴቶች ናቸው፡፡
ጤና ነክ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ አሉባልታዎች በተለይ የክትባትና የምርምር ሥራዎችን ለመሥራት እንቅፋት ሆኖብኛል ይላል የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ።
በጣና ቂርቆስ ገዳም የሚኖሩ መነኮሳት በእንቦጭ አረም ምክንያት ህልውናችን አደጋ ላይ ወድቋል ሲሉ ተናገሩ።
ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ሰላምን ለመስበክ በራሳቸው ፈቃድ የተሰባሰቡ የሰላም እናቶች ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ በመገኘት ለአዲስ አበባና ለባህር ዳር ከተማ ወጣቶች ስለ ሰላም ሰብከዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የጣና ሀይቅን ከእምቦጭ አረም ለመታደግ የአሥር ሚሊዮን ብር ልገሳ በከተማው አስተዳደር ስም አበረከቱ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ