የትምህርት ተቋማት የእውቀት እንጅ የግጭት ማዕከል እንዳልሆነ ተማሪዎች ተረድተው የመጡበትን ዓላማ ለማሳካት ቅድሚያ መስጠት አለባቸው ሲሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገለፁ።
"ወሰንና የማንነት ጥያቄን በህገ መንግሥቱ አስመልሳለሁ" ይላል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ በቅርቡ አካሂዶት በነበረው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ።
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር ትላንት ከባህርዳር ከንቲባ ጋር በተለያዮ ጉዳዮች ላይ እንደመከሩ ተገለፀ።
የወልቃይት ህዝብ ማንነት እኛ የወልቃይት ተወላጆች እንጂ ሌላ አካል እንዲገልፅልን አንፈልግም ሲሉ ቪኦኤ ያነጋገራቸው የወረዳዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የፌዴሬሽን ም/ቤት በማንነት ዙርያ እያወጣው ያለው መግለጫ እንደ ተቋም ገለልተኛ ያልሆነና ወገንተኝነት የሚታይበት ነው ሲሉ የወልቃይት ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮሎኔል ደመቀን ጨምሮ አንዳንድ የወልቃይት ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።
የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ(አዴፓ) እና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) አንድ ፓርቲ ሆነው በጋራ ለመሥራት ተስማሙ።
የኢትዮጵያ፣ የኤርትራና የሶማልያ መሪዎች ስለአካባቢያቸው ሰላምና ምጣኔ ኃብት መምከር በአፍሪካ ቀንድ ለሚታየው የስደትና የድኅነት ማዕበል መረጋጋት ይፈጥራል ሲሉ አንዳንድ የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ጠ/ር አብይ አሕመድ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እናየሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ አመሻሹን ባህርዳር ከተማ ገብተዋል፡፡ መሪዎቹ ባህርዳር ከተማ ሲደርሱ የከተማዋ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አደርገውላቸዋል።
ጠ/ር አብይ አሕመድ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ዐብዱላሂ ሞሐመድ አመሻሹን ባህርዳር ከተማ ገብተዋል፡፡
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ዛሬ ጎንደር ከተማ ገቡ፤ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አቀባበል አደርገውላቸዋል ሲሉ መንግታዊ ዜና አውታሮች ዘገቡ።
በምዕራብ ጎንደር ዞን በተለይ መተማ አካባቢ ሰሞኑን ሁከት ተፈጥሮ ነበር። በሁከቱ የሰው ህይወት ጠፍቷል ንብረትም ወድሟል።
የእንቦጭ አረም በእለት ከእለት ኑሮአችን ላይ የከፋ ችግር እየፈጠረብን ነው ሲሉ የአካባቢው አርሶ አደሮች ገለፁ።
ከወልቃይት ጠገዴ ተፈናቅለው ጎንደር ከተማ በጊዚያዊ መጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሚገኙት ተፈናቃዮች መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ ይስጠንና ወደቀያችን እንመለስ ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።
ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማካሄድ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ገልጿል።
ማኅበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ ለሚያውሉ ግለሰቦችና ቡድኖች በየዓመቱ ዕውቅና የሚሰጠው ሁለተኛው የጣና ሽልማት ሰሞኑን በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል።
"የላሊበላን ቅርስ እንታደግ" በማለት የከተማዋ ነዋሪዎች ትላንት ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
በ12ኛው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ የተደረገው የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ምርጫ፣ ፍፅም ዴሞክራሲያዊ እንደነበር በድምፅና ያለ ድምፅ የተሳተፍ ጉባዔተኞች ገለፁ።
አሥራ አንደኛው የአህዴግ ድርጅታዊ ጉባዔ የተለየ የርዕዮተ-ዓለም ለውጥ እንደማያደርግ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ /አዴፓ/ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።
በምኅፃር “ብአዴን” እየተባለ ሲጠራ የነበረው የአማራ ክልል ገዥ ፓርቲ ብሔረ-አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ስሙን ወደ “አማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” (አዴፓ) መቀየሩን ትናንት አስታውቋል።
የብአዴን ጉባዔ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል፡፡ ጉባዔው በዛሬው ውሎው በክልሉ ልማት በዴሞክራሲና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ባሉ ችግሮች ላይ መወያየቱ ተገልጿል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ