ጅግጅጋ ተወልዶ ያደረገውና ኑሮውን በአዲስአበባ ያደረገው ሱራፌል ጥላዬ ለሌሎች ወጣቶች ምሳሌ የሚሆን በጎ ተግባር አከናውኗል ሲሉም ሌሎች ምስክርነት ይሰጡለታል። አዲስ ቸኮል ለዛሬው የዘጋቢዎቻችን መስኮት መሰናዶ አነጋግሮታል።
አምና ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ቀናት ጂጂጋን ጨምሮ በሶማሌ ክልል ልዩ ልዩ ከተሞች ሄጎ ተብለው በተደራጁ ወጣቶች እንደተፈፀመ የሚነገርለት ዘርፈብዙ ጥፋት ደርሷል፡፡ ከደረሱት ጥፋቶች መካከል አብያተ ክርስትያናትን ዒላማ ያደረገው ጥፋት ይጠቀሳል፤ በጥቃቱ 10 አብያተ ክርስትያናት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፡፡ ከ300 ሚሊዮን በላይ የሚገመት የቤተክርስትያኗ ሀብት እንደወደመም ቀሳውስቱ ይናገራሉ፡፡
በድሬዳዋ ከተማ በዳቦ ማምረትና ማከፋፈል ዘርፍ ለመሰማራት በቅርቡ በሽርክና ከተደራጁ አምስት ወጣቶች መካከል አንዱን ወጣት ማርኮን ይልማን ለጋቢና ቪኦኤ እንግዳ አድርገነው ነበር።
ኢትዮጵያና አሜሪካ በምስራቅ ኢትዮጵያ ሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ጥምር ወታደራዊ ልምምድ እያካሄዱ መሆናቸው ተገለፀ፡፡
ድሬዳዋ በትላንትናው ዕለት በችግኝ ተከላው ሰፊ ተሳትፎ አድርጋለች፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 2ኛ የስራ ዘመን 6ኛ አስቸኳይ ጉባዔ አዲስ አፈጉባዔና አዲስ ምክትል ከንቲባ ሾሟል፡፡
“ሐገረ-መንግሥት ግንባታና ብሄራዊ መግባባት በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ውይይት ድሬ ዳዋ ላይ ተካሂዷል።
በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን በገንዘብ ትረዳላችሁ በሚል ተጠርጥረው ታስረው የነበሩ 56ቱም ተጠርጣሪዎች ከ10 ቀን ቆይታ በኋላ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር ተለቀዋል፡፡
በሐረር ሸዋ በር የመብራት ኃይል ገበያ ማዕከል በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ከ300 በላይ መደብሮች እንደወደሙ ተገለፀ፡፡
በድሬዳዋ የእግር ኳስ ውድድርን ተከትሎ የተነሳ የሠፈር ፀብ፣ ቆይቶ የብሔር መልክ በመያዝ በድርጊቱ ተሳታፊ ያልነበሩ ንፁሐንን ጭምር ለጥቃት መዳረጉን ተጎጂዎች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ፡፡
የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ጭምር የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ እየተወዳደረ ያለ ክለብን በማሰልጠን የመጀመሪያዋ ናት፡፡
በአፋርና በሶማሌ ክልሎች ድንበሮች አካባቢ ከአንድ ሣምንት በላይ መዝለቁ የተነገረ ግጭት መርገቡንና መረጋጋት መፈጠሩን ነዋሪዎች ገልፀዋል።
ኮሌራ ከተከሰተባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው የምዕራብ ሐረርጌ ዞን እስከ ትናንት፣ ማክሰኞ 244 ለኮሌራ የተጋለጡ ሕሙማንን መለየታቸውን የዞኑ ጤና ጥበቃ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አህመዲን መሀመድ በተለይ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ገልፀዋል።
ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር በ2009 ዓ.ም የተመደበው አሥር ቢሊዮን ብር ተዘዋዋሪ ብድር ለታለመለት ዓላማ መዋሉን ማረጋገጥ እንዳልቻለ ፌደራል ዋና ኦዲተር ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሣምንት በፊት ባቀረበው ሪፖርት አሳውቋል።
በምሥራቅ ሀረርጌ ደንገጎ አካባቢ በህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች ላይ ተደጋጋሚ ዘረፋ እየተፈፀመ ነው ሲሉ የሐገር አቋራጭ አውቶብሶች ስምሪት ኃላፊዎች በተለይ ለቪኦኤ አስታወቁ፡፡
1440ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ህዝበ ሙስሊሙ በተገኘበት በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ፣ በአሥመራ ተከበረ፡፡
በረመዳን የፆም ወር ለፆም መፍቻነት ተብለው የሚዘጋጁ ልዩ ልዩ የምግብ ዓይነቶች አሉ፡፡ በድሬዳዋ ዋነኛው የፆም መፍቻ ምግቦች መሸጫ ኮኔል እና አምስተኛ አካባቢ ነው፡፡ ለገበያ ከቀረቡ የማፍጠሪያ ምግቦች ከፊሎቹ እንዲህ ተዳሰዋል፡፡
ላለፉት 4 ወራት ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች የኮንዶሚኒዬም ቤታቸው ተወስዶባቸው የነበሩ የሀረር ገልመሺራ ነዋሪዎች ቤቶቻቸው ተመልሰውላቸዋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ