በሀረሪ ክልል ማንነታቸው ያልታወቁ የመሬት ይገባናል ጥያቄ ያነሱ ግለሰቦች በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውና በርካታ ቤቶችንም ማፍረሳቸው ተገለፅ፡፡
በድሬዳዋ ማረሚያ ቤት በተደረገ ፍተሻ ከስድሣ በላይ ተንቀሳቃሽ ስልኮች እና ስለታማ ቁሰቁሶች መያዛቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ፑንት ላንድ በሃገሯ የሚገኙ 1400 ኢትዮጵያውያንን ወደ ኢትዮጵያ መልሳለች፡፡
ዛሬ ድሬዳዋ ላይ የታየው በአንድ ሊትር 48 ብር የሚያወጣውን ዘይት ከነጋዴዎች ከመግዛት በመንግሥት ሊትሩ በ26 ብር ሂሳብ የሚቀርበውን ዘይት ለመግዛት የተያዘ ወረፋ ነው፡፡ ቀኑን ሙሉ ወረፋ ይዘው ሳይደርሳቸው ለነገ የተቀጠሩም አሉ፡፡ ለአንድ ቤተሰብ በሽያጭ የሚቀርበው ከፍተኛው መጠን 5 ሊትር ነው፡፡
168 የኢትዮጵያ ከተሞች በልማት፣ በመልካም አስተዳደር፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በመሰረተ ልማት፣ እና ተያያዥ ጉዳዮች ያከናወኗቸውን ተግባራት በምስል፣ በቅርፅ፣ በባነርና በናሙና አምጥተው እርስ በርስ የሚማማሩበት የከተሞች ፎረም ኤግዚቢሽን አከባበር በከፊል ይሄንን ይመስላል፡፡ ከተለያዩ ከተሞች ለተሳትፎ ወደ ጅጅጋ የሄዱት 10ሺ ገደማ ሲሆኑ የጅጅጋ ከተማም 60 አውቶብሶችን በማዘጋጀት የከተማዋና አካባቢዋ ነዋሪዎች ኤግዚቢሽኑን እንዲጎበኙ ተደርጓል።
ኢትዮጵያ ከ2013 እስከ 2023 ዓ.ም የምትመራበት መሪ የልማት እቅድ ጥናት ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለፀ፡፡
በኢትዮጵያ ከተሞች ያለውን ስር የሰደደ የቤት ችግር ለመቅረፍ መንግሥት 7 አይነት አማራጮችን እንደሚከተል የቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ደኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ አስታወቁ።
በሶማሌ ክልል የተለያዩ ዞኖችና በዋናነት በድሬዳዋ ዙሪያ እንዲሁም በምስራቅ ኦሮሚያ ተሠባጥረው የሚገኙት የጉርጉራ ጎሣዎች 54ኛውን ኡጋዛቸውን (የጎሣ መሪያቸውን) ሾመዋል:: በበዓለ ሲመቱ ላይ ለመሳተፍ ከሰሜን አሜሪካ፣ አውሮፓ፣ አውስትራሊያና ቻይና በርካታ የጎሳው ተወላጆች ተገኝተዋል:: ከዘጠኙም የሶማሌ ክልል ዞኖች ከሶማሊላንድ፣ ከኬንያና ጂቡቲ በእንግድነት ተጋብዘው የመጡ ኡጋዞች ፣ ሱልጣኖችና ገራዶችም ነበሩ::
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ በድሬዳዋ ተነስቶ በነበረው ተቃውሞ በቁጥጥር ሥር አውሏቸው ከነበሩ 308 ተጠርጣሪዎች መካከል ዛሬ አመሻሽ ላይ 44ቱን እንደለቀቀ አስታወቀ፡፡
ጥር 13 ቀን 2011 ዓ.ም የጥምቀት በዓል ላይ የእግዚአብሔር አብ ቤተክርስትያን ታቦት ሲገባ በምዕመናን ላይ የተፈፀመውን ትንኮሳ ተከትሎ በተነሳው ተቃውሞ ከታሰሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተጠርጣሪዎች መካከል 86ቱ ትናትናና ዛሬ አመሻሽ ላይ ክሰቸው ተቋርጦ ተለቀዋል፡፡
በድሬዳዋ ከሳምንት በፊት ተቀስቅሶ በነበረው ተቃውሞ ሁከትና ረብሻ አስነስተዋል፣ ከተባሉት መካከል 155ቱ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፤
በድሬዳዋ የሐይማኖት በዓል አከባበር ላይ የተፈፀመ ጥቃትን ተከትሎ የተነሳው ተቃውሞ ላይ ተሳትፋችኋል በመባል የተያዙ 27 ተጠርጣሪዎች ላይ የአስተዳደሩ የመጀመሪያ ፍርድቤት ፈቅዶት የነበረውን ዋስትና የይግባኝ ሰሚ ፍርድቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ከጂግጂጋ ወደሃረርና አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ባቢሌ ላይ ተዘጋ፡፡
በትላንትናው ዕለት ከጭናክሰን ከተማ አካባቢ ቤተክርስትያን አንግሰው ወደ ጂግጂጋ ከተማ ሲመለሱ በነበሩ ምዕመናን ላይ ጥቃት መፈፀሙንና ይሄንን ተከትሎ በተነሳው ረብሻ ሁለት ሰዎች መገደላቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች ለቪኦኤ ተናገሩ፡፡
የአካባቢው ነዋሪ ማኅበረሰብ ያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በአፋጣኝ ለመፍታት ልዩ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ሊገባ መዘጋጀቱን የድሬዳዋ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
የፌዴራል መንግሥት አመራሮች የድሬዳዋ ነዋሪዎችን በከተማዋ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አወያይተዋል፡፡
በድሬዳዋ ከተማ በጥምቀት አከባበር በዓል ላይ ያልታወቁ ሰዎች በምዕመናን ላይ የፈፀሙትን ትንኮሳ ተከትሎ የተነሳው አለመረጋጋት ዛሬ ተባብሶ ቀጥሏል። ተቃውሞውም ሃይማኖትን ከመከላከል ወደ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተሻግሯል። በከተማው የታሰሩ ወጣቶች እንዲፈቱም ተጠይቋል። በዛሬው ዕለት በአብዛኞቹ የከተማዋ መንገዶች፣ የንግድ ማዕከላት የሆኑት ቀፊራ፣ ኮኔል፣ ታይዋን፣ ሩዝ ተራ፣ አሸዋና አካበቢው ያሉ መደብሮችና ባንኮችም ተዘግተው ውለዋል።
ከትናንት አመሻሹ ጀምሮ ድሬዳዋ ላይ ግጭት ተከስቷል፤ ግጭቱ እስከዛሬ ከሰዓት የዘለቀ ነበር፡፡ በግጭቱ የሞቱና የከፋ ጉዳት የደረሰበት ባይኖርም ቀላል የአካል ጉዳቶችና የንብረት ውድመቶች መከሰታቸው ግን ሪፖርት ተደርጓል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ