በባለፈው መስከረም በቡራዩ ከተማና በአካባቢው እንደዚሁም በአዲስ አበባ ተከስቶ በነበረው ግጭትና ግድያ በተጠረጠሩ ከመቶ በላይ ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱን የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡
የአቶ ንጉሡ ጥላሁን በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ኃላፊ ሆኖ መሾም የቢል ለኔ ስዩም መነሳት አያሳይም ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትር ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የቀድሞውን የአማራ ክልል ቃል አቀባይ ንጉሡ ጥላሁንን የጽ/ቤታቸው የፕሬስ ኃላፊ አድርገው ሾመዋል፡፡
የቀድሞውን የብሄራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው አሰፋን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ከትግራይ ክልል ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡
ከአንድ ዩኒቨርስቲ በስተቀር በሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንደቀጠለ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስትር አስታወቁ፡፡
የኢትዮጵያን ሕግጋት ማንም ተጠቃሚና የሚፈልግ ሰው በቀላሉ እንዲያገኛቸው ለማድረግ የታሰበ የመረጃ ቋት ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ የኤርትራ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ሰመረ ርእሶም የሹመት ደብዳቤያቸውን ዛሬ ለፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ አቅርበዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥት የአዳዲስ አምባሳደሮችን ሾመ።
የኢትዮጵያ ፓርላማ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅን አፅድቋል፡፡
በኢትዮጵያ የታወጀው የምህረት ዓዋጅ የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ ጥቂት ሳምንታት እንደቀሩት የገለፀው የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ፣ የሚመለከታቸው ሁሉ በፍጥነት እንዲጠቀሙበት ጥሪ አቀረበ፡፡
ዶ/ር ዐብይ አህመድንና የለውጥ ቡድናቸውን ስልጣን ያመጣው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ነው ሲሉ ሁለት አንጋፋ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች አስታወቁ፡፡
የቀድሞ የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዮርጊስ የቀብር ሥነ ስርዓት ዛሬ በመንበረ ፀባዎት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ኃላፊነታቸውና በቀደመው የሕይወት ጉዟቸው ታላቅ አስተዋፅዖ ማድረጋቸው በሥነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡
በአለፉት 27 ዓመታት በኢትዮጵያ የተፈፀሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እየተገለፀ ካለውም የከፉ መሆናቸውን፣ በቀዳሚነት በጉዳዩ ላይ ሲሰራ የቆዮ ሀገር በቀል ድርጅት ይናገራል፡፡
ኢትዮጵያን ወደ ኋላ የሚመልስ ኃይል የለም ሲሉ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ ተናገሩ፡፡
በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ክልሎች ከተፈጠረው ግጭት ጀርባ በጣም የተደራጀ ኃይልና ጉልበት አለ ሲል የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር መንስዔ እየተጠና መሆኑንም አመልክተዋል፡፡
በተለያዩ የዓለም ሀገራት በሚገኙ 59 የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና የቆንሲላ ጽህፈት ቤቶች ያካሄደውን የዲፕሎማቶችና የሌሎች ሠራተኞች ድልድል መጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የፌዴራል መንግሥት የጸጥታ አካላት በኦሮሚያና በቤንሻንጉል አዋሳኝ አካባቢዎች ያለውን ችግር ለመፍታት ታጣቂዎች እንደሚገቡ ተገለጸ።
ሰሞኑን በጠ/ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ሰብሳቢነት የተካሄደው የፓርቲዎች ውይይት በምርጫ ቦርድ መሪነት እንደሚቀጥል የጠ/ሚኒስቴር ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
በከፍተኛ የስብዓዊ መብት ጥሰት የተጠረጠሩ ባለሥልጣናት ገንዘብ እንዲታደግ ከኢትዮጵያ መንግሥት የቀረበ ጥያቄ ስለመኖሩ፣ አናረጋግጥም፣ አናስተባብልም ሲሉ አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን ተናገሩ፡፡
የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎችና አባላት የኢትዮጵያ ዜግነት ለማግኘት አሁን የያዙትን ፓስፖርት መተው እንዳለበቸው ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ