በቡራዩ በሚኖሩ የጋሞ ተወላጆች ላይ የተፈፀመውን ግድያ ተከትሎ በጋሞ ጎፋ ዞን ዋና ከተማ አርባ ምንጭ የታየውን የአንዳንድ ወጣቶች የጥቃት ሙከራ ከተከላከሉት የጋሞ ብሔረሰብ ባህላዊ መሪ አንዱን አነጋግረናቸዋል።
አሁን በሀገሪቱ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ ከስሜታዊነት መውጣትንና አስተውሎ መንቀሳቀስን የሚጠይቅ መሆኑን የሁለት ዋና ዋና የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎች አስታወቁ፡፡
ከትናንት በስተያ ተዘግቶ የዋለው በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ትናንት ወደ መደበኛ ሥራው ተመልሷል።
በአዲስ አበባና በቡራዩ ለደረሱ ጉዳቶች ተጠያቂ የሆኑ ኃይሎችን በተመለከተ ከፌደራል ፖሊስ የተሰጠው መረጃ ለተለያዩ ትርጉሞች ሊጋለጥ አንደሚችል የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሥጋታቸውን ገልፀዋል፡፡
በቡራዩና በአካባቢው "በተደራጁ ኃይሎች የተፈፀመ ነው" በተባለው ጥቃት የተገደለው ሰው ቁጥር ሃያ ሦስት መድረሱን የኦሮምያ ፖሊስ ኮሚሽነር አስታውቀዋል።
አዲሱ ዓመት በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ መሠረት የሚይዝበት እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እያስመዘገቡ ናቸው ያለችውን ለውጥ እንደምታደንቅ የገለፀችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን ዛሬ /ዕሁድ፣ ጳጉሜ 4/2010 ዓ.ም/ የዕውቅና ሽልማት አበርክታላቸዋለች።
በትናንትናው ዕለት የታሰሩት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ ዘጠኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች የታሰሩት አድማ በማስተባበር ኢኮኖሚውንና የሀገሪቱን ገፅታ የሚጎዳ ተግባር ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው እንደሆነ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡
"አሁንም በመስቀለኛ መንገድ ላይ ነን" ሲሉ ፕሬዚዳንት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ተናገሩ።
ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን እየታየ ያለው ለውጥ እንዲመጣ ከፍተኛ “አስተዋጽዖ አድርገዋል፤ መስዋዕትነት ከፍለዋል” ኢትዮጵያዊያን ዕውቅና ለመስጠት ሥራ መጀመሩን አንድ የሽልማት ድርጅት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ሥራ የማቆም አድማ መትተዋል።
ወደ ሥልጣን ኃላፊነት ከመጡ በኋላ የመጀመሪያው የሆነውን ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት ጠ/ሚ አብይ አሕመድ የርሳቸውም ሆነ የድርጅታቸው ፍላጎት በኢትዮጵያ በዕውነተኛ ምርጫ ተመርጦ ማገልገል እንደሆነ ገልፀዋል። የምርጫ ጊዜው እንዲተላለፍ እንደማይፈልጉም ተናግረዋል።
ኤችአር 128 ተብሎ የሚታወቀውን የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ቀደም ሲል ባሳለፈው የሰብዓዊ መብቶችና የተጠያቂነት ሕግ ላይ ከተቀመጡት አንቀፆች አንፃር በሀገሪቱ ያለውን መሻሻል ለባልደረቦቻቸው እንደሚያስረዱ ኢትዮጵያ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች አስታውቀዋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስና ሌሎች ዲሞክራሲያዊ ሀገሮች ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድና ለአሰባሰቡት ቡድን ድጋፍ እንደሚሰጡ የዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ እንደራሴ ክሪስ ስሚዝ እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡
እየተጠናቀቀ ያለው የ2010 ዓ.ም የተለያዩ ዲፕሎማሲ ስኬቶች የተገኙበት መሆኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ መንግሥት በፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በኩል በተቋቋመ ገለልተኛ ምክር ቤት አማካኝነት ሮሮ የሚሰማባቸውን ዐዋጆች በመመርመር ጀምሯል።
የበጎ አድራጎትና ሲቪክ ማኅበራት ዐዋጅ ለሥራቸው እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን የገለፁ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ተወካዮች ዐዋጁን ለማሻሻል በተያዘው ጥረት ላይ ተስፋቸውን ጥለዋል።
ፈተናዎች ቢያጋጥሙንም በኢትዮጵያ የተጀመረው የለውጥ ሂደት ወደኋላ አይመለስም ሲሉ የመንግሥት ኮሙኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚንስትር አሕመድ ሺዴ አስታወቁ።
በጂግጂጋ ከተማ ያለው የፀጥታ ሁኔታ የተሻሻለ መሆኑን አሁንም በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቤተክርስቲያን ተጠልለው እንደሚገኙ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በሀገሪቱ እየታየ ያለ ለውጥ የዕጩዎች ጥቆማና ምርጫ በነፃነት እንዲካሄድ እያስቻለ መሆኑን የበጎ ሰው ሽልማት አስታውቋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ