የሪዮ ኦሎምፒክ የብር መዳሊያ ባለቤትና የሰብዓዊ መብት ታጋይ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ሀገሩ እንዲመለስ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የተናጥል ተኩስ አቁም ማድረጉን ያስታወቀው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር /ኦብነግ/ አመራሮች ትላንት ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ከዩናይትድ ስቴይትስ ከተመለሱ በኋላ በስፋት ያተኮሩት በሶማሌ ክልል የተፈጠረውን የፀጥታ ሁኔታና ግጭት መፍትኄ ለመስጠት መሆኑን አስታውቋል።
በሶማሌ ክልል የተፈጠረውን ብጥብጥና የደረሰውን ጉዳት ተከትሎ በሽሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ሐረር ከተማ መሰደዳቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ከአሰብ እስከ አዲስ አበባ የነዳጅ ማስተላለፊያ ቱቦ ለመዘርጋት ከሥምምነት ላይ መድረሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ከተሞች ጎሳን መሰረት ያደረግ ግጭት ተቀሰቅሶ የብዙዎች ሕይወታ መጥፋቱና ንብረት መውደሙ ይታወቃል፡፡
በደረሰባቸው ጉዳት ምክንያት ወደ ተለመደ ሕይወታቸው እና ኑሯቸው መመለስ እንዳልቻሉ የገለፁ የጂግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች መንግሥት ችግራቸውን እንዲመለከትላቸው ጠይቀዋል፡፡
በርሃብና በውሃ ጥም እየተቸገርን ነው ሲሉ በሶማሌ ክልል በተከሰተው ብጥብጥ ምክንያት ተፈናቅለው በቤተ ክርስቲያን የተጠለሉ እና ሌሎችም የጂግጅጋ ከተማ ነዋሪዎች አማረሩ፡፡
ወልቃይትና አካባቢው ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ ለሲቪክ ማህበራትና ለጋዜጠኞች ክፍት እንዲደረግ “ልሳነ ግፉዓን” የተሰኘ ድርጅት ጠይቋል፡፡
በዕርቀ ሠላም መርሃ ግብሩ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመን ጨምሮ የተለያዩ ሀይማኖት መሪዎች፣ አምባሳደሮች ተገኝተዋል፡፡
በሶማሌ ክልል በንፁሐን ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጥቃት ለማስቆም የፌዴራል መንግሥቱ መግባት አስፈላጊ መሆኑን በቤተክርስቲያን ተጠልለው የሚገኙ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በጅቡቲና በኤርትራ መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት የሽምግልና ሚና የመጫወት ሚና ፍላጎት እንዳላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የአምባገነኖች ጊዜ አልፏል ያሉ አንዳንድ የአፋር ወጣቶች ፌደራል መንግሥቱ በክልሉ የሚፈፀሙ የሰብዓዊ የመብት ጥሰቶችን እንዲያስቆሙ ጠየቁ፡፡
የኢትዮጵያ የተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አራተኛ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከ27 ዓመታት ስደት በኋላ፣ ዛሬ ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል፡፡
በኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት ማዘናቸውን የተለያዩ ከተማዎች ነዋሪዎች ትናንት የሻማ ማብራት ሥነ ስርዓት አካሂደዋል፡፡
ትላንት በመኪናቸው ውስጥ ሞተው የተገኙት የታላቁ የኅዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ሥራ አስኪያጅ የኢንጂነር ስመኘው በቀለ የቀብር ሥነስርዓት የፊታችን እሁድ እንደሚፈፀም አስተባባሪ ኮሚቴ አስታወቀ።
በአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ እንደሚሆን የሚነገርለት ግዙፉ የሕዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ መሃንዲስ ስመኘው በቀለ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኙ።
በባሌ ዞን ጎባ ከተማ በደረሰው ግጭት እስከ አሁን በተረጋገጠው አሥር ሰዎች መገደላቸውን፣ ከአንድ መቶ በላይ ደግሞ ቀላል እና ከባድ የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል።
ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሄደው የኢትዮጵያ ፓርላማ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሂደት ላይ የነበረውን የምህረት ዓዋጅ በአንድ ድምፀ ታዕቅቦ እና በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ እያካሄዱ ያለው ለውጥ ከፍጥነትም ሆነ ከይዘት አንፃር የሚደነቅ መሆኑን ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ