ዩናይትድ ስቴትስ የጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድን የመቶ ቀናት ክንውኖች አድንቃለች፡፡
ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው ከመጡና በቢሾፍቱ ከተማ በመቋቋም ላይ ከነበሩ ወጣቶች ዘጠኙ መታሰራቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡
በቅርቡ በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተፈረመውን የሰላምና የወዳጅነት ስምምነት ተግባራዊ የማድረጉ ሂደት መጀመሩን አቶ መለስ ዓለም ገለፁ፡፡
በአለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት በመንግሥት የደኅንነት ኃይሎች ተጠልፈው የተወሰዱና የደረሱበት ሳይታወቅ የቀየ የዜጎች ጉዳይ መፍትኄ እንዲሰጠው ቤተሰቦቻቸው እየጠየቁ ነው፡፡
በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ለማስቆም የሚደረጉ ሙከራዎች ባዶ መሻቶች ናቸው ሲሉ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አሕመድ ተናገሩ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ከሦስት ሳምንታት በኋላ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚያደርጉት ጎዞ ብቸኛ ዓላማ በዛ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መነጋገር መወያየት መሆኑን በአዲስ አበባ የሚንቀሳቀሰው አብይ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
የኤርትራ መንግሥት የልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ያደረገው ጉብኝት የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መሻሻልና ለተጨማሪ ውይይቶች መንገድ መጥረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አስታወቁ፡፡
የኢትዮጵያና የኤርትራ መሪዎች ለሃያ ዓመታት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኝተው ለመነጋገር ተስማምተዋል።
የተጀመረው የሰላም ሂደት በየሀገሮቻቸው ከፍተኛ ደስታ መፍጠሩን የገለፁት ኢትዮጵያና ኤርትራ አሳዛኙ የታሪክ ምዕራፍ መዘጋቱን አስታውቀዋል፡፡
የኤርትራ መንግሥት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከሃያ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ የቀረበውን ጥሪ ተከትሎ ሁኔታዎችን ለመርመር የመጣው የልዑካን ቡድን የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከፍተኛ አማካሪ የማነ ግብረአብና የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳላህ የሚገኙበት ነው፡፡
በአዲስ አበባው የመስቀል አደባባይ የቦምብ ጥቃት ሕይወታቸው ያለፈው ሁለት ሰዎች ማንነት ይፋ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ ዛሬ ከቦንብ ጥቃት አመለጡ፣ 132 ዜጎች ቆስለዋል፡፡ ሌላ አንድ መሞታቸውን ተገልጿል፡፡
ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ እየወሰዷቸው ባሉ አውንታዊ እርምጃዎች በእጅጉ ተበረታተናል ሲሉ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ማይክ ሬነር አስታወቁ፣ አሳሳቢ ለሆኑ ጉዳዮች ምላሽ ለመስጠት ኢትዮጵያ እያደረገች ያለችውን ጥረት ለመደገፍ፣ ሀገራቸው የምትችለውን ሁሉ እንደምታደርግም አምባሳደሩ አረጋግጠዋል፡፡
የዓለም የስደተኞች ቀን የጎረቤት ሃገሮች ስደተኞችን እያስተናገደች ባለችው ኢትዮጵያም በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች እየታሰበ ነው።
መ/ቤታቸው ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ ሆኖ እንደሚሰራ አዲሱ የኢትዮጵያ የደሕንነት ኃላፊ ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ ሀብት “በብዙ ሀገሮች ተከማችቷል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተጠያቂዎቹን ለህግ ለማቅረብ አስተዳደራቸው ከየሀገሩ መንግሥት ጋር እየሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለው ይቅርታ መንግሥትን ጭምር መጥቀሙን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ተናግረዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ በሚገኙ ሦስት ከተሞች ውስጥ ባለፉት አምስት ቀናት በተካሄዱ ግጭቶች 15 ሰዎች መገደላቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ