የኢትዮጵያና የኤርትራ የድንበር ውዝግብና የመንግሥት ድርጅቶችን ወደ ግል ይዞታ ማዞርን በተመለከተ በመገናኛ ብዙኃን ይፋ መግለጫ ከመሰጠቱ በፊት የኢሕአዴግ ምክር ቤት መወያየት ነበረበት ሲል የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
በተለያየ ደረጃ በሚገኙ በሺህዎቹ የሚቆጠሩ የአመራር አባላት ላይ ዕርምጃ መውሰዱን የኦሮምያ ገዢ ፓርቲ /ኦህዴድ/ አስታወቀ፡፡
ኢትዮጵያ የአባይን ውኃ ለልማት ስትጠቀም የግብፅንም ሆነ የሱዳን ፍላጎት እንደምትረዳና ድርሻቸውንም እንደምታከብር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታውቀዋል።
ከ2009 ዓ.ም ክረምት ጀምሮ በሙስና ተጠርጥረው የታሰሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን እና ሌሎች ግለሰቦች ለበርካታ ዜጎች የተሰጠውን የመፈታት ዕድል እንዲያገኙ ቤተሰቦቻቸው እየጠየቁ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ መነሳት በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር እየተወሰዱ ያሉ ሌሎች አውንታዊ ዕርምጃዎችን ተከትሎ የመጣ ነው ሲል በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርሱን ሥምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የደረሰበት ድምዳሜ ከኤርትራ ጋር ያለውን ውጥረት እንደሚያረግብ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ለሦስት ወራት ተጥሎ የቆየው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ዛሬ ተነስቷል፡፡
ለሁለት ቀናት ይካሄዳል የተባለ ስብሰባውን ዛሬ የጀመረው የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የአልጀርሱን ሥምምነትና የድንበር ኮሚሽኑን ውሣኔ ሙሉ በሙሉ ተቀብሎ ተግባራዊ ለማድረግ የደረሰበት ውሣኔ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉ ዓመታት ካንፀባረቀው አቋም የተለየ እንደሆነ የፖለቲካ ተንታኞች እየተናገሩ ነው።
የኢትዮጵያ ፓርላማ በነገው ዕለት በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ እንዲነሳ በሚኒስትሮች ምክር ቤት በቀረበው ሀሳብ ላይ ይወያያል።
ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ከጥላቻ ይልቅ ለአንድነት እና ለአብሮነት አውንታዊ አመለካከት ቦታ እንዲሰጡ ጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ ጥሪ አቀረቡ፡፡
መንግሥት በፖለቲካ ምክንያት የታሠሩ ዜጎችን መፍታት ያለበት በአንድ ጊዜና በአጠቃላይ ምህረት እንጂ ተራ በተራ አይደለም ሲሉ ዶክተር መረራ ጉዲና ተናገሩ።
ሰሞኑን የክስ መዝገባቸው እንዲቋረጥ ከተወሰነው 137 ግለሰቦች እና ድርጅቶች ውስጥ የግንቦት ሰባት ሊቀርመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጀዋር መሀመድ እንደዚሁም ኢሳት እና ኦኤምኤን ቴሌቪዥን እንደሚገኙበት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታውቋል፡፡
የደርግ መንግሥት የወደቀበትና ኢሕአዴግ ወደ ሥልጣን የመጣበት የግንቦት 20 በዓል 27ኛ ዓመት ዛሬ ተከብሯል።
ለሥድስት ወራት የቤት ክራይ ለመክፈል ቃል የገባልን የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥትና የአካባቢው አስተዳደር ከሁለት ወራት በኋላ ሜዳ ላይ በትኖናል ሲሉ ከሶማሌ ክልል ተፈናቅለው በቢሾፍቱ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች አማረሩ፡፡
ከኦሮምያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳኖ ወረዳ የተፈናቀለ አንድም የአማራ ክልል ተወላጅ አርሶ አደር የለም ሲሉ የአካባቢው ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ ትላንት ምሽት ፍንዳታ መድረሱን የዓይን እማኞች ለአሜሪካ ድምጽ ገልጸዋል።
በሳዑዲ አረቢያ ሰሞኑን ያደረጉት ጉብኝት ካሳካቸው ጉዳዮች አንዱ ሼህ መሐመድ ሁሴን አል-አሙዲን ለማስፈታት ጫፍ ላይ መደረሱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ አስታወቁ።
የዳንጎቴ ኩባንያ የኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅና በሁለት ኢትዮጵያውያን ባልደረቦቻቸው ላይ የተፈፀመው ግድያ እየተጣራ መሆኑን ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ አስታወቁ፡፡
"አቦይ ስብሃት" በሚል መጠሪያ የሚታወቁትን አንጋፋውን የሕውሓት መሥራች አቶ ስብሃት ነጋን ጨምሮ አምስት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በጡረታ እንዲያርፉ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት አስታወቋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ