አዲሱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አሕመድ ከግብፁ ፕሬዚዳት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ጋር በስልክ መወያየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ኦፊሴላዊ ሥራቸውን ትናንት በቃለ-መሃላ የጀመሩት አዲሱ የኢትዮጵያ መሪ ዶ/ር አብይ አሕመድ የመጀመሪያ እንግዳቸው የሆኑትን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪን ዛሬ በቢሯቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
ዛሬ ልዩ ስብሰባ ያካሄደው የኢትዮጵያ ፓርላማ አዲሱን የኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሰይሟል፡፡
አዲሱ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድ የፊታችን ሰኞ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከሚያደርጉት ንግግር ብዙ እንደሚጠበቅ፣ የቀድሞ የፓርላማ አባል አቶ ልደቱ አያሌው አስታወቁ፡፡
አዲሱ የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድ የፊታችን ሰኞ ጠዋት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ቃለ መሃላ እንደሚፈጽሙና፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ንግግር እንደሚያደርጉ ተገለፀ።
ዛሬ ስብሰባውን ያጠናቀቀው የኢህአዴግ ምክር ቤት የኦህዴዱን ዶ/ር አብይ አህመድን ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡
በመካሄድ ላይ ያለው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናትም ሊቀጥል እንደሚችል የገዥው ፓርቲ ምንጮች ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ አካባቢያዊ ጣልቃ ገብነት ወይንም እገዛ የሚፈገልግ አይደለም ይላሉ የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ማሁቡብ ማአሊም - የኢትዮጵያ ሁኔታ የሀገሪቱ መሪዎች ራሳቸው መፍትኄ እያፈለጉለት ያለ ጉዳይ ነው ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡
ቀጣዩን የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር የሚመርጠው የኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡
በጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ የሚገኘው ብቸኛ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዛሬ ትምህርት መዘጋቱንና አንዳንድ ተማሪዎችም በፀጥታ ኃይሎች መደብደባቸውን የዓይን እማኞች ገለፁ፡፡ ሁኔታው የተፈጠረው ተማሪዎቹ በሞያሌ የተገደሉ ሰዎችን ለማሰብ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት በማጣቱ ነው ብለዋል - እነዚሁ የዓይን እማኞች፡፡
የፓርቲውን ሊቀመንበር ብሎም የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመርጠው የኢህአዴግ ምክር ቤት በመጨው ሳምንት መጀመሪያ እንደሚሰበሰብ ተገለፀ፡፡
ዓለምቀፍ የሴቶች ታሪክ ወር በሚታሰብበት መጋቢት - የኢትዮጵያ ሴቶች ስለ ፆታ ዕኩልነት ይናገራሉ
ካለፈው ጥር እስከ መጭው ታኅሣስ ባለው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ቁጥራቸው ወደ ስምንት ሚሊየን የሚጠጋ ኢትዮጵያዊያን ሰብዓዊ ዕርዳታ እንደሚፈልጉ መንግሥትና አጋሮቹ አስታውቀዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቴለርሰን ያደረጉት ጉብኝት ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ያላትን አቋም ይበልጥ ያረጋገጠችበትና ግልፅ ያደረገችበት መሆኑን በአዲስ አበባ የሚገኙት አምባሳደር አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ላለው ችግር መልሱ "የበለጠ ነፃነት እንጂ መገደብ አይደለም" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን አስታውቀዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ግለሰቦች መኖራቸውን የኮማንድ ፖስት ማለትም የማዘዣ ዕፅ ጽ/ቤት ኃላፊ የመከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሳ አስታወቁ፡፡
በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣውና ለኢትዮጵያ ፓርላማ የቀረበው የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ፣ ዛሬ “ያልተለመደ” ከሚባል ሰፊ ተቃውሞ ጋር ፀድቋል፡፡
ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ ከ2007ቱ ምርጫ አንስቶ በሀገሪቱ የተካሄዱ ሂደቶች ድምር ውጤት ነው ይላሉ የፖለቲካ ተንታኞችና ተቃዋሚዎች።
የኦሮሚያ ገዥ ፓርቲ ኦህዴድ እና ተቃዋሚው ኦፌኮ ለመደራደር መወሰናቸውና በቅርቡ እየታዩ ያሉ ሌሎች ለውጦች ከሁለቱ ፓርቲዎች ግንኙነት የዘለለ ትርጉም እየተሰጣቸው ነው፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ