የጉራጌ ዞን ማዕከል የሆነችው የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች ያነሱት የልማት ጥያቄ ፖለቲካዊ ትርጉም እየተሰጠው ነው ሲሉ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ተናገሩ።
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁን በብርቱ በመቃወሙም ሆነ ያንን ይፋ በማድረጉ አቋሙ እንደሚፀና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡
ዛሬ ስብሰባውን ያጠናቀቀው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ ደመቀ መኮንንን ሊቀመንበር፣ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር በማድረግ በድጋሚ መርጧል፡፡
ኦህዴድ ዛሬ ያካሄደው የኃላፊነት ሽግሽግ የቀጠዩን የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ማንነት ያመላከተ እንደሆነ የሚገልፁ አስተያየቶች እየተሰጡ ነው፡፡
የጉራጌ ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ወልቂጤ ከሳምንት በፊት የተጀመረው አድማ እያበቃ ቢሆንም የታሰሩ አለመፈታታቸውን፣ ጥያቄዎችም አለመመለሳቸውን ነዋሪዎች ገለፁ፡፡
ኢትዮጵያ “ሰላማዊ ነች፤ ተቋማቷም ሥራቸውን ያለምንም ችግር እያከናወኑ ናቸው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ለውጭ ሃገሮች ዲፕሎማቶች ተናግረዋል። የአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አሿሿምም “በጣም በተሳለጠ ሁኔታ እየተካሄደ” መሆኑን ዶ/ር ወርቅነህ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ “ሰላማዊ ነች፤ ተቋማቷም ሥራቸውን ያለምንም ችግር እያከናወኑ ናቸው” ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ወርቅነህ ገበየሁ ለውጭ ሃገሮች ዲፕሎማቶች ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን እየገጠሟት ያሉ ፈተናዎች፣ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ሊፈቱ እንደማይችሉ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ስጋቷን እየገለጠች ነው።
የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ለስድስት ወራት ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስትር ሲራጅ ፈጌሣ ገለፁ። አዋጁ ለመጭዎቹ ስድስት ወራት ተግባራዊ ሆኖ የሚቆየው በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ እንደሚሆንና በሁሉም አካባቢዎች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ አመልክተዋል።
በዛሬው ዕለት ለጋዜጠኞች በተሰጠው ማብራሪያ፤ ዐዋጁ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ ለቀጣይ ስድስት ተግባራዊ ሆኖ እንደሚቆይ ታውቋል። ዐዋጁ በሁሉም የአካባቢው ክፍሎች እንደሚተገበርም ተናግረዋል።
ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ከአደጋ ለመጠበቅ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ መታወጁን የሚኒስትሮች ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
በወልቂጤ ከተማ የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ሁለት ወጣቶች በፀጥታ ኃይሎች ጥይት መገደላቸውን እና ሌሎችም መቁሰላቸውን የዓይን እማኞች አስታወቁ፡፡
እሥረኞችን መፍታት ለቀጣዩ እርምጃ በር ከፋች እንጂ ለሕዝቡ ጥያቄ መልስ አይደለም ይላሉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች፡፡ የሕዝቡ ዋንኛ ጥያቄዎች ግን እስካሁን አልተመለሱም ባይ ናቸው - የመኢአድና የሰማያዊ ፓርቲ መሪዎችን አነጋግረናል፡፡
በኦሮምያ እየተካሄደ ያለውን አድማ ተከትሎ ክልሉን አቋርጠው ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ ከተለያዩ ከተሞች የተነሱ ወደ ሥልሳ አውቶብሶች በደብረ ብርሃን ከተማ መቆማቸውን ትናንት ዘግበናል፡፡
ከመንግሥት ሰራተኞችና ከሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች እያገኙት ያለው ድጋፍ የሕዝቡ ትግል አንድ እርምጃ ወደ ፊት መሄዱን እንደሚያሳይ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል፡፡
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌንና አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ) ከእስር ለመፈታት የግንቦት ሰባት አባል መሆናቸውን አምነው የይቅርታ ፎርም ላይ እንዲፈርሙ መጠየቃቸውን ለቤተሰቦቻቸው ገለፁ። በሌላ በኩል በይቅርታ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው 417 ታራሚዎች ዝርዝር ለውሳኔ ወደ ሀገሪቱ ርዕሰ ብሄር መላኩን የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ምንጮች ገልፀዋል፡፡
በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአካሄደው ልዩ ስብሰባ አዳዲስ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አባላትን ሹመት አፅድቋል፡፡
ንግድና ኢንቨስትመንት ለአፍሪካ መፃዒ ዕጣ ያላቸውን አስፈላጊነት እንደሚረዱ የገለፁ የአፍሪካ መሪዎች ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ ሁኔታ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ጥረት እያፋጠኑ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ