የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን መሪዎች በሦስትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
ትላንት የተከፈተው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ አሁን ማማሻውን ተጠናቋል። በሙስና ላይ የሚካሄደውን ትግል በማሸናፍ ላይ እንደሚያተኩር የተገልፀው ይኸው ጉባዔ ሌሎች ውሳኔዎችም ይፋ ተደርገውበታል።
የደቡብ ሱዳን የሰላም ሂደትን በሚያደናቅፉ ላይ ማዕቀብ ለመጣል ጊዜው አሁን ነው ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ አስታወቁ፡፡ የሕብረቱ የመሪዎች ጉባዔ አዲስ አበባ ላይ ተከፍቷል፡፡
ሙስና በአፍሪካ ውስጥ እያስከተለ ያለው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ኢትዮጵያ በሊብያ የሚገኙ ዜጎቿን ወደ ሀገር መመለስ መጀመሯን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የዚህ ዓመቱ የመሪዎች ጉባዔ በሙስና ላይ ማተኮሩ ትግሉ አሁን ተጀመረ ማለት እንዳልሆነ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ አስታወቁ፡፡
አዲስ አበባ የተሰባሰቡ የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገሮች አምባሳደሮች ኮሚቴ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቅርብ አፍሪካ ላይ የሰነዘሩትን የሚያወግዝ ረቂቅ የአቋም መግለጫ አዘጋጅተዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ዓመታዊ ጉባዔ አዲስ አበባ ላይ ተከፍቷል፡፡
ኢትዮጵያን ከገባችበት ችግር ለማውጣት ኢህአዴግ ተጨማሪ ፓለቲካዊ ርምጃዎችን መውሰድ እንዳለበት ዶ/ር መረራ ጉዲና አሳሰቡ፡፡ ታሳሪዎችን ለመፍታት የተደረሰበትን ውሳኔ መነሻ አድርገው የተናገሩት ዶ/ር መረራ በዚች ሀገር ፓለቲካዊ ውሳኔ የሚያስፈልግበት ከዚህ የበለጠ አሳሳቢ ጊዜ የለም ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለይፋ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ መሪዎችንና ሌሎችም ታሣሪዎች ለመፍታት የደረሰበት ውሳኔ የሚያበረታታ የመጀመሪያ እርምጃ ነው ሲል በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ተናግሯል።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባወጣው የሀገራት የፀጥታ ሁኔታ ደረጃ ኢትዮጵያን የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ከሚያስፈልግባቸው ተርታ መድቧል፡፡
የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ባካሄደው ስብሰባ የውጭ ጉዲፈቻን የሚከለክል ሕግ አፅድቋል፡፡ በዚህም መሠረት የውጭ ሀገር ዜጎች ኢትዮጵያውያን ሕፃናትን በጉዲፈቻ መውሰድ አይችሉም፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ መሪዎችንና ሌሎችን ግለሰቦች ለመፍታት የደረሰበት ውሳኔ የሚያበረታታ ነው ሲል የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከፀጥታና ከጉብኝት አመቺነት አንፃር የዓለም ሀገሮችን በአራት ምድብ የሚያስቀምጥ አሠራር ይፋ ሊያደርግ ነው፡፡
ሰሞኑን የተጠናቀቀው የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ ከአመራሩ አንድነት አንፃር የነበሩ ችግሮች በጥልቀት የተዳሰሱበት እንደነበረ የግንባሩ አራት አባል ድርጅቶች ሊቃነ-መናብርት አስታወቁ፡፡
ገዥው ፓርቲ አህአዴግና መንግሥት የፖለቲካ መሪዎችና ግለሠቦች ያሏቸውን ለመፍታት የደረሱበት ውሳኔ መነሻ፣ ከሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር እያነጋገረ ነው፡፡
በአመራር ድክመት የተፈጠሩትን አደጋዎችና ሥጋቶች ለመቅረፍ በሚያስችል መግባባትና ስምምነት ግመገማውን ማጠናቀቁ የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አስታወቀ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ