ኢህአዴግ ሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ችግር ሊፈታ እንደማይችል አሳይቶናል ሲሉ አቶ ልደቱ አያሌው አስታወቁ፡፡
እየተካሄዱ ያሉ እሥራቶች ሰላማዊ የትግል እንቅስቃሴያቸውን እያወኩ መሆናቸውን የስልጤ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል አስታወቁ፡፡
በኅዳሴ ግድብ ላይ የሚደረጉ ውይይቶችን ወደፊት ለማራመድ የሚያስችል አዲስ ሃሣብ ማቅረባቸውን ኢትዮጵያ ውስጥ ጉብኝት ላይ ያሉት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰምሃ ሹክሪ አስታውቀዋል።
ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ የተወሰኑ አመራሮችን ከኃላፊነት ዝቅ እንዲሉ መወሰናቸውን የኢዴፓ ብሔራዊ ምክር ቤት አባላት አስታውቀዋል።
በኦሮምያና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ የበኩላቸውን እያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበርና ዓለምቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቀዋል፡፡
ከሁለት ዓመታት በፊት የተፈረመው የደቡብ ሱዳን የሰላም ሥምምነት እንዲተገበር የተቀናጀ ግፊት የሚያደርግ ስብሰባ ዛሬ በአፍሪካ ሕብረት ተጀምሯል፡፡
ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰሞኑን በምሥራቅና ምዕራብ ሐረርጌ እንደዚሁም በሌሎች አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ስለጠፋው ሕይወት ማዘናቸውን ገልፀዋል፡፡
ጨለንቆ ከተማ ላይ የተቃውሞ ስልፍ በማድረግ ላይ የነበሩት አሥራ አምስት ሰዎችን የገደሉ የሠራዊት አባላትና ትዕዛዝ የሰጡ ኃላፊዎች በሕግ እንዲጠየቁ የኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አሳሰብ። ግድያው መሣርያ ባልታጠቁ ሰዎች ላይ የተፈፀመ ወንጀል ነው ብለዋል የኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ አዲሱ አረጋ።
መሻሻል ባለባቸውና ልዩነት በፈጠሩ ጉዳዮች ላይ ሃገራቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በግል ስትወያይ መቆየቷን፣ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር አምባሳደር ዶናልድ ያማሞቶ ተናገሩ።
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት ሚኒስትር ዶናልድ ያማሞቶ ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር በአዲስ አበባ ተነጋግረዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የግብፅ ጉብኝት በታቀደው መሠረት እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በአፋር ክልል በጉብኝት ላይ የነበሩትን ጀርመናዊ ቱሪስት የገደሉትን ታጣቂዎች ማንነት ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈጠሩ ያሉ ቅሬታዎች እና ተቃውሞዎች ዋንኛ መነሻ ኢህአዴግና አጋሮቹ መቶ በመቶ ያሸነፉበት የ2007 ምርጫ ውጤት ነው - ይላሉ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ፡፡
መንግሥት በሀገሪቱ ለሚፈጠሩ ችግሮች እና ለሚነሱ ሕዝባዊ ጥያቄዎች በጊዜው መፍትሄ አይሰጥም ሲሉ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በሀገሪቱ የሚገኙትን ሃያ ሰባት ካምፖች በአሥር ዓመታት ውስጥ የሚዘጋ እና ስደተኞችም ከኅብረተሠቡ ጋር ተቀናጅተው እንዲኖሩ የሚያደርግ ዕቅድ ይፋ አድጓል፡፡
ተቃዋሚው የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢዴፓ/ ከገዥው ፓርቲ ጋር እየተካሄደ ያለውን ድርድር መነሻ ያደረገ የአመራር ውዝግብ ውስጥ ገብቷል።
ሕዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይ - ሕወሐት ሊቀመንበሩን ከሥልጣን አነሣ። አዜብ መስፍን ከማዕከላዊ ኮሚቴው ታገዱ።
የኅዳሴውን ግድብ አስመልክቶ ከግብጽ ጋር እየተካሄደ ያለው ውይይት አልተቋረጠም፣ የተፅዕኖ ጥናቱም እንደቀጠለ ነው ሲሉ የውሃ መስኖና ኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስትር አስታወቁ፡፡
በኦሮምያና በሶማሌ ክልል አዋሳኞች ወረዳዎች ሰሞኑን በተካሄዱ ግጭቶች የሰው ሕይወት መጥፋቱን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ