የኢትዮጵያ መንግሥት በዚምባቡዌ የሚደረግን የአመራር ለውጥ ከኮሎኔል መንግሥቱ ተላልፎ የመሰጠት ዕድል ጋር አያይዞ እንደማይመለከት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ በሰብዓዊ እርዳታና ልማት ዘርፍ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ እንደምትቀጥል አምባሳደር ማይክል ሬነር አስታወቁ፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት ኤችአር - 128ን በሀገሮቻችን መካከል ካለው የትኛውንም ዓይነት ትብብር እና ግንኙነት ጋር የሚያያዝ ጫና አላደረገም ሲሉ በአዲስ አበባ የሚኙት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ተናግረዋል፡፡
ቀደም ሲል በኦሮምያ በሶማሌ ድንበር በአለፉት ሳምንታት ደግሞ በተለያዩ ቦታዎች የተከሰተው ብጥብጥና ሁከት እንደሚያሳስባቸው በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ገለፁ፡፡
የትግራይ ጠገዴና የአማራ ጠገዴ በሚባሉ አዋሳኝ ወረዳዎች የነበሩ የወሰን ችግሮች፣ መፈታታቸውን የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሣለኝ የተመራው የኢትዮጵያ የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት ሰሞኑን ዝርዝር የሥራ ዕቅዱን ይፋ አድርጓል፡፡
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በቃታር ለሦስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ለማድረግ ዶሃ ገብተዋል። ሼኽ መሃመድ አል አሙዲ አልተፈቱም።
በኦህዴድና በሌሎች የኢህአዴግ አባል ፓርቲዎች መካከል ችግሮች ስለመኖራችው የሚወጡ ዘገባዎች የተሳሳቱ ናቸው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ።
ግጭት የነበረባቸው የኦሮሚያና የሶማሌ ክልል ድንበር አካባቢዎች ወደ ሰላምና መረጋጋት ተመልሰዋል ሲሉ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ተናገሩ፡፡
ባህር ዳር ላይ የተካሄደው የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች የምክክር መድረክ ከሁለቱ ክልሎች አልፎ የኢትዮጵያዊነት ጥንካሬ የተነገረበት የአንድነት አስፈላጊነት የተስተጋባበት መሆኑ ታይቷል፡፡
የኢትዮጵያ የምርጫ ሥርዓት አሁን ካለው የአብላጫ ድምፅ አሠራር ይልቅ ከተመጣጣኝ ውክልና ጋር የተቀየጠ ቢሆን መራጮች የሚሰጡት ድምፅ የበለጠ ዋጋ እንደሚኖረው የተቃዋሚ መሪዎች ተናግረዋል፡፡
በሕገወጥ ሰዎች ዝውውር ምክንያት ዛምቢያ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙት ዜጎቹ 1መቶ አሥራ ሥምንት መሆናቸውን የጠቆመው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲፈቱና ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ገዥው ኢህአዴግና በድርድሩ እየተሳተፉ ያሉ አብዛኛዎቹ ሀገርቀፍ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ የምርጫ ሥርዓት የሁለቱም ማለትም የአብላጫ ድምፅ እና የተመጣጣኙ ውክልና ሥርዓት ቅይጥ እንዲሆን ተስማምተዋል፡፡
በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ላይ ያለውን የካርቦን ልቀት መጠንና የኃይል አጠቃቀም የተመለከተ አውደ ጥናት ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡
ዓላማን በኃይል ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሰውን ፅንፈኝነትን በመዋጋት ረገድ ሀገራቸው ከአፍሪካ ጋር በአጋርነት እንደምትሰራ በአፍሪካ ሕብረት የዩናይትድ ስቴትስ ተልዕኮ ጉዳይ ፈፃሚ ጀሲካ ዴቪሲባ ተናገሩ፡፡
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሰሞኑን ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በአልሸባብ ላይ ከሚካሄደው ውጊያ አንፃር ይበልጥ ድጋፍ ለማግኘት ጭምር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቃል አቀባይ አስታውቀዋል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኒኪ ሄሊ በዛሬ የኢትዮጵያ ቆይታቸው በጋምቤላ በሚገኙ መጠለያዎች የሰፈሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ገብኝተዋል፡፡
በደቡብ ሱዳን የሰላም ጉዳይ ሁላችንም አንድ ድምፅ ሊኖረን ይገባል ሲሉ በተባበሩት መንግሥታት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኒኪ ሄሊ ተናገሩ፡፡
በአዲስ አበባ የተካሄደው የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሦስትዮሽ ስብሰባ በስኬት መጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በቅርቡ የተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎችን ተከትሎ ለተገደሉ ሰዎች ተጠያቂዎቹን የሚለይ ግልፅ ምርመራ እንደሚያስፈልግ በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡ መንግሥት ሀሳብን በነፃነት መግለፅን እንዲፈቅድ እናበረታታለን ሲል መግለጫው አመልክቷል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ