በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች በተከሰተው ግጭት የተሳተፉና ጉዳት ያደረሱ አካላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትር አስታወቁ፡፡
በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር የተጠረጠሩ ሠባ ኢትዮጵያውያን በዛምቢያ ሉሳካ መታሠራቸውን የሀገሪቱ መንግሥት አስታውቋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት /ዩኤስአይዲ/ በኢትዮጵያ ያለውን የእናቶች እና የሕፃናት ሞት ለመቀነስ ያለሙ መርኃ ግብሮችን ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡
በደቡብ ሱዳን ሰላም ላይ ለመነጋገር የምሥራቅ አፍሪካ ሃገሮች የጋራ ልማት ባለሥልጣን - ኢጋድ መሪዎች እዚያው ደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ ጁባ ላይ ስብሰባ ተቀምጠዋል።
በኢትዮጵያ የሁለት ቀን ጉብኝት ያደረጉት የዩናይትድ ስቴትስ ሴናተሮች ጄምስ ኤኖፍና ማይክል ኢንዚ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በእነዚህ ሁለት ቀናት በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች የተካሄዱ ሰላማዊ ሠልፎች መነሻ ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ወገኖች ጉዳይ ቢሆንም ከአለፈው ዓመት የቀጠሉ ብሶቶችም ተንፀባርቀዋል ይላሉ አንዳንድ ተሳታፊዎች፡፡
በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በሚገኙ የሐይማኖር ተቋማት መሪዎቻቸው በኩል በሁለቱ ሃገሮች መካከል ሰላም ለማምጣት ጥረት መጀመሩን የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት አስታወቋል፡፡
አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች እና የፌደሬሽን ምክር ቤት ሦስተኛ ዓመት የሥራ ዘመን የጋራ መክፈቻ ስብሰባ ዛሬ ተካሂዷል፡፡
ደቡብ ሱዳን ውስጥ ሰላም ለማስገኘት ማዕቀብ መፍትሄ ሊሆን አንደማይችል የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ያዘጋጁት በግብርና ላይ የተሰማሩ አፍሪካውያን ሴቶች የልምድ ልውውጥ መድረክ ዛሬ በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡
የዲቪ ሎተሪ ምዝገባ የፊታችን ማክሰኞ መስከረም 23 እንደሚጀመር በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታውቋል፡፡
የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ማምሻውን በደማቅ ሥነ ስርዓት ተከብሯል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ለአምስት ዓመታት 40ሚሊዮን ዶላር የተመደበለት የማኅበረሠብ አቀፍ የኤችአይቪ እንክብካቤ እና ሕክምና ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ይፋ አድርጓል፡፡
በኢትዮጵያ ሶማሌ እና ኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች ያለው ግጭት እንዳሳሰባት ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች፡፡
በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሞ አዋሳኝ ወረዳዎች የተከሰተውን ግጭት ለመካላከል መንግሥት እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ጠ/ሚኒስትር ኃይለማሪያም በግጭቱ እጁ ያለበት ግለሰብም ሆነ የፀጥታ ኃይል ተጠያቂ እንደሚሆንም በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ጠቅሰዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ አዋሳኝ ወረዳዎች በተነሳው ግጭት ከሞቃዲሾ የመጡ ኃይሎች ተሳትፈው እንደሆን የተጠየቀው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለግጭቱ ዝርዝር መናገር እንደማይቻል አስታውቋል፣ የሰው ሕይወት በማለፉ ግን ማዘኑን ገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ወረዳዎች የሚካሄደውን ግጭት ለማስቆም መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረቡ፡፡
እየተጠናቀቀ ያለውን የ2009 ዓ.ም. “አስቸጋሪ ዓመት ነበር" ሲሉ የገለፁት ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በአዲሱ የ2010 ዓ.ም ለውጥ ለማምጣት ሠላማዊ ትግላቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ