የበጎ ሰው ሽልማት ትናንት እሁድ ባካሄደው ሥነ ስርዓት የፌስቱላ መሥራች የሆኑትን ዶ/ር ካትሪን ሃምሊንን ጨምሮ የላቀ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አሥራ አንድ ሰዎች እውቅና ሰጥቷል፡፡
መንግሥትና ሌሎች አጋሮች ለምግብ ዋስትና ፕሮግራሞች የሚያደርጉትን ድጋፍ ማሳደግ እንዳለባቸው የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምቀር የተራድዖ ድርጅት /ዩኤስአይዲ/ አስተዳዳሪ አሳሰቡ፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ኮንግረስ እአአ ለ2018 በሚያፅድቀው በጀት ለሰብዓዊ ዕርዳታና የምግብ ዋስትና ጋር የተያዙ ፕሮግራሞች በቂ ገንዘብ እንደሚመድብ እርግጠኛ ነኝ ይላሉ፣ የዩኤስአይዲ አስተዳዳሪ ማርክ ግሪን፡፡
ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሰለኝ ጋር የተወያዩት የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ዩኤስአይዲ አስተዳዳሪ ማርክ ግሪን በድርቅ ለተጎዱ ኢትዮጵያውያን የሚሆን የ91 ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ ይፋ አድርገዋል።
ዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡና ከድኅነት እንዲወጡ ለማገዝ ለጀመረችው “የፊድ ዘ ፊውቸር ፕሮግራም” ለሁለተኛ ዙር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመረጠቻቸውን ሀገራት ይፋ አደረገች፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት /ዩኤስአይዲ/ አስተዳዳሪ ማርክ ግሪን ከነገ ጀምሮ የሁለት ቀናት የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ ያደርጋሉ፡፡
ቀጠዩ ዓመት ሌላ የድርቅ ዓመት እንደማይሆን ለመናገር ጊዜው ገና ነው ይላል የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኤጄንሲ፣ ዘንድሮን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ዓመታት የተከሰተው ድርቅ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን የእርዳታ ጥገኛ አድርጎ ቆይቷል፡፡
የተስተካከለው የቀን ገቢ ግምትም ቢሆን የተጋነነ ነው ያሉ አንዳንድ የደረጃ “ሐ” የቀን ግብር ከፋዮች ይግባኝ ማለታቸውን አስታወቁ፡፡
በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነው የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤትና የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው፡፡
ቁጥራቸው በ3 ሚሊዮን ለጨመረው ለኢትዮጵያ የድርቅ ተጎጂዎች፣ የሚፈለገው ዕርዳታ አጣዳፊ መሆኑንና አሁኑኑ መመጣት እንዳለበት የተበባሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
በአዲስ አበባ የተከበረው ዓለምቀፍ የሰብዓዊነት ቀን፣ ለኢትዮጵያ የድርቅ አደጋ ምላሽ በመስጠቱ ሥራ የተሰማሩ የዕርዳታ ሠራተኞች የተወደሱበት ሆኗል፡፡
መኢአድና ሰማያዊ አቅደውት የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ ያልተካሄደው፣ በራሳቸው በፓርቲዎቹ ምክንያት እንደሆነ የአዲስ አበባ አስተዳደር አስታወቀ፡፡ ፓርቲዎቹ ሕዝባዊ ስብሰባውን ለማካሄድ የሚያስፈልጉ የተለመዱ ሂደቶችን ተከታትለው፣ አላጠናቀቁም ነው ያለው፡፡
ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እንቅስቃሴ መጠንሰስ እና መጎልበት ግንባር ቀደሙን ሚና የተጫዎቱት አቶ ኃብተ ሥላሴ ታፈሰ የቀብር ሥነ ሥርዓት ትናንት በመንበረ ፀባዎት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡
በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት በትናንትናው ዕለት የጠሩት ሕዝባዊ ስብሰባ፣ በአዲስ አበባ አስተዳደር ምክንያት እንደተደናቀፈባቸው መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ አስታውቀዋል፡፡
በኢትዮጵያ ተከስቶ በቆየው ድርቅ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎች ቁጥር፣ ከ7.8 ሚሊዮን ወደ 8.5 ሚሊዮን ከፍ ብሏል፡፡
ሴት ተማሪዎችን ወደ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ እና ሂሳብ ዘርፎች ለመሳብና ለማነቃቃት፣ የተጀመረው የኮምፒዩተር ክህሎት ሥልጠና፣ ዓላማውን እያሳካ መሆኑን በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፓርላማ የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዲኤታ የአቶ አለማየሁ ጉጆን ያለመከሰስ መብት ማንሳቱና በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
"አዋጁ መታወጅም ሆነ ለአሥር ወራት መቆየት አልነበረበትም" - ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ
ተጨማሪ ይጫኑ