የሁለገቡ እና የአንጋፋው ባለ ተሰጠዖው የኪነጥበበ ሰው የአቶ ተስፋዬ ሣህሉ (የአባባ ተስፋዬ) አስከሬን ሽኝት ትናንት በመንበረ ፀባዖዎት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መካነ መቃብር ተፈፅሟል፡፡
ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ የሚሆን የ137 ሚሊዮን ዶላር ሰብዓዊ ዕርዳታ ዛሬ ይፋ አደረገች።
በሙስና ተጠርጥረው የታሠሩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሃብቶችና ደላሎች ቁጥር 42 መድረሱን የፌደራሉ ጠቅላይ ዋና አቃቤ ሕግ ጌታቸው አምባዬ አስታውቀዋል።
ሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰጠውን ተጨማሪ የአንድ ወር የእፎይታ ጊዜ እንዲጠቀሙና ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል፡፡
በሙስና ተጠርጥረው የተያዙ 37 የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ትናንት ፍ/ቤት መቅረባቸውን የሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል፡፡
ቤተ-እሥራኤላውያን፣ ራስ ተፈሪያን እና ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያደረጉ ሌሎች የውጭ ሀገር ዜጎች፣ የትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ እንዲሰጣቸው መወሰኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በሙስና የተጠረጠሩ ሠላሳ አራት የመንግሥት ባለሥልጣናትና የሥራ ኃላፊዎች እንደዚሁም ባለሃብቶችና በመሃል አሉ የተባሉ ደላሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።
የ2009ዓ.ም. የቀን ገቢ ግምት የተጋነነና ትርፍና ኪሳራችንን ግምት ያላስገባ ነው፤ ያሉ የአዲስ አበባ ግብር ከፋዮች ማማረራቸውን ቀጥለዋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ለሁለት የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪዎች የመታሠቢያ ሃውልት እንዲቆም መወሰኑ ለኢትዮጵያውያን ታላቅ ድል ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
29ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ለቀድሞ የኢትዮጵያ መሪዎች ለቀዳማዊ ኃይለሥላሴና ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የመታሰቢያ ሃውልት እንዲቆምላቸው መወሰኑ - ተገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ ከትናንት በስቲያ የተከፈተው ሃያ ዘጠነኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ተጠናቋል፡፡
በአንዳንድ ሀገራት ያሉ የሰላምና የፀጥታ ጉዳዮች አሳሳቢ መሆናቸውን ቀጥለዋ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ተናገሩ፡፡
አፍሪካ በዓለምቀፍ መድረኮች ያላት ተቀባይነት መጨመሩ አህጉሪቱ በአንድ ድምፅ የመናገሯን አስፈላጊነት እንደሚያጎላው የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ተናገሩ፡፡
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገር ውስጥ ላሉ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ውሃ፣ መብራትና ስልክ የመሳሰሉ ክፍያዎችን በቀጥታ መክፈል እንዲችሉ የሚያስችላቸው አገልግሎት ሊጀምር ነው፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያሉ ኩባንያዎች ስኬታማ አይሆኑም የሚለውን አስተሳሰብ አሸንፏል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ተናገሩ፡፡
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም የሚያስጠብቅ ረቂቅ ዓዋጅ አዘጋጀ፡፡
በሣምንቱ መጨረሻ በአዲስ አበባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አዳራሽ የሚያደርጉትን ውይይት ያጠናቀቁት ገዢው ኢሕአዴግና አስራ ስድሥት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ዋናውን ድርድር ለመጀመር ወስነዋል።
ደቡብ ሱዳን ውስጥ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፕ ግራንዲ አሳሰቡ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ