የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት ለአህጉራዊው ድርጅት መዋጮ የሚደርጉበት አሰራር ለመተግባር ተጠየቀ።
"ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ቀደም የነበረውን ያህል ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር አይደለችም ያሉት" የአፍሪካ ኅብረት ኢኮኖሚ ኮሚሽነር ፕሬዚዳንት ትራምፕ የነበረውን የኢኮኖሚ ትብብር ባይቀጥሉ እንኳን አፍሪካ ሌሎች አማራጮች እንዳሏት ተናግረዋል።
ከጥር 14 / 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በጋሞ ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ታስረው የነበሩ 13 አመራሮቹና አባላቱ ትናንት ምሽት ላይ መፈታታቸውን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/ አስታውቋል።
ሦስት ከፍተኛ አመራሮቹን ጨምሮ 13 ሰዎች በጋሞ ጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ መታሰራቸውን የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት(መኢአድ) አስታወቀ።
በኢትዮጵያም ሆነ በሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች የውጭ ፖሊሲዎችና ምንነታቸውን በማሣወቅ ላይ ክፍተት መኖሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አስታውቀዋል።
በጎርፍ አደጋና አዲስ ባጋጠመ ድርቅ ምክንያት 5.6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው መንግሥትና አጋሮቹ ይፋ አደረጉ።
ልክ የዛሬ ሣምንት ዶናልድ ትራምፕ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት በመሆን ቃለ መሓላ ይፈጽማሉ። አዲሱ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ላይ የሚከተሉት ፖሊስ ከተሰናባቹ ፕሬዚዳንት አንድ ሊሆን እንደሚችል የቀድሞ የፓርላማ አባላትና የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ይናገራሉ።
በኢትዮጵያ ተከስቶ የነብረው አለመረጋጋት በአገሪቱ ጠንካራ ሥርአት መኖሩ የታየበት አጋጣሚ መፍጠሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለፓርላማ አባላት በሰጡት ማብራርያ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ መፈጠር ስላለበት እርቀ ሰላም ለሁለት ቀናት የመከረው የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የተነሱ ሃሳቦችን ለመንግሥት ለማቅረብ በመስማማት ዛሬ ማምሻውን ተጠናቋል።
ተፈጥሮ የነበረው አለመረጋጋት ሰከን ያለ ቢመስልም ለዘላቂ መፍትሄ ግን እርቀ ሰላም እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታወቀ።
የኢትዮ ጅቡቲ የምድር ባቡር ፕሮጀክት አካል የሆነው የደዋሌ ጅቡቲ የምድር ባቡር ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተቀስቅሰው ከቆዩ ተቃውሞዎች ጋር በተያያዘ በአሥር ሺኾች የሚቆጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መቆየታቸውን፣ መንግሥቱ የአስተዳደር ማሻሻያ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን፣ እንደ ግብፅ ካሉ መንግሥታት ጋር ውይይት መጀመሩን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ክርስቲያኖችና በዓለም ዙሪያ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማንያን የገናን በዓል ዛሬ አክብረው ውለዋል።
በዩናይትድ ስቴትስ የሚደረግ የመሪዎች መተካካት ሀገሪቱ በኢትዮጵያ ላይ ከምትከተለው ፖሊሲ አንርፃ ለውጥ አምጥቶ እንደማያውቅ አንድ አንጋፋ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ተናግረዋል።
የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት አቶ ለማ መገርሳ የተቀመጡ መስፈርቶችን ላሟሉና በፈጸሙት ወንጀል ለተፀፀቱ አስር ሺሕ የሕግ ታራሚዎች ይቅርታ አደረጉ።
ኢትዮጵያዊ የመካከለኛ ርቀት የኦሎምፒክ ጀግና የሻምበል ምሩፅ ይፍጠር የቀብር ሥነ ስርዓት ትላንት በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።
በአትሌቲክሱ የረዥም ርቀት ሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያን በበርካታ ዓለምቀፍ መድረኮች በበላይነት ያስጠራው ዝነኛው አትሌት ምሩፅ ይፍጠር በ72 ዓመት ዕድሜው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ የቀብር ሥነ ስርዓቱ አዲስ አበባ በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈፅሟል።
ተጨማሪ ይጫኑ