በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለማስቆም ያለሙ የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች በስፋት መካሄድ እንዳለባቸው ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ አስተያየታቸውን የሰጡት ወጣት ተማሪዎች ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ የአስተዳደር መሥሪያ ቤቶች በተፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች የተጠረጠሩ 125 ግለሰቦችን በቁጥር ስር ማውሉንና ጉዳያቸውን እያጠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
በሁከትና ብጥብጥ ተጠርጥረው የተያዙ ከ12 ሺሕ በላይ የሚሆኑ ዜጎች የተሀድሶ ስልጠና እንደሚሰጣቸው የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ወደ አዲሱ የፈረንጆች አመት የምትሸጋገረው ኤል ኒኖ ያስከተለውን ድርቅ ተቋቋማ ባለፈችበትና በሀገሪቱ የተፈጠረው ሁከት በተረጋጋበት ሰዓት መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
ሰዎች የኤችአይቪ ምርመራ እንዲያደርጉና ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ ከተገኝም መድሃኒት እንዲጀምሩ፤ ኤችአይቪ/ኤድስን ለመዋጋትም የበለጠ ንቅናቄና የፖለቲካ ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ዩኤሰኤአይዲ አሳስቧል፡፡
ከኦሮሚያና ከአማራ ክልሎች በሁከት ተጠርጥረው የተያዙ ወደ አምስት ሺሕ የሚጠጉ ተጠርጣሪዎች የተሃድሶ ሥልጠና ወስደው መለቀቃቸው ተገለፀ፡፡
1870 ሜጋ ዋት ኃይል የሚያመነጨው ጊቤ ሦስት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ዛሬ ተመረቀ።
በፕሬዚዳንቱ የአስቸኳይ ጊዜ የኤድስ እርዳታ ፔፍ ፋርም አማካኝነት ከዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እየተደረገ ያለው ድጋፍ የኤች አይ ቪን ስርጭት ለመቀነስ ያገዘ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡
“ሰዎች በሚሉት ጋር ላትስማማ ትችላለህ፤ ማለት የሚፈልጉትን ነገር የማለት መብታቸውን ግን ልታከብር ይገባል” በኢትዮጵያ የአሜካ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ኒኮላስ ባርኔት ናቸው ይህንን ያሉት።
በዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ድጋፍ የሚካሄዱ የፀረ ኤችአይቪ/ኤድስ ፕሮጄክቶች ከፍተኛ ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን ድሬዳዋ የሚኖሩ ተጠቃሚዎች ተናግረዋል።
የኢትዮጵያዊነት መንፈስ በሁላችንም ልብ ውስጥ ሊሰርፅ ይገባል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጥሪ አቅርቡ፡፡
የዶ/ር መረራ ጉዲናን መታሠር በተመለከተ የተሻለው አማራጭ ፖለቲካዊ መፍትሔ መሆኑን የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎችና የቀድሞ የፓርላማ አባላት አሳስበዋል።
ዶ/ር መረራ ጉዲና የታሠሩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ክልከላ በመተላለፋቸው መሆኑን የገለፁት የመንግሥቱ ቃል አቀባይ ተጨማሪ መረጃ በሂደት ሊገኝ የቻለው ከሕግ አካላት ወይንም ከማዘዣ ጣቢያው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ሠሞኑን የሚከበረውን ዓለምአቀፍ የኤድስ ቀን በማስመልከት እየወጡ ያሉ መረጃዎች ለፀረ - ኤች አይ ቪ ዘመቻ የሚሠጠው ትኩረት እንዲቀጥል እያሳሰቡ ነው፡፡
በመጭው እሁድ የአዲስ አበባው የኢትዮ - ኩባው ወዳጅነት አደባባይ የሚካሄደው ሥነ ስርዓት “ካስትሮና ሀገራቸው፤ የዋሉልንን ውለታ የምናሳውቀበት ነው” ሲሉ በኩባ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ተናግረዋል፡፡
በ1970ዎቹ በኩባ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ለፊዳል ካስትሮ የመታሠቢያ ሥነስርዓት ለማካሄድ ኮሚቴ አቋቁመው እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡
“በአስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን የቆሙ” ሲሉ ፊደል ካስትሮን የጠሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ በኩባው መሪ በኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያን የአየር ክልል በመጣሳቸው በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩት ሃያ አይሮፕላኖችና አብራሪዎቻቸው በመንግሥት ውሣኔ ጉዟቸውን እንዲቀጥሉ መደረጉን የሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡
የአማራ ክልል ምክር ቤት ለሦስት ቀናት ያካሄደውን ጉባኤ ሲያጠናቅቅ አሥር ነባርና አሥራ ሁለት አዳዲስ ተሿሚዎች የተካተቱበት ካቢኔ ይፋ አድርጓል።
ተጨማሪ ይጫኑ