መጀመሪያ ፍርሃት የነበረ ቢሆንም 16ኛው ታላቁ ሩጫ ውድድር በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ኃይሌ ገ/ሥላሴ አስታወቀ፡፡
በነገው ዕለት በአዲስ አበባ በሚካሄደው 16ኛው ታላቁ ሩጫ 42 ሺሕ ሰዎች እንደሚሳተፉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።
“በሀገሪቱ የሚወጡ አዋጆች ከማዕከል ርቆ በሚገኘው ወገናችን በትክክል አይተገበርም” ሲሉ የኦሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ኅብረት ሊቀ መንበር ተናግረዋል።
አፍሪካ በዩናይትድ ስቴትስ እየተካሄደ ባለው ሠላማዊ የሥልጣን ሽግግር ብዙ መማር እንዳለባት ኢትዮጵያውያን አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡
በሕግ የበላይነት እና በሠብዓዊ መብት አያያዝ ላይ መሻሻል እንዲኖር እንደሚፈልጉ ከኢትዮጵያ መሪዎች ጋር የተወያዩት የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስቴፈን ዲዮን አስታወቁ።
የዩናይትድ ስቴትስ ምርጫ ተጠናቋል ዶናልድ ትራምፕም የአሜሪካ 45ኛው ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ዛሬ ከማለዳው አስራ ሁለት ሰዓት ጅምሮ አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ባዘጋጀው የምርጫ ቀን ቁርስ ላይ ነው አስተያየታቸውን የሰጡት
“ፕሬዚዳንቱ ከየትኛውም ይመረጥ በአፍሪካ ከሚከተሉት ፖሊሲ አንፃር መሠረታዊ ለውጥ አያመጣም” የፖለቲካ ሣይንስ መምህር
ዲፕሎማቶች “ለራሳቸው ደህንነት” ሲባል ከአዲስ አበባ 40ኪሎ ሜትር ራዲዮስ ውጭ ያለፈቃድ እንዳይንቀሳቀሱ የተጣለው ክልከላ መነሳቱን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ፡፡
ዶናልድ ትራምፕ ከስደተኞች አንፃር የሚከተሉት ፖሊሲ እንደሚያሳስባቸው የገለፁት ቬኦኤ ያነገራቸው ኢትዮጵያውያን አስተያየት ሰጭዎች ነገ በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ሂላሪ ክሊንተን ማሸናፋቸውን እንደሚመርጡ ገልፀዋል፡፡
በኢህአዴግና በአጋሮቹ ብቻ የተያዘው የኢትዮጵያ ፓርላማ ከቀጣዩ ሀገርአቀፍ ምርጫ በፊት መስተካከል እንዳለበት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ተናገሩ።
”ሮጬ ወርቅ አምጥቼአለሁ፤ ፌዴሬሽኑን በመምራት ደግሞ ወርቅ እንዴት እንደሚመጣ አሳያለሁ” ብሏል ኃይሌ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገር።
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ሃያ አዳዲስ ሹመቶች የተካተቱበት የካቢኔ ሹም ሽር ዛሬ ይፋ አድረገዋል፡፡ በዚህም መሠረት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የወጭ ጉዳይ ሚኒስተር ሆነው ተሹመዋል፡፡
በኢትዮጵያ "የምርጫ ሥርዓት ማሻሻል ብቻውን የተሻለ የፓርቲዎች ውክልና ሊያመጣ አይችልም" ሲሉ የኢትዮጵያ ፓርላማ የቀድሞ አባልና የፓን-አፍሪካ ፓርላማ የክብር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ ተናግረዋል።
አፍሪካ አሁን ካለው ጥራት የሌለው የኢኮኖሚ ዕድገት በመውጣት ጥልቀት ያለው ለውጥ ማምጣት እንዳለባት ተሰናባቹ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ጸሃፊ ካርሎስ ሎፔዝ አስታወቁ፡፡
"ሰሞኑን ይፋ የተደረገው አዲስ ካቢኔ የህዝቡን ፍላጎት ሊያረካ የሚችል፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄን የሚመልስና የመንግሥትን የማስፈፀም አቅም የሚያሳድግ ነው” ሲል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ፡፡
በኦሮሚያ ክልል ቀደም ሲል በተነሱት የክልሉ አመራሮች ምትክ አዲስ መሾማቸው ታውቋል።
ድኅነትን የመቀነስ የሚሌኒየሙን የልማት ግብ ካሳኩት ሀገሮች መካከል ኢትዮጵያ አልተጠቀሰችም፡፡
የአፍሪካ ሀገሮች የውስጥ ተፈናቃይ ዜጎቻቸውን በተመለከተ የተዘጋጀውን የካምፓላ ስምምነት ማፅደቅና ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የዓለም አቀፍ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ፕሬዚዳንት አስታውቀዋል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዘዳንታዊ ምርጫ በሌላው የዓለም አካባቢ ትኩረት እንደሚስብ የተናገሩት፥ የህዝብ ግንኙነትና የፖለቲካ ስልት ባለሞያ፥ ተሞክሯቸውን ለኢትዮጵያውያን አካፍለዋል። የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን በምርጫው ሂደት የሚጫወቱት ሚና ከፍተኛ መሆኑን ያስረዱት ኪቲ ከርት በፕሬዘዳንታዊ እጩዎቹ የሚወጡና የሚነገሩ መረጃዎችን የማጣራት ሥራ እንደሚሠሩም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ውይይትና የሃሳብ ልውውጥ እንዲኖር፣ የተለያዩ ድምጾችም እንዲደመጡ ለማድረግ መስራት እንዳለባት፤ የጀርመንዋ ቻንስለር አንገላ መልከር ተናገሩ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ