የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ያስፈለገው፣ ከተቃውሞ ሰልፎች ጋር በተያያዘ ሳይሆን፤ ከተለያዩ አቅጣጫዎች እየመጣ ባለው እና በሀገሪቱ ላይ በተደቀነው ስጋት ምክንያት መሆኑን፣ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡
በሃገሪቱ "ያንዣበበውን አደጋ ለመቀልበስ" በሚል የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለስድስት ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማወጁን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ።
በአገሪቱ ለተፈጠረው የፖለቲካ ችግር መፍትሄ ለማስገኘት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አስታውቋል።
ማንኛውም ክፍል ከምንም ነገር በላይ ለሰው ህይዎት ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አሳሰበ።
በቢሾፍቱ የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ በርካቶች መሞታቸውን ተከተሎ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ በኦሮሚያ ከተሞችና በዋና ከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ከሰኞ ማታ ጀምሮ መካሄዱን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አስታውቋል።
በቢሾፍቱ የኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ለሞቱት ሰዎች ኀዘናቸውን የገለፁት ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሁኔታው በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጠይቀዋል።
በቢሸፍቱ የእሬቻ በዓል አከባበር ላይ የሞቱ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ መሆኑን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አሰታወቀ።
በቢሾፍቱ የእሬቻ በዓል አከባበር ወቅት በተፈጠረው ሁከትና ትርምስ ውስጥ የጠፋው ሕይወት ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የዐይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
የእሬቻ በዓል የሕዝብ መሆኑን ያስታወቀው የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ የማንም ጣልቃ ገብነት አያስፈልገውም ብሏል።
ከደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ስደተኞች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ ተጨማሪ ካምፕ ለማቋቋም እየሰራ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ባለፉት ሁለት ዓመታት ከፍተኛ እድገት ያስመዘገበው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት መቀነስ እንደሚያሳይ የአፍሪካ ልማት ባንክ እና የተመድ የልማት ፕሮግራም ትንበያ አመለከተ።
የፊታችን ዕሁድ፤ መስከረም 22 በኦሮሞ ማኅበረሰብ የሚከበረው የእሬቻ በዓል ያለጣልቃገብነት ሕዝባዊ በዓል ሆኖ እንዲከበር ተቃዋሚው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ - ኦፌኮ ጥሪ አስተላልፏል።
በተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት እየተነሱ ያሉ የህዝብ ጥያቄዎች ለመንግሥትና ለሚመለከታቸው አካላት የሚያቀርብ ኮሚቴ እየተቋቋመ መሆኑን ተገለጸ።
"በቅዱስ ሲኖዶስና ጎንደር ባሉት የሃይማኖት መሪዎች መካከል ልዩነት ስለመፈጠሩም የምናውቀው ነገር የለም"የቅዱስ ፓትሪያርኩ ልዩ ፀሃፊው አባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል
ሞሮኮ ወደ አፍሪካ ህብረት አባልነት ለመመለስ ይፋ ጥያቄ ማቅረቧ ተገለጸ።
በተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ወቅት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች መጣራት ያለባቸው ገለልተኛ በሆነ የአገር ውስጥ ወይም የውጭ አካል መሆኑን ተቃዋሚዎች እያሳሰቡ ነው።
ከፓርቲው ኃላፊነት የተነሱት የኦህዴድ ሊቀ-መንበር አቶ ሙኽታር ከድር እና ምክትላቸው ወ/ሮ አስቴር ማሞ በሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልነት እንደሚቀጥሉ ተገለጸ።
በፌደራሉ መንግስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ወ/ሮ አስቴር ማሞና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙክታር ከድር ከያዙት የፓርቲ ኃላፊነት ተነስተዋል። እስከአሁን በነበረው የኢህአዴግ ልምድ ከተካሄደ፣ከፌደራልና ከክልል መንግስት ስልጣናቸውም ሊነሱ ይችላሉ።
የፀጥታ ኃይሎች ጨዋ የሆነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ይተኩሳሉ፣ ይገድላሉ ያሉት ተቃዋሚዎች ተጠያቂዎቹም የመንግሥት የፖለቲካ መሪዎች እንደሆኑ አስታውቀዋል።
ተጨማሪ ይጫኑ