በአማራ ክልል በደብረማርቆስ ከተማ ለተቃውሞ የወጣ ሕዝብ፣ በፀጥታ ኃይሎች ከፍተኛ ድብደባ እየተፈጸመበት መሆኑን ነዋሪዎቹ ተናገሩ።
በአገሪቱ ሕልውና ላይ ያንዣበበውን ከፍተኛ አደጋ ለመከላከል ሁሉም ወገን በኃላፊነት እንዲቀሳቀስ የኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)ጥሪ አቀረበ።
በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር በመጠኑ መቀነሱን መንግሥትና አጋሮቹ አስታወቁ ።
የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴ አባላትና በግርግሩ ወቅት የታሠሩ ሁሉ ይፈቱ ሲል የመላ ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጥሪ አቅርቧል።
በአዲስ አበባ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ስናገለግል የቆየን ከ600 በላይ ሠራተኞች ከምደባ ውጭ ሆነናል ከሥራ ተባረናል ሲሉ ቅሬታ አቅራቢዎች ገለጹ።
መንግሥት ኃላፊነቱን ሊገነዘብና የማስተካከያ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ሲሉ የኦሮሞ ፈደራሊስት ኮንግረስ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ጥሩነህ ገምታ አሳስበዋል፡፡
የኢጋድ አባላትና የሌሎችም አገሮች መሪዎች ለደቡብ ሱዳን ችግር እልባት ለመስጠት በአዲስ አበባ ስብሰባ በማካሄድ ላይ ናቸው።
የአጣዳፊ ትውከትና ተቅማጥ በሽታ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ ወደ ክልሎችም መስፋፋቱን መንግሥት አስታውቋል።
የደቡብ ሱዳን የእርሻና የተፈጥሮ ኃብት ሚኒስትር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶ/ር ላም አኮል ሥልጣናቸውን መልቀቃቸውን አስታውቀዋል።
በየአከባቢው የሚሰበሰበው ቆሻሻ በፍጥነት ባለመነሣቱ የጤና ስጋት እየሆነባቸው መሆኑን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች አማረሩ።
የኢትዮጵያ ፓርላማ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ሳይጠናቀቁ የቆዩ የተለያዩ አዋጆችን መርምሮ አጽድቋል።
በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ብቻ ለስድስት ሚሊዮን ሰዎች የኤችኣይቪ ምርመራ ለማካሄድ ያለመ ዘመቻ ዛሬ በኢትዮጵያ ይፋ ተደርጓል።
የዓመቱን ሥራ አጠናቆ ለእረፍት ከተበተነ ሦስት ሳምንት ያልሞላው የኢትዮጵያ ምክርቤት ለአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርቷል።
ያለ በቂ ምክንያትና ያለ በቂ ማስጠንቀቂያ ቤታችን እንዲፈርስ በመደረጉ በዚህ የክረምት ወቅት መጠለያ አጥተን እንድንበታተን ተደርገናል ሲሉ በአዳማ ከተማ የቦኩ ሸነን አካባቢ ነዋሪዎች እያማረሩ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምሕርት መግቢያ ፈተና መንግሥት የማኅበራዊ መገናኛ ድረ ገፆችን ከዘጋ በኋላ ተጀምሯል። እየተናፈሱ ያሉ ውዥንብሮችን ለመግታት ሲባል የማኅበራዊ ድረ-ገፆች እንዲዘጉ መወሰኑን መንግሥት አስታውቋል። እርምጃው በተጠቃሚው ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል። አንዳንድ ተማሪዎች ግን በአዎንታዊ ጎኑ ተመልክተውታል።
የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ የኢትዮጵያ ጉብኝት ከኤርትራ ጉዳይ ሆነ ከሌሎች ወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ግንኙነት የለውም ሲሉ አዲስ አበባ የሚገኙት የእሥራኤል አምባሳደር ተናግረዋል።
ታሪካዊ የተባለ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የሚገኙት የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታንያሁ በአገራቸው እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ጊዜው አሁን መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያን የ2008 ዓ.ም የምጣኔ ኃብት ዕድገት ትንበያ በተመለከተ መንግሥታቸውና በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) መካከል የተቀራረቡ ግምቶች መኖራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ አስታውቀዋል።
ለ2009 ዓ.ም የበጀት ዓመት 274 ቢሊዮን ብር መፅደቁን የኢትዮጵያ የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ