በኦሮምያና በአማራ ክልሎች ተፈፅመዋል የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን የተመለከተ ሪፖርት ከሁለት ሣምንታት በኋላ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚያቀርብ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሺን አስታወቀ።
አገሮች ፎረሙ የመነጩ ሃሳቦችን እየተጠቀሙ ነዉ ተባለ
ችግሩ የሚታወቅ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሣ እልባት ለመስጠትም የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነዉ ብለዋል።
መመሪያዎች መዉጣት የነበረባቸዉ በመስሪያ ቤት ጠረጴዛዎች ሳይሆን ከተጠቃሚዉ ሕብረተሰብ ጋር በሚደረግ ዉይይት ነዉ ብለዋል።
በኦሮሚያም ሆነ በሌሎች የሃገሪቱ ክልልች ለተፈጠረው የሕዝብ ቅሬታ፥ መንግሥታቸውና ፓርቲያቸው ሙሉ ኃላፊነት እንደሚወስዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ።
ኢትዮጵያውያን ቡና አምራቾችና ላኪዎች በአዲስ አበባ የተካሄደው ዓለምአቀፍ የቡና ጉበዔ ጉዳዩ ትኩረት እንዲያገኝ መነሻ ሊሆን እንደሚችልም ለአሜሪካ ድምጽ አስረድተዋል።
በሥራና በሃላፊነት ቦታዎች ተመጣጣኝ የጾታ ዉክልና እንዲኖር ለማድረግ የሚወጡ ሕጎች ብቻቸዉን ዉጤት ማምጣት አይችሉም ሲሉ የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ዶክተር ዲላሚኒ ዙማ ተናገሩ።
የኦሮምያ ክልል ገዢ ፓርቲ ኦሕዴድ እስካሁን የሰጠው ይፋ መግለጫም ሆነ ማረጋገጫ የለም።
ሪፖርተር ጋዜጣ በዛሬው እትሙ እንዳለው ከሃላፊነት የተነሱት፣ የኦሄዴድ አስፈጻሚና የኦሮሚያ ገዢ ፓርቲ የሆነው የኦሮሞ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ እና የክልሉ አስተዳደር እና ጸጥታ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰሎሞን ኩቹ ናቸው።
እንደነሱ እምነት ደንቡ የተዘጋጀው በቢሮና በአደራሽ ውስጥ ስብሰባ እንጂ የአሽከርካሪዎችን የየእለት ተመክሮዎች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት አይደለም።
ወደ ሀገራቸው የተመለሱት ኢትዮጵያውያን ስንት እንደሆኑ መረጃውን ያሰራጨው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አላብራራም።
ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡት ወታደሮች እስካሁን ባለው ጊዜ ሲንቀሳቀሱ የነበረው በተናጠልና በየተመደቡባቸው አከባቢዎች እንደነበር የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ልዩ ልዑክ አምባሳደር ብርሀነ ገብረ-ክርስቶስ ተናግረዋል።
የዓለም የጤና ድርጅት ባለሥልጣናት በበኩላቸው፥ የዚካ ቫይረስ በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊት፥ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
“ኢቦላን እንዴት መቆጣጠር እንዳለን እናውቃለን። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ከምዕራብ አፍሪቃ አገሮች ጋር በመሥራት ለሥኬት የበቃ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል። ይህ ባይሆን ዓለም አቀፍ ቀውስ ይሆን ይችል ነበር። ዚካን በተመለከተ ግን ሳይንቲስቶች ክትባት ለማግኘት ተግተው እየሰሩ ነው። እስከ ሁለት ዓመት የሚደርስ ጊዜ ሊጠይቅ ይችላል።” ዶ/ር ቶማስ ፍሪዳን የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታዎች መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዲሬክተር።
በአፍሪቃ ከሚከሰተዉ የማጅራት ገትር በሽታ ዘጠና ከመቶዉን የሚሸፍነዉን ዓይነት ወደ ማስወገድ መቃረባቸዉን የዓለም ጤና ድርጅትና ፓዝ ኢንተርናሽናል (PATH INT.) አስታወቁ።
ከወልቃይት አካባቢ እየተነሣ ላለው የማንነት ጥያቄ መንግሥት ሰላማዊ ምላሽ መስጠት እንዳለበት የመድረክና የአረና ትግራይ አመራር አባላት አሳስበዋል፡፡
ሕገ-መንግሥታዊ መብታችን በኢሕአዴግ መንግሥት እየተጣሰ ነው ሲል መድረክ አማረረ። የፓርቲው መሪዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሕጋዊና የሰላማዊ ትግል መንገዶች እየተዘጉ ነው ብለዋል።
”ንጽህናና ውሃ ለሁሉም”የተሰኘ ከአንድ ወር በኋላ በአዲስ አበባ የሚካሄድ ዓለም አቀፍ ጉባዔ።
ጥናቱን እንዲያካሄዱ የተመረጡት 2 የፈረንሳይ ኩባንያዎች የቀረበዉ የሥራ መዘርዘርና የሚፈረመዉ ዉል በሦስቱ አገሮች የቴክኒክ ኮሚቴዎች እየታየ መሆኑንም ነዉ ሚኒስትሩ የጠቀሱት።
የትላንት ሥነ-ሥርዓቱ፥ ሰማእቱ አርበኛ የብጹእ አቡነ ጴጥሮስ የተዘከሩበትን አጋጣሚ ፈጥሯል።
ተጨማሪ ይጫኑ