በኬንያ የሚገኙ ስደተኞች የኬንያ መንግሥት በሀገሪቱ የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ ላይ በይበልጥ እንዲያሳትፋቸው ጠየቁ።
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ውስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች በክልሉ አስተዳደራዊ በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ተናገሩ።
የኬንያ ሲቪል ማኅበራትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዛሬ በናይሮቢ በኬንያ ሙስና ተንሰራፍተዋል ሲሉ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ።
ከሞያሌ ተሰደው ኬንያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በምግብ እጥረት እየተቸገሩ መሆናቸውን ተናገሩ።
የኬንያዉ ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ በኮምፒዩተርና በኢተርኔት አማካኝነት የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቆጣጠር የሳይበር ደህንነት ዐዋጅ አፀደቁ። ዐዋጁ ተጨባጭ ያልሆነ መረጃ’ን የሚያሰራጩ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶችን 5 ሚሊዮን የኬንያ ሺሊንግ ወይም ሁለት ዓመት እሥራት እንደሚቀጡ ይደነግጋል።
በሞያሌ ከተማ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በከተማዋ ያሉትን የኦሮምያንና የሶማሌ ክልልን የፀጥታ ኃይሎች ትጥቅ ማስፈታቱ ታውቋል።
ትላንት ረፋድ በሞያሌ በከሰተዉ ግጭት ስምንት ሰዎች እንደሞቱና ከአርባ በላይ እንደቆሰሉ የሞያሌ ሆስፒታል ገለፀ። በሆስፒታሉ የውስጥ ዶክተር የሆኑ ዶ/ር ንጉሱ አዱኛ እንደተናገሩት ከሞቱት ሰዎች ህፃናት እንደነበሩበት ገልፀዋል።
ምሥራቅ አፍሪካ አሁንም ለጋዜጠኞች አስቸጋሪ ቦታ እንደሆነ ለመረጃ ነጻነት የሚሟገተው አርቲክል 19 አስታወቀ።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀዉ የዓለም የፕሬስ ነፃነት በዓል ለመታደም ኬንያ ናይሮቢ ገብቷል።
ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀው የዓለም የፕሬስ ነፃነት በዓል ለመታደም ኬንያ ናይሮቢ ገብቷል። በዝግጅቱ ላይ እስክንድር ንግግር እንደሚያደርግና የግል ታርኩን ለታዳሚዎች እንደሚያካፍልም ታውቋል።
ትላንት ጠዋት በሞያሌ በደረሰዉ ግድያ የተጠረጠሩ ሁለት ሰዎች በፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሞያሌ ወረዳ ፖሊስ አስታወቀ።
ዛሬ ረፋድ በሞያሌ ተከስቶ በነበረዉ አለመረጋጋት 3 ሰዎች ሞተዉ ከ 50 በላይ የሚሆኑት ከባድ ና ቀላል የመቁሰል አደጋ እንደደረባቸዉ ነዋሪዎች ለአሜርካ ድምፅ ተናግረዋል። ግጭቱ የተከሰተዉ በሞያሌ 02 ቀበሌ መናኸርያ በሚባል ቦታ ሲሆን አንድ የእጅ ቦምብ መወርወሩንና ሽጉጥ መተኮሱን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
የኬንያ መንግሥት “የብሔራዊ ንቅናቄ መሪ” በማለት ራሳቸዉን የሚጠሩት ሚጉና ሚጉና ወደ ሀገር እንዳይገቡ ከለከለ።
ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ ተሰደው የሚገኙ ተፈናቃዮች ምግብና መጠለያ በማጣት ችግር ላይ መሆናቸውን ተናገሩ። ለተፈናቃዮቹ ዕርዳታ እያደረገ ያለው የኬንያ ቀይ መስቀል በበኩሉ ማምሻውን ባወጣዉ መግለጫ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ በመሰደድ ላይ ያሉ ሰዎች ቁጥር እያሻቀበ መሆኑን ገልፀዋል።
የባለፈው ቅዳሜ ግድያ ሸሽተው በኬንያ ሰፍረው የሚገኙ የኢትዮጵያ ስደተኞች ዘላቂ መፍትሄ እንዲያገኙ የዓለምቀፉ የስደተኞች ድርጅት /ዩኤንኤችሲአር/ ተጨማሪ የሰው ኃይል ወደ ቦታው ሊልክ መሆኑን የድርጅቱ ኬንያ ቅርንጫፍ ቃል አቀባይ ዩቮን ንዴጌ ተናገሩ።
ባለፈዉ ዓርብ በኬንያዉ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና በፖለቲካ ተቃዋሚያቸው ራይላ ኦዲንጋ መካከል የተደረገው ሥምምነት ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ ጥምር አባላት አላካተተም ሲሉ የኬንያ ተቃዋሚ ፓርቲ ጥምር ናሽናል ሱፐር አሊያንስ አባላት ተናገሩ።
የኬንያው ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከተቃዋሚዉ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ ጋር ዛሬ በኬንያ ብሔራዊ ቤተመንግሥት ተወያዩ። ከውይይታቸዉ በኋላ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኬንያታ የአገራቸዉን የወደፊት ዕጣ ፈንታን የተሳካ ለማድረግ መሪዎች መነጋገርና መፍትሄ መፈለግ እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።
የታንዛኒያ ፍርድ ቤት በ84 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ላይ የ3 ዓመት እሥራት አስተላለፈ። ኢትዮጵያዊያኑ የተያዙት በታንዝኒያ ማዕከላዊ ክፍል “ኢሪንጋ” በሚባል ቦታ ሲሆን በህገ ወጥ መንገድ ወደ ማላዊ ሊያልፉ ሲሉ ነው - በታንዛኒያ ፖሊስና በሀገሪቱ ኢሚግሬሽን ኃላፊዎች የተያዙት።
በኬንያ ባሉ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ስደተኞች የዓለም ምግብ ፕሮግራም የምግብ ዕርዳታ በመቅነሱ ለረሃብ መጋለጣቸውን ተናገሩ።
ባለፈው ሳምንት መጀመርያ የተጠናቀቀው የኢትዮጵያ መንግሥትና የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግምባር ድርድር ሁለቱ ተደራዳሪዎች ከስምምነት ሳይደርሱ ተጠናቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ